TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrMatshidisoMoeti 

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ '#አፍሪካ' ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ እንዳሉት በቂ ምርመራ እየተደረገ ባለመሆኑና የመከላከያ አቅርቦቶችም በቂ ባለመሆናቸው ቫይረሱ ከዋና ዋና ከተማዎች አልፎ በገጠር አካባቢዎችም ስሩን እየሰደደ ነው።

ነገር ግን የቫይረሱ ስርጭት አሁንም ቢሆን ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆ እና የሚመዘገቡ ሞቶች በመንግሥታት ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ መናገራቸውን #BBC ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#USA

"የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም" - አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ ትላንት እሁድ በሰጡት ቃል አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ብቸኛው መፍትሄ ዲፕሎማሲ ነው ብላ ታምናለች ብለዋል።

ከTeN የሳተላይት ቻናል ቃለምልልስ የነበራቸው ዋርበርግ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ለአፍሪካ አህጉር እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ዓላም አቀፉ ማህበረሰብ የህዳሴው ግድይ ጉዳይ ለናልይ ተፋሰስ ቀጠና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ተገንዝቧል ብለዋል።

ዋርበርግ፥ የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በማንሳት "በአፍሪካ አህጉር ምንም አዲስ ጦርነት ልንገምት አንችልም" ብለዋል።

የተፋሰሱ አገራት እና የ #አፍሪካ_ህብረት ድርድርን እንደገና መጀመር እንዳለባቸው ጠቁመው አሜሪካ ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ዋርበርግ፥ "ውይይቱን ለመቀጠል አሜሪካ ሁሉም ወገኖች ከማንኛውም መግለጫ እንዲታቀቡ ጥሪ ታደርጋለች ፤ የሚደረገው ማንኛውም ውይይት ድርድሮችን ወደፊት ለማስቀጠል ያለመ መሆን ይገባዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ድርድሩ ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያልፍ አትፈልግም ብለዋል።

@tikvahethiopia
#GoE

የፌዴራል መንግስት በቅርቡ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች የልዑካን ቡድን " የህወሃትን የውሽት ትርክት አስተጋብቷል፤ ይህም ስህተት ነው " ብሏል።

ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ላይ መንግሰት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም ስምምንት ለማድርግ ወሰኖ እንደነበር እና አሁንም #ለሰላም ውይይት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የምግብ ድጋፍ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት ተደራሽ እየተደረገ ነው ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " መንግስት ወደ ትግራይ የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ ባላቋረጠበት እና ክልከላዎች ባላደረገበት ወደ መቐለ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኞችን የያዘው የዲፕልማቶች ቡድን የህወሓት የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው " ብለዋል።

መንግስት በ #አፍሪካ_ህብረት በኩል የሚካሄደው የሰላም ውይይት ሁሌም በማንኛውም ቦታ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት በህወሃት በኩል ከሰላም ድርድር ፍላጎት ይልቅ አሁንም የጦርነት ጉሰማዎችና ለሰላም ውይይት እንቅፋት የሚሆኑ ንግግሮች እየተሰሙ ነው ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ? የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል። በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል። ዜጎችን ከ "ህወሓት"…
#ተመድ #አፍሪካ_ህብረት

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት ጉተሬዥ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።

" ኢትዮጵያውያን ትግራዋዮች፣ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች ፣ አፋሮች ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" አጠንክሬ የምጠይቀው በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የመንግስትና የህወሓት የሰላም ድርድር እንዲቀጥል ነው " ብለዋል።

ጉተሬዥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሙሉ ዋስትና እንዲሰጠው ፤ በተጨማሪ የህዝብ አግልግሎቶች ተመልሰው እንዲቋቋሙ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኢትዮጵያ እንደገና ወታደራዊ ግጭት መፈጠሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች መስማታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፤ ሁኔታውን እየተከታተሉ መሆኑንም አመልክተዋል።

ሊቀመንበሩ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ንግግሩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት #የሀገሪቱን_ጥቅም_ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሂደትን ለመደገፍ ከሁሉም ወገን ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።

ለዚህም ሁሉም ወገኖች ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#ሩስያ #አፍሪካ

ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሁለት ቀናት ጉባኤ ተቀምጠው የነበሩት የአፍሪካ መሪዎች፣ ከዩክሬን ለዓለም ገበያ እህል መቅረብ እንዲቀጥል ያቀረቡትን ጥያቄ በተመለከተ እንዲሁም በዩክሬን በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ አንዳች መፍትሄ ላይ ሳይደርሱ መበተናቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ቭላድሚር ፑቲን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ከዩክሬን እህል ወደ ዓለም ገበያ የሚቀርብበትን ስምምነት በዚህ ወር ማቋረጣቸው፣ የእህል ዋጋ እንዲጨምር አድርጎ የሩሲያ ኩባንያዎችን ተጠቃሚ አድርጓል ብለዋል።

ሞስኮ የተወሰነውን ትርፍ ከድሃ ሀገራት ጋር እንደምትጋራ ፑቲን ጨምረው ገልጸዋል።

ፑቲን በተጨማሪ ሩሲያ በአፍሪካ መሪዎች የቀረበውን የሰላም ሃሳብ ታጤነዋለች ብለዋል።

ከ25 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ቶን እህል ለስድስት አፍሪካ ሀገራት በነጻ እንደሚሰጥ ፑቲን ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር። እነዚህም፤ ቡርኪና ፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ናቸው።

ፑቲን ቃል የገቡት እህል መጠን የተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እህል ከዩክሬን በሚወጣበት ስምም ነት መሠረት ገዝቶ ረሃብ ለተጋረጠባቸው ሀገራት ካሰራጨው 725 ሺሕ ቶን እህል ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው ተብሏል።

54 ከሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ውስጥ በጉባኤው የተሳተፉት 17 ብቻ ናቸው ፤ እ.አ.አ በ2019 በተደረገው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ 43 የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር።

የአሁኑ የተሳታፊዎች ቁጥር መቀነስ " በምዕራባውያን ግፊት የመጣ ነው " ስትል ሞስኮ እንደምትከስ ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 አባል ሆነ። ቡድን 20 " ታሪካዊ ነው " በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት ስብስብ የሆነው ቡድን ሃያ አባላት ውሳኔ ታሪካዊ ተሰኝቷል። 55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 (G20) አባል አገራትን ተቀላቅሏል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ…
#G20

አፍሪካ ህብረት " ቡድን 20 " ን በቋሚ አባልነት መቀለቀሉን ተከትሎ የቡድኑ ዝርዝር ይህን ይመስላል።

🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት
🌍 #አፍሪካ_ሕብረት

@tikvahethiopia
" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን የጤና ባለሞያዎች ቁጥር የሚስደነግጥ ነው " - ካሉምቢ ሻንጉላ

አፍሪካ የጤና ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ በናሚቢያ ዋና ከተማ ፤ #ዊንድሆክ በዚህ ሳምንት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የጤና ባለሞያዎች ፎረም ላይ ነው ይህን ያሳወቀው።

ፎረሙ ላይ የናሚቢያ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎት ሚኒስትር ካሉምቢ ሻንጉላ ፥ " #አፍሪካ ያጋጠማት የጤና ባለሙያዎች እጥረት አህጉሪቱ እ.አ.አ በ2030 ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማግኘት የያዘችውን እቅድ እንዳታሳካ እንቅፋት ይሆናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የተሻለ ህይወት ፍለጋ አህጉሩን ጥለው የተሰደዱ አፍሪካውያን ቁጥር #የሚስደነግጥ_ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህን ጉዳይ የአፍሪካ መንግስታትም ሆኑ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ተለውጠው ማየት የሚሹ በሙሉ ቅድሚያ ሰጥተው ሊፈቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።

የአፍሪካ በሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳይሬክተር ጀነራል ጂን ካሳያ እንዳስታወቁት፣ እ.አ.አ በ2030 ለመድረስ የታቀደውን ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ለማሳካት አፍሪካ ተጨማሪ 1.8 ሚሊየን የጤና ሰራተኞች ያስፈልጓታል።

በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ 1.55 የጤና ባለሙያዎች ለአንድ ሺህ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ፣ ይህም ለ1 ሺህ ሰዎች 4.55 የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ገደብ በታች ነው።

እ.አ.አ በ2023 ብቻ አፍሪካ " 166 ወረርሽኞች "ን መመዝገቧን ያመለከቱት ካሳያ ፤ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እ.አ.አ በ2030 ሁለት ሚሊየን የቋማዊ የማህበረሰብ የጤና ሠራተኞችን እንዲመለምሉ እንዲያሰለጥኑና ወደ ስራ እንዲያሰማሩ የተወሰነውን ውሳኔ ለማሳካት በጣም ወደኃላ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia