TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ ይለቀቁ " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የኢፌዲሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ አበረታች እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ፤ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የነበረው ሁኔታ በመሻሻሉና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት የአዋጁ አስፈላጊነት እየተገመገመ ተገቢው ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ የነበረ መሆኑ አስታውሷል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት በመንግስት የቀረበለትን ውሳኔ ሃሳብ በአፋጣኝ እንደሚያጸድቀው ኢሰመኮ ተስፋውን የገለፀ ሲሆን የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪውን አቅርቧል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው አዋጅ የተነሳ መሆኑን ከሚያጸድቅበት ቀን ጀምሮ ከእስር ያልተለቀቁ ሰዎች የሚኖሩ ቢሆን፤ ከ48 ሰዓታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት አለመቅረብ እስሩ ከሕግ ውጭ የሚያደርገው በመሆኑ የሁሉም የሕግ አስከባሪ አካላት የሕግ ማስከበር ተግባራት የሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ በመደበኛው ሥርዓት እንዲከናወኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት /USAID/ አማካይነት በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል፣ 400ሺ በላይ ሰዎችን ኑሮ ሊያሻሽል የሚችል፣ በ10.2 ቢሊዮን ብር ሁለት አዳዲስ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በኢፋ /Iffa/ እና በUSAID ተግባራዊ የሚደረጉ 2ቱ የመዋዕለ ንዋይ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ መንግሥት የሚመራውንና 9 ሚሊዮን ሰዎች ራሳቸውን ከድህንነት እንዲያወጡ የሚያግዘውን የማኅበራዊ የምርት ደህንነት ወይም ሴፍቲኔት መርኃግብር እንደሚያጠናክር በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየተካሄዱት ለሚገኙ ተመሳሳይ መርኃግብሮች ቀዳሚውን ድጋፍ እየሰጠ ያለው ዩኤስኤድ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ እኤአ ከ2015 ጀምሮ ወደ 60 ቢሊዮን ብር ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

አሁን የሚካሄዱት ሁለቱ መርኃግብሮችም በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል የቆየውን ወዳጅነትና የጋራ ፍላጎት እንደሚያረጋግጡም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በዚህ ሳምንት ውስጥ ይፋ የተደረጉት ሁለቱ ፕሮጀክቶች USAID ባላፉት 5 ዓመታት ውስጥ በ220 ቢሊዮን ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ እያደረጋቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡

የሚሰጠው ድጋፍ በሁሉም አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ጤናማና የበለጸገ ህይወት እንዲመሩ የሚያግዝ መሆኑንም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ / ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#ተወዳደሩ #GenerationUnlimitedEthiopia

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀነሬሽን አንሊሚትድ መፍትሔ አምጪ የሥራ ሃሳቦችን ማወዳደር ጀምሯል።

ሚኒስቴሩ የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች ለማበረታታት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር የሚያከናውነው የ 2014 ዓ.ም የጀነሬሽን አንሊሚትድ ለውጥ አምጪ የወጣቶች ውድድር ይፋ ሆኗል።

የዚህ ውድድር ተልዕኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.8 ቢሊዮን ወጣቶችን ከተለያዩ ዕድሎች ጋር ማገናኘት መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአጋርነት እና ፈንድ ዳይሬክተር ፥ " ወጣቶችን የማገናኘት እና አቅማቸውን የማሳደግ እንቅስቃሴ በቀድሞ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ተጀምረው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀጠሉት አንዱ ሆኖ ይህ ዓለማቀፍ መሆኑ ይለየዋል " ብለዋል።

አክለውም ፤ " 35 በሚጠጉ አገራት መካከል የሚካሄድ፣ በአገራችን 5 ከተሞች ተከናውኖ በ 8 ሳምንታት የሚጠናቀቅ ፣ ሁለት ተወዳዳሪ ቡድኖችን ለዓለማቀፍ ውድድር የሚያዘጋጅ፣ ለአገራችን ወጣቶች ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዕድሉን ይጠቀሙበት " ሲል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ተወካይ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ሃሳቦቻቸውን አዳብረው የማኅበረሰባቸውን ችግር በመፍታት ተፅዕኖ ማሳደር እንዲችሉ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

ውድድሩ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦችን ስኬት ለማፋጠን የሚቀርቡ የፈጠራ ሃሳቦች ላይ አትኩሮ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሃሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መነሻ ገንዘብ ይመድባል።

የውድድር የማመልከቻ መቀበያው ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ሆኖ የካቲት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቅና ውድድሩ ይቀጥላል።

ይህንን ውድድር የተለያዩ ዓለማቀፍ ተቋማት የደገፉት ሲሆን ሥራው በፈርስት ኮንሰልት አማካኝነት ይከናወናል።

በኦላይን ለመመዝገብ 👉 https://bit.ly/3rQOERQ

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#AddisAbabaUniversity

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነፃ እና እራሱን የቻለ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ የተደራጀው ግብረ ሀይል ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሥራ አመራር ቦርድ ጋር የግብረ ሃይሉን የሥራ ማስጀመሪያና ትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡

መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተጎናፅፈው መስራት እንዲችሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት መልሶ እንዲደራጅ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቋማዊ ነጻነት መስጠት ከመንግስትም ከማህበረሰቡም ስምምነት የተደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ የለዉጥ ስራ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃማዊ ነጻነትን ማምጣት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ተቋማዊ ነጻነት የሚሰጥ መሆኑንም አሳውቀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ከፍተኛ ተቋማትም የሚስፋፋ መሆኑም ተገልጿል።

#MoE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይበቃል ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ፍትህን እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ተመልክተናል። ዘመቻው ሳዑዲ ያሉ ዜጎቻችን እምነበረድ ላይ ለብሰው የሚተኙትን ጥቁር ፌስታል በመልበስ አጋርነት የሚገለፅበት ነው። ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በርካታ ዜጎቻችን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል። የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

በሳውዲ ታሳሪዎች ጉዳይ ከንጉሥ ሰልማን ጋር ለመወያየት ለፊታችን ቅዳሜ ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት ለማሻሻልና በሳውዲ ታስረው የሚገኙና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸው ከፍተኛ የልዑክ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ከንጉስ ሰልማን ኢብኑ አብዱልአዚዝ ጋር ዉይይት ያደርጋሉ።

በተጨማሪ ልዑኩ በቆታው ከሳውዲ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

የልዑካን ቡድኑ ከሚኒስትሮች፥ከሃይማኖት አባቶች፥ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በኢትዮ-ሳውዲ ጉዳይ ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ግለሰቦች የተካተቱበት ነው።

ልዑኩ የተላከው የእስረኞችን ችግር ለመፍታትና የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል ልዑክ በመላክ ንጉሡን ማናገር እንደሚገባ በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መነሻነት መንግስት ልዑኩ ወደ ሳውዲ እንዲሄድ መንግስት መወሰኑን ነው የተሰማው።

ልዑኩ በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ ዐረቢያ ዋና ከተማ በሪያድ ከተማ ይገኛል። የልዑኩ አባላት አስር ሲሆኑ የሚከተሉት ይገኙበታል።

1) አቶ አሕመድ ሺዴ
2) አምባሳደር ሪድዋን ሁሴን
3) ዶ/ር ጄይላን ከድር
4) ፕሮፌሰር አደም ካሚል
5) ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ
6) ቄስ ታጋይ ታደለ
7) አቶ መስፍን ገብሬ
8)አቶ ሀይደር አብደላ
9) አምባሳደር ሌንጮ ባቲ
የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት በተመለከተ ፕሮፌሰር አደም ካሚል በዐረብኛ ቋንቋ ለንጉሡ ገለፃ እንዲያደርጉ በልዑኩ ተመርጠዋል።

ምንጭ፦ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ

@tikvahethiopia
#Italy #Ethiopia

#ጣሊያን እና #ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

" በኦሮሚያ ክልል የጤና ስርዓትን ማጠናከር " የተሰኘው ይኸው ፕሮጀክት የጤና ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት፣ የእናቶችና ህፃናት አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እና ከኤችአይቪ/ኤድስ ጋር የተያያዙ ተግባራትን መደገፍ ያለመ ነው።

በተጨማሪ ፕሮጀክቱ የሎጂስቲክስ አስተዳደርን ማጠናከር ፣ የመረጃ ሥርዓቱን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (CBHI) ልማትንም ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#ችሎት

በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ዋና ዳሬክተር በነ አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው የነበሩ 22 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ30 ሺ ብር ዋስ አሲዘው ከእስር ተፈተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።

ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ዋስትና ከተፈቀደላቸው መካከል የብሔራዊ መረጃ ደህንኘት ም/ዳሬክተር የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን እና የተቋሙ የፀረሽብር ወንጀሎች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ይገኙበታል።

ፍ/ቤቱ የዓቃቢህግ የዋስትና መቃወሚያን ነጥቦችን ውድቅ በማድረግ በአንድ ዳኛ የድምጽ ተቋውሞ በሁለት ዳኞች አብላጫ ድምጽ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በተባለበት በተሻሻለው አንቀጽ 423 እና አንቀጽ 556 መሰረት ነው 30 ሺህ ብር ዋስ አሲዘው ከስር እንዲፈቱ የፈቀደው።

ፍርድ ቤቱ ዋስትና የተፈቀደላቸው ተከሳሾቹ ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ እንዲጣል አዟል።

የዛሬውን ችሎት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር የሆኑት ፖለቲከኛ ደጀኔ ጣፋ ታድመዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#Update

ተቋርጦ የቆየው የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አገልግሎቱ ከሰኞ ጥር 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን አገልግሎቱ ተገልጋዮች በትዕግስት ስለጠበቁት ምስጋና አቅርቧል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት እና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የonline አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት / ሸገር ኤፍ ኤም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (ዩኤኢ) ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘ ከኬንያ፣ #ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ወደ ሀገሯ የሚገቡ መንገደኞችን አገደች። እግዱ ከታህሳስ 16 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው። እግዱ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከመምጣታቸው 14 ቀናት በፊት በአራቱ ሀገራት የነበሩ ተጓዦችን እንዳይገቡ ማገድን የሚያካትት ነው። ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ…
#Update

ዩኤኢ ጥላው የነበረው እገዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ይነሳል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከ " ኦሚክሮን " ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ከተወሰኑ የአፍሪካ አገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይ እገዳ ጥላ እንደነበር ይታወሳል።

እገዳው ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኬንያ፣ ከናይጄሪያ እና ከሌሎች ስምንት የአፍሪካ አገራት ወደ ግዛቷ የሚጓዙ ተጓዦችን ያካትት እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን እገዳ ከተጠቀሱት አገራት የሚነሱትን ብቻ ሳይሆን ከጉዟቸው ቀደም ብለው ባሉት 14 ቀናት ውስጥ እዚያ የቆዩትንም ያካትት ነበረ።

አሁን ግን ለሳምንታት ተጥሎ የነበረው እገዳ ከሚቀጥለው #ቅዳሜ አንስቶ እንደሚነሳ በአገሪቱ የብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ቀውሶችንና አደጋዎችን የሚከታተለው ተቋም አስታውቋል።

ነገር ግን ከተለያዩ አፍሪካ አገራት ወደሀገሪቱ የሚጓዙ ሰዎች ከጉዟቸው 48 ሰዓታት በፊት ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን የሚያመለክት የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እና ከሚነሱበት አየር ማረፊያ ፈጣን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ መንገደኞች የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እንደደረሱ ሌላ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ይገባቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ሹመት

የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በቀድሞው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ያገለገሉትን ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል።

አዲሱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በዛሬው ዕለት በተቋሙ በመገኘት ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ከአመራሩ እና ከጠቅላላ ሠራተኞች ጋር በመተዋወቅ ስራቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት

@tikvahethiopia
#AtmafegedYilma

አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍሰገድ ይልማ ባደረባቸው ህመም በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በሚያዚያ 27/1929 ዓ.ም በቀድሞ አጠራር በአርሲ ጠቅላይ ግዛት ጢቾ ከተማ የተወለዱት ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍሰገድ በ1950 በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የፅህፈት ኮርስ መምህር ሆነው ስራ መጀመራቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍሰገድ ይልማ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና በአዲስ ዘመን ጋዜጦች ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ጋር በአዘጋጅነት የኢትዮጵያ ድምፅ ጋዜጣናና በመነን መፅሄት ላይም አገልግለዋል።

በደራሲነት የብደል ካሳ የተሰኘ ልብወለድ ፣ የአቤቶ ኢያሱ አነሳስ እና አወዳደቅ ፣ የህይወቴ ሚስጥር (የ50ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸው ማስታወሻ) መፅሀፍትን አሳትመዋል።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍሰገድ ይልማ በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ውስጥም አገልግለዋል።

ባለትዳር እና የ4 ወንዶች እና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

ስርዓተ ቀብራቸው ነገ 8 ሰዓት ሃያት በሚገኘው ሰአሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ፎቶ : የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር

@tikvahethiopia