TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA #Election

" ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች " የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " በማለት ተናገሩ።

ትራምፕ ይህ ያሉት #ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት " ኒው ሃምሻየር " ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።

ትራምፕ ለ4 አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።

ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

" ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር " ናሽናል ፐልስ " ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች " ደማችንን እየበከሉት ነው " የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር " ዘረኝነት እና ጥላቻ " የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።

የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን አሁንም ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።

ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ " የጀርመኖች ደም በጅዊሾች እየተበከለ ነው " የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ ነው ሲሉ ተችተውታል።

ስታሊ" ትራሞፕ ይህ ቃል በሁሉም የድጋፍ ሰልፎች ላይ እየደገሙት ነው። አደገኛ  የሆኑ ንግግሮችን መደጋገም እንዲለመዱ ያደረጋል " ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ እንደተናገሩት ይህ በአሜሪካ የሚኖሩ ስደተኞችን ስጋት ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቴቨን ቹንግ እንዲህ አይነት ቃላት በመጽሀፍ፣ በዜና እና በቴሌቪዥን የተለመድ ናቸው በማለት በትራምፕ የቀረበውን ትችት " ትርጉም የለሽ " ሲሉ አጣጥለውት ነበር።

Credit - AL AIN News

@tikvahethiopia