TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ላከች።

ሀገሪቱ 35 ቶን ምግብ የጫነ አውሮፕላን ወደ የትግራይ ክልል መዲና መቐለ በዛሬው እለት መላኳን ገልጻለች፡፡

በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም አልረሽድ ፥ " የተደረገው የምግብ እርዳታ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ ለመርዳት ነው " ብለዋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ድጋፍ የምታደርገው ድጋፍ ለሚሹ ሀገራት ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ ባላት ቁርጠኝነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

" የምግብ እጥረት ላለበት ህዝብ አስፈላጊ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ ኢምሬትስ ትሻለች " ሲሉ የገለጹት አምባሳደሩ " ይህ እርዳታ የተበረከተው ኢምሬትስ አስቸኳይ እርዳታ ለመፈልጉ ሀገራት ለመድረስ ባላት ቁርጠኝነት ነው " ብለዋል፡፡

አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም ረሺድ ፥ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ባለፈው አመት 200 ቶን የአትክልት ዘይትን ጨምሮ 300 ቶን እርዳታ መቐለ ማድረሷን መግለፃቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Professor

11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጣቸው።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲ የውስጥና ውጭ ገምጋሚዎች በጥልቀት ተመርመሮ ፣ በኮሌጆች የአካዳሚክ ኮሚሽኖች ተፈትሾ ፣ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ታይቶና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን መረጃ ከተመለከተ በኋላ የየኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው፦

1. ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ፣  
2. ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ፣  
3. ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ፣
4. ዶ/ር ጉታ ዘነበ፣
5. ዶ/ር ፋሲል አሰፋ፣  
6. ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ፣
7. ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ፣  
8. ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ አለሙ፣  
9. ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ፣  
10. ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና
11. ዶ/ር ንጉሴ ደየሳ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምሁራኑ የ #ሙሉ_ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው
በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማኅበረሰብ ዐቀፍ እና ሙያዊ አገልግሎት የነበራቸው አበርክቶ ተገምግሞ መሆኑ ታውቋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#AfCFTA

ሁለት ኢትዮጵያውያን ሹመት ተሰጣቸው።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት ሴክሬታሪያት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና አቶ ታፈረ ተስፋቸውን የንግድ እና ኢንዱስትሪያል ልማት አማካሪ ምክር ቤት አባል አድርጎ መሾሙን ሪፖርተር ጋዜጣ [እንግሊዘኛው ክፍል] ዘግቧል።

ዶ/ር አርከበ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐብይ አህመድ ልዩ አማካሪ ሆነው በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ በከፍተኛ የመንግስት አመራርነት እንዲሁም በፖሊሲ ቀረፃ ላይ ተሳትፈዋል፤ በፖሊሲ አውጪው ክበብ ላይም ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ቁልፍ ሰው ናቸው።

አቶ ታፈረ ተስፋቸው ደግሞ ከንግድ እና ከልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ አማካሪ ሲሆኑ የተመድ የንግድ እና ልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) በአፍሪካ በኢኮኖሚ ወደ ኃላ የቀሩ ሀገራት ክፍል ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

ከዶ/ር አርከበ ዕቁባይ እና ከአቶ ታፈረ ተስፋቸው በተጨማሪ የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ካርሎስ ሎፔዝ ከአማካሪ ምክር ቤቱ 14 አባላት መካከል አንዱ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል።

አዲስ የተቋቋመው ምክር ቤት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ስምምነት ትግበራ አካል ሆኖ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የማማከር ስራ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ምስረታ በየካቲት ወር በተካሄደው የመሪዎች እና መንግስታት ጉባኤ ላይ ነበር የፀደቀው።

@tikvahethiopia
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች።

ትላንትና ለሊት ሰሜን ኮሪያ የተጠረጠረ ባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ ተጨማሪ መረጃ ሲያገኝ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

ሚሳኤሉ ወደ ጃፓን ባህር አቅጣጫ መወንጨፉ ነው የተነገረው።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ሰ/ኮሪያ ሚሳኤል ማስወንጨፏን ገልጻ ሚሳኤሉ በምስራቅ አቅጣጫ በኩል የተወነጨፈ ነው ብላለች።

ባለፈው ጥር ወር ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ በተደጋጋሚ ሚሳኤል እያስወነጨፈች ሙከራ ስታደርግ የነበረችው ሰሜን ኮሪያ አሁን አስወነጨፈች የተባለው ሚሳኤል በዚህ ወር የመጀመሪያዋ ነው።

ስለ ትላንትናው ለሊት የሚሳኤል ማስወንጨፍ ጉዳይ በሰሜን ኮሪያ በኩል የተሰማ ነገር የለም።

ከፔንታጎን ወይም ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኩል ወዲያውኑ የተሰጠም አስተያየት የለም።

ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ ዋሽንግቶን ከሰሜን ኮሪያ ጋር " ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ " ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ብትልም ፒዮንግያንግ " ቅንነት የጎደለው " መሆኑን በመግለፅ እስካሁን የአሜሪካን ጥያቄ አልተቀበለችም።

@tikvahethiopia
#Ukraine #Russia

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በበርካታ ታዳጊ ሀገራት እንዲሁም ባደጉት ሀገራት ጭምር የሚያሳድረው ተፅእኖ የበረታ እንደሚሆን እየተገለፀ ነው።

በተለይ በጦርነቱ ከ2ቱ ሀገራት ውጭ NATO የመሰሉ ኃይሎች የሚቀላቀሉ ከሆነ ዓለማችን እጅግ የከፋ ቀውስ ውስጥ ትገባለች ተብሎ ተፈርቷል።

እስካሁን ምዕራባውያን ከሩስያ ጋር ጦር ባይማዘዙም የማዕቀብ ናዳ ሩስያ ላይ እያወረዱ ዩክሬንን በመሳሪያ እያስታጠቁ የሚያስፈልግሽን ሁሉ ድጋፍ እናደርግልሻለን እያሉ ይገኛሉ።

ጦርነቱ እንዲሁ በቀላሉ የማታይ አይደለም፤ በተዋጊዎቹ ሀገራት መካከል የሚረግፈው የሰው ህይወት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢኮኖሚያቸው ይዳከማል። በርካታ ሀገራትን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል። እስካሁን በነዳጅ፣ በስንዴ፣ በተፈጥሮ ጋዝ...ዋጋ ንረት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ የሚታይ ነው።

ተጎጂዎቹ ግን ታዳጊ ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ያደጉትንም ያካትታል።

ለምሳሌ፦ ዩናይትድ ኪንግደምን ብንመለከት ተንታኞች በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ባለፉት አሥርተ ዓመታት ባልታየ ፍጥነት የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ይጠቁማሉ።

ካረን ዋርድ የተባሉ አንድ ተንታኝ በግጭቱ ምክንያት የሚከሰቱ ኢኮኖሚያዊ ውድቀቶች የዋጋ ግሽበት 8 በመቶ ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጨምሯል ያሉት ተንታኙ ይህም የዩናይትድ ኪንግደም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጓል ብለዋል።

ሩሲያ ትልቅ #የማዳበሪያ ላኪ በመሆኗ የምግብ ምርት ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋትም አለ።

ጦርነቱ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ይገኝ እንደሆነ አንዳችም ፍንጭ ማየት አልተቻለም። በየዕለቱ እየተባባሰ ዓለምን ህዝብ ስጋት ከፍ እንዳደረገ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ከዩክሬን ጋር ልትነጋገር ነው። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ሊልኩ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የተሰማው የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ከተናገሩ ከሰዓታት በኃላ ነው። ሞስኮ ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያላትን ጥያቄ እንድታቆም እና ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ትፈልጋለች። ሚኒስክ…
" ቤላሩስ ውስጥ አንደራደርም " - የዩክሬን ፕሬዜዳንት

ሩስያ የልዑካን ቡድኗ ከዩክሬን አቻው ጋር ለመነጋገር ቤላሩስ መግባቱን አሳውቃለች።

የሩስያ ልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ደግሞ የፕሬዚዳንት አስተዳደርን ያካተተ እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ሀገሪቱ ንግግሮችን በጎሜል ለመጀመር ዝግጁ ነኝ ብላለች።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሩስያ ጋር በቤላሩስ #እንደማይደራደሩ አሳውቀዋል። ምክንያቱ ደግሞ ቤላሩስ ፤ ሩስያ ሀገራቸውን ለማጥቃት እየተጠቀሙባት በመሆኑ ነው።

ሀገራቸው ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኗን ግን ገልፀዋል።

ከቀናት በፊት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደ ቤላሩስ ሊልኩ መሆኑ መነገሩ ይታወቃል።

በዚህም የልዑካን ቡድኑ ቤላሩስ ቢደርስም ዩክሬን በቤላሩስ እንደማትደራደር ገልፃለች።

@tikvahethiopia
#Somalia

አሜሪካ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች።

አሜሪካ ፤ " የሶማሊያን የዲሞክራሲ ሂደት አደናቀፈዋል " ባለቻቸው በርካታ የሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች።

ሶማሊያ የሕግ አውጭ ም/ቤት አባላት ምርጫ ምታጠናቅቅበትን ቀነ ገደብ ተፈፃሚ ሳታደርግ ቀርታ በድጋሚ ወደ መጋቢት 6 አራዝማለች። የካቲት 25 መጠናቀቅ የነበረበት ምርጫ ነው ወደ መጋቢት 6 ያራዘመችው።

ሁኔታው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውም እንዲራዘም ሊያስገድድ ይችላል እየተባለ ነው።

በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎች እስካሁን አልተሟሉም።

ከዚህ ጋር ተያይዞ አሜሪካ የሶማሊያን የዲሞክራሲ ሂደት አደናቅፈዋል ባለቻቸው በርካታ ባለስልጣናት ላይ የቪዝ እገዳ ጥላለች።

ሶማሊያ የህግ አውጪ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን "ግልጽና ተአማኒ በሆነ መንገድ እንድታጠናቅቅ " ስትል አሳስባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል ይገኛሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ሆስፒታል በመገኘት ጠይቀዋቸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሕመም ምክንያት በሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ…
ፎቶ ፦ አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል እንደሚገኙ ይታወቃል።

ትላንት ቅዳሜ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሆስፒታል በመገኘት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን መጎብኘታቸው እና እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸው ጸሎት በማድረስ መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ሆስፒታል በመገኘት ጎብኝተዋቸዋል።

በተጨማሪ የኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም ቅዱስነታቸውን ጎብኝተዋቸዋል። ፕሬዜዳንቷ በቀደመው ጊዜ የቅዱስነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጅ መሆናቸውን ገልፀው በቶሎ ድነው ከሆስፒታል እንዲወጡ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ቅዱስነታቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በመደበኛ ክል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል አለመግባታቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia
አቶ ተስፋየ አባተ ተገደሉ።

የሀብሩ ወረዳ ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተስፋየ አባተ ያዘው መገደላቸው ተሰማ።

ኃላፊው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመተው #ከትዳር_አጋራቸው ጋር ህይወታቸው ማለፉን የሀብሩ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቤላሩስ ውስጥ አንደራደርም " - የዩክሬን ፕሬዜዳንት ሩስያ የልዑካን ቡድኗ ከዩክሬን አቻው ጋር ለመነጋገር ቤላሩስ መግባቱን አሳውቃለች። የሩስያ ልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ደግሞ የፕሬዚዳንት አስተዳደርን ያካተተ እንደሆነ ነው የተገለፀው። ሀገሪቱ ንግግሮችን በጎሜል ለመጀመር ዝግጁ ነኝ ብላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሩስያ…
#Update

ዩክሬን ከሩስያ ጋር ለመነጋጋር ተስማምታለች።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቢሮ ፤ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዘሌንስኪ ዛሬ ደውለውላቸው እንደተነጋገሩ ገልጿል።

የዩክሬን ልዑካን ከሩሲያ ልዑካን ጋር " ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ " በዩክሬን-ቤላሩስ ድንበር በፕሪፕያት ወንዝ አቅራቢያ ተገናኝተው ለመነጋገር መስማማታቸውን ቢሮው አሳውቋል።

አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በቤላሩስ ግዛት ያሉ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሚሳኤሎች የዩክሬን ልዑካን በሚጓዙበት፣ ተገናኝተው በሚነጋገሩበት እና በሚመለሱበት ጊዜ ያለንአንዳች እንቅስቃሴ እንደሚቆዩ ሃላፊነት መውሰዳቸው ተነግሯል።

የሩስያ መንግስት ዜና ተቋማት የዩክሬን ልዑክ ከሩስያ ልዑክ ጋር በቤላሩስ ፣ ጎሜል ክልል ለመነጋገር መስማማታቸውን ዘግበዋል፤ የዩክሬን ልዑክን ወክለው ስለሚገኙ ሰዎች ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።

ይህ የስምምነት ከመሰማቱ ቀደም ብሎ ዩክሬን በቤላሩስ ከሩስያ ጋር እንደማትነጋገር ገልፃ ነበር፤ ምክንያቷ ሩስያ ሀገሪቱን እንድታጠቃ ቤላሩስን እየተጠቀመች በመሆኑ ነው።

በኃላም የሩስያው ልዑክ የውይይቱን ሃሳብ ያቀረበች እራሷ ዩክሬን ናት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ (በቤላሩስ ሰዓት አቆጣጠር) የዩክሬን ልዑካንን እንጠብቃለን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ነገር ኃላፊነቱን እራሷ ትውስዳለች ሲል አስፈራርቶ ነበር።

@tikvahethiopia