PHOTO : የ2022 የቤል ግሬድ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ትላንት ለሊት ላይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን🇪🇹 አትሌቶቻችን ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በ1500 ሜትር ሴቶች ውድድር ፦

1ኛ. አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ለሀገራችን ስታስገኝ ፤
2ኛ. አክሱማዊት እምባዬ ለሀገራችን የብር ሜዳሊያ አገኝታለች፡
3ኛ. ሂሩት መሸሻ ሶየነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራችን አስገኝተያለች።

ለሀገሯ ወርቅ ያስገኘችው ጉዳፍ 3:57.19 የገባችበት ደቂቃ አዲስ የሻምፒዮናው ሪከርድ ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ በ3,000 ሜትር ሴቶች ውድድር በለምለም ኃይሉ ባገኘችው ወርቅ እና እጅጋየሁ ታዬ ባገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ የሻምፒዮናውን የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በሁለት ወርቅ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ 5 ሜዳሊያዎች በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች።

More : @tikvahethsport