TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አጣርቼ እምርጃ ወስዳለሁ " - መንግስት ትላንትና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን አሰቃቂ ቪድዮ (የሰው ልጅ በህይወት እያለ ሲቃጠል የሚያሳይ) በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል። መንግስት ድርጊቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ሰሞኑን መፈፀሙን ገልጿል። ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ነው ያለው…
#Update

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር የወንጀል ምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው (መተከል ዞን) ረቡዕ መሰማራቱን ተሰምቷል።

ይህ ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን ከፍትህ ሚኒስቴር እና ፌደራል ፖሊስ በተውጣጡ መርማሪዎች የተዋቀረው ነው።

በዚህ የምርመራ ቡድን ውስጥ ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሶስት ባለሙያዎች መካተታቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ቀሪ ሁለቱ አባላት ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወከሉ ናቸው።

የወንጀል ምርመራው በሁለቱ የፌደራል ተቋማት የሚከናወን መሆኑን እና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአጋዥነት ሚና እንደሚኖረው " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የየፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በመተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ፣ አይሲድ ቀበሌ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመው በህይወት ያለን ሰው አቃጥሎ የመግደል ድርጊት በመንግስት የጸጥታ አባላት ተሳትፎ ጭምር መከናወኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው እሁድ አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።

መንግስትም ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ቀብቶ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ #ሩሲያን በማውገዝ እና ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ድምፅ ሠጠ። በዚህም ከ193 ሀገራት መካከል 141 ሀገራት ድጋፍ ሲሰጡ ፣ 5 ሀገራት ውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል፣ 35 ሀገራት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጨምሮ 13 ሀገራት በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሙሉ በሙሉ አልተሳተፉም። የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ…
" በዩክሬን ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም " - አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ

በቅርቡ ተጠርቶ በነበረው የተመድ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ብዙ የአፍሪካ ሃገሮች በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ላይ ተአቅቦ ማስመዝገባቸው “ሃገሮቹ ከማንም ጋር አለመወገናቸውን የሚያሳይ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ገለልተኛ መሆን እንደማይቻል” በድርጅቱ የአሜሪ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ አስታወቁ።

ዛሬ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የሩሲያን ወረራ መዘዝ አፍሪካዊያኑ ሃገሮች እንዲገነዘቡት ለማድረግ ተጨማሪ ጥረቶች እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

“[ሃገሮቹ] ያንን አቋም መያዛቸው መብታቸው ቢሆንም ሁኔታውን ከዓለምአቀፍ ሥርዓት አኳያ መመልከትም ትክክለኛው አካሄድ ነው” ብለዋል።

“ይህ ቀዝቃዛ ጦርነት አይደለም " ያሉት አምባሳደሯ " በአሜሪካና በሩሲያ ወይም በምዕራቡና በሩሲያ መካከል ያለ ፉክክርም አይደለም።” ሲሉ ተደምጠዋል።

በመቀጠልም ፤ “ ይህ ሩሲያ በጎረቤቷ ላይ የከፈተችው ጥቃት ነው፤ ሩሲያ በመንግሥታቱ ድርጅት አስኳል እሴቶች ላይ የፈፀመችው ጥቃት ነው፤ እየተጋፈጥን ያለነው ዩክሬን ላይ ከፈፀመችው ጥቃት ጋር ነው ” ብለዋል።

“በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለ ወረራ ጦርነት አይደለም” ሲሉ አምባሳደሯ ማሰስባቸውን ቪኦኤ ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ከተመዘገበው የተአቅቦ ድምፅ ግማሽ ያህሉ የአፍሪካ ሃገሮች ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በድምፅ አሰጣጡ ላይ አልተሳተፈችም። በወቅቱ በነበረው ድምፅ አሰጣጥ ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ መሆኑ ከቀናት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#አዲስ_የልብ_ህክምና

የልብዎ ጤንነት ያለበት ሁኔታ ያውቃሉ?
ሙሉ የልብ ምርመራ በማድረግ የልብዎ ጤንነት ያለበትን ደረጃ ይወቁ። ይሄን ጥቅል በመግዛት ለወዳጅ ዘመዶ ያበርክቱ

ዛሬዉኑ ደዉለዉ ቀጠሮ ያስይዙ
0952343434

Telegram 👉:https://publielectoral.lat/addiscardiachospitalplc

ለልብዎ ከልብ እንሰራለን
TIKVAH-ETHIOPIA
''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዛሬ ተገቢው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጾልኛል ሲል…
የቀጠለው ቅሬታ ...

የምስረቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ የተነሳው ቅሬታ ነፃ እና ገለልተኛ በሆኑ አካላት ተጣርቶ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠው ጠየቀ።

መምሪያው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ዉጤት በማስመልከት ለትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታ ማቅረቡን እና ተገቢ ምላሽ ሊሰጠዉ እንደሚገባም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዞኑ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ40 ት/ቤቶች በሶሻል ሳይንስ 15,222 ተማሪዎች ተፈትነው 1765 ተማሪዎች 11.6% ማለፋቸው በናቹራል/ተፈጥሮ/ሳይንስ ደግሞ 7,075 ተፈትነው 1,619 (22.8%) ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን ተመላክቷል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አስተራረም እና የውጤት አሞላል ችግር ያለበት መሆኑን በተደጋጋሚ ብንገልጽም የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነ ገልጿል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለቀረበው ቅሬታ ምክንያት ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል አንደኛው የአብርሃ አፅብሃ 2ኛ ድረጃ ት/ቤት አንድ ተማሪ (አማኑኤል ፀሐይ) በመጀመሪያ የተለቀቀው ውጤት 162 ሆኖ በኦንላይ ቅሬታ ቢያቀብርም ሳይፈታለት ቀርቶ በአካል በሀገር አቀፍ ፈተና አገልግሎት ቀርቦ ሲያስፈትሽ 647 ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።

ሌላው ተማሪዎች ፈተና ሲወስዱ በክልሉ ጦርነት የነበረበት ወቅት በመሆኑና ወላጆችም ግንባር የዘመቱ በመሆናቸው ተማሪዎች በስነልቦና ጫና ውስጥ ሆነው ፣ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየሰሙ መፈተናቸውን ይህ እየታወቀ እንደ ሰላማዊ ጊዜ ከሌሎች ክልሎች እኩል የመግቢያ ውጤት መወሰኑ ችግር ያለበት እና ኢፍትሃዊ እንደሆነ ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/East-Gojjam-03-19

@tikvahethiopia
#Ukraine #Russia

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ውጤት የሚያስገኝ የሰላም ንግግር በአስቸኳይ ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት በግዛታቸው ውስጥ ግዙፍ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ካለችው ሩሲያ ጋር " ካለምንም መዘግየት ትርጉም ያለው " የሰላምና የደኅንት ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል።

ይህ ሩሲያ በአገራቸው ላይ በከፈተችው ወረራ በፈጸመችው "ስህተት" የሚደርስባትን ጉዳት ለመቀነስ ያላት ብቸኛው እድል ነው ሲሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል።

" ለመገናኘት፣ ለመነጋገርና የዩክሬንን የግዛት አንድነት እንዲሁም ፍትህን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ዜሌነስኪ ለሩሲያ ጥሪ አቅርበዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ሩሲያ ከሚገጥማት ውድቀት ለመውጣት በርካታ ትውልዶችን መጠበቅ ሊያስፈልጋት ይችላል " ማለታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሀሙስ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አገራቸው ጦርነቱን ለማቆም ከዚህ በፊት ይፋ አድርጋው የነበረውን ቅድመ ሁኔታዎች በድጋሚ ገልፀዋል።

ዋነኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ፦

- ዩክሬን NATOን እንደማትቀላቀል ማረጋገጥ።

- ዩክሬን ትጥቅ እንድትፈታ፣

- በዩክሬን የሩሲያ ቋንቋ እንዲከበር እና የናዚ አመለካከት አራማጅ ናቸው የተባሉ ኃይሎችን ዩክሬን እንድትቆጣጠር፣

- ክራይሚያ የሩሲያ ግዛት መሆኗን፣ በቅርቡ ነጻነታቸውን ላወጁት ምሥራቃዊ የዩክሬን ግዛቶች ደግሞ እውቅና እንድትሰጥ ዋነኞቹ የሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።

@tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PMOEthiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ (ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ) @tikvahethiopia
#Turkey #Ethiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል።

ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል።

በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ አንካራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቀት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ/ም የተፈረሙ ሶስት ስምምነቶች ለምክር ቤቱ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ገልጿል።

ከስምምነቶቹ አላማ ፦

👉 በትምህርትና ስለጠና፣
👉 የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች፣
👉 በመከላከያ ኢንዱስትሪ ግንባታ፣
👉 የሳይበር ጥቃት መከላከል፣
👉 በሰላም ማስከበር፣
👉 የወታደራዊ ፋይናንስ ትብበብር፣
👉 በባህር ላይ ዉንብድና መከላከል ላይ በሚደረጉ ዘመቻዎች ለመተባበር የሚያስችል ማዕቀፍ መፍጠር ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ በቀረቡት ሶስት የሁለትዮሽ ስምምምነቶች ላይ በመወያየት ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ መወሰኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ NATO በኖርዌይ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገ ይገኛል።

በዚሁ ልምምድ ላይ የነበረ አንድ ንብረትነቱ የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከስክሷል።

በአውሮፕላን የመከስከስ አደጋው አራት ሰዎች እንደሞቱ ተረጋግጧል።

ከላይ የተያያዘው አጭር ቪድዮ የNATO ኃይሎች በኖርዌይ እያደረጉ ያሉትን ወታደራዊ ልምምድ የሚያሳይ ነው።

ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የNATO ኃይሎች ከሩስያ ጋር ከፍተኛ መካረር ውስጥ እንደገቡ ይታወቃል።

ዩክሬን በተደጋጋሚ ከሩስያ እንዲታደጓት ለምዕራባውያኑ ጥሪ ብታቀርብም NATO የአባል ሀገራቱ ላይ የሚሰነዘር ጥቃትን መከላከል እንጂ ወደ ዩክሬን የመግባት እቅድ እንደሌለው በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዛሬ ተገቢው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጾልኛል ሲል…
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናና ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ።

ፎረሙ ጥያቄውን ያቀረበ ዛሬ ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ነው።

የመግቢያ ፈተናውን ውጤት ተከትሎ የሚወጡት መረጃዎች ያልተለመዱና አስደንጋጭ ናቸው ያለው ፎረሙ በተወሰኑ ተማሪዎችና ወላጆች ግፊትና ጫና የተስተካከሉ ውጤቶች ለተፈጠረው ስሕተት ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።

የአማራ ትምህርት ቢሮ የሁሉንም ትምህርት ቤቶች ውጤት ዝርዝር መረጃ በመሰብሰብ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚገባው የጠቆመው ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው ለማረም እድል ያገኛሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

በተማሪዎችና ወላጆች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ሁሉም ወገን በቅንነት ተቀብሎ የድጋሜ እርማትን እና ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ በዜጎች ዘንድ ፍትሐዊነትና ተዓማኒነት ከማረጋገጡም በላይ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ይጠቅማል ሲል አሳስቧል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተናውና ውጤቱ ላይ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አቻችሎና ሰምቶ በመተው የሚፈቱ ሳይሆን የትውልዱን እድል የሚወስኑ በመኾናቸው በፍጹም አካዳሚያዊ ሥነ ምግባርና ከፍተኛ መሆን አለበት ብሏል።

ፎረሙ ሁሉም አካላት ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጠይቋል።

ፈተና በደቦ እየተሠራ መልካም ትውልዶችን መፍጠር አይቻልም ያለው ፎረሙ ጉዳዩ ከብሔር አውድ ፍፁም ነጻ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ ጠይቋል።

ተማሪዎችና ወላጆች ጥያቄው መልስ እስኪያገኝ ተረጋግተው እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናና ውጤት ላይ እርማት እንዲደረግ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ። ፎረሙ ጥያቄውን ያቀረበ ዛሬ ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ነው። የመግቢያ ፈተናውን ውጤት ተከትሎ የሚወጡት መረጃዎች ያልተለመዱና አስደንጋጭ ናቸው ያለው ፎረሙ በተወሰኑ ተማሪዎችና ወላጆች ግፊትና ጫና የተስተካከሉ ውጤቶች ለተፈጠረው ስሕተት ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ብሏል። የአማራ ትምህርት…
" .. የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው ይራዘምልን " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ።

ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ ቢሮው የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል።

ቢሮው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ነው።

@tikvahethiopia
PHOTO : የ2022 የቤል ግሬድ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ትላንት ለሊት ላይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን🇪🇹 አትሌቶቻችን ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በ1500 ሜትር ሴቶች ውድድር ፦

1ኛ. አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ለሀገራችን ስታስገኝ ፤
2ኛ. አክሱማዊት እምባዬ ለሀገራችን የብር ሜዳሊያ አገኝታለች፡
3ኛ. ሂሩት መሸሻ ሶየነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራችን አስገኝተያለች።

ለሀገሯ ወርቅ ያስገኘችው ጉዳፍ 3:57.19 የገባችበት ደቂቃ አዲስ የሻምፒዮናው ሪከርድ ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ በ3,000 ሜትር ሴቶች ውድድር በለምለም ኃይሉ ባገኘችው ወርቅ እና እጅጋየሁ ታዬ ባገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ የሻምፒዮናውን የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በሁለት ወርቅ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ 5 ሜዳሊያዎች በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች።

More : @tikvahethsport