TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ ሃይል በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለይ ቀርቦ ስልጣን መቆናጠጡን አሳውቋል። መግለጫውን በቴሌቪዥን ቀርበው የሰጡት ወጣት የጦሩ ቃል አቀባይ ናቸው። ጦሩ ፤ ሕገ መንግሥቱ መታገዱን ፣ በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ መታወጁን፣ ሁሉም የሀገሪቱ ድንበር መዘጋቱን ገልጿል። ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ በወታደሮቹ እንደታሰሩ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ…
#BurkinaFaso

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) የቡርኪናፋሶ ጦር በአስቸኳይ ያሰራቸውን የሀገሪቱን ፕሬዜዳንት እንዲፈታ በጥብቅ አሳስቧል።

በቡርኪናፋሶ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት የአፍሪካ ህብረት ፣ ECOWAS እና አሜሪካ አውግዘዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ፕሬዜዳንት ላይ የመፈንቅለ መንግስት መደረጉን ህብረቱ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

ECOWAS በተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስቱን በጥብቅ አውግዟል።

አሜሪካ በበኩሏ በቡርኪናፋሶ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባት ገልፃ በአስቸኳይ የሲቪል አስተዳደር ወደቦታው እንዲመለስ አሳስባለች።

ፕሬዜዳንት ሮች ካቦሬ በወታደሮች እንደታሰሩ ናቸው።

@tikvahethiopia