TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ባለንበት ማረሚያ ቤት በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት እና በማረሚያ ቤት በተለያየ ቦታ ላይ የታሰርነው ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር አስተያየት እንዲሰጥበት ታዘዘ። አቶ ተክላይ አብርሐ ፖስፖርቴንና መንጃ ፍቃዴን ለማሳደስ ለዩንቨርስቲ መታወቂያ ላላቸው ቤተሰቦቼ ውክልና እንድሰጥ ይፈቀድልኝ…
#Update

በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ለማውራት እና ማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ ይፈቀድልን ሲሉ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ መልስ ሰጥቷል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በ6 ተከሳሾች በተነሱ አቤቱታዎች ላይ መልስ እንዲሰጥ በያዘው ቀጠሮ ችሎቱ የተሰየመ ሲሆን አቤቱታ አቅርበው ከነበሩ ስድስት ተከሳሾች ውስጥ 11 ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዛብሔር ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታቸው ታልፏል።

በዛሬው ቀጠሮ 8ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና 19 ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በህመም ምክንያት በችሎት ያልቀረቡ ሲሆን 20ኛ ተከሳሽ አሰፉ ሊላይ 43 ኛ ተከሳሽ ተክላይ አብርሐ እና 44 ኛ ተከሳሽ ዘሚካኤል አንባዬ ግን ቀርበዋል።

የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በትግረኛ ቋንቋ ስልክ ለማውራት ስለተከለከልን እንዲፈቀድልት ይታዘዝልን ስትል ያቀረበችው አቤቱታን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ በስልክ ማውራትም የተከለከለው ለሀገሪቷ ደህንነት ክትትል ስለሚደረግ መሆኑን በጽሁፍ ምላሽ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የማስታወሻ ደብተር ተከልክለናል ሲሉ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ ከፍርድ ቤት ማህተም ካለበት ሰነድ ውጪ መያዝ የተከለከለው በደህንንነት መከታተያ ስርአት መሰረት መሆኑን ምላሽ ሰጥቷል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/UPDATE-01-13-3

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
#ተራዝሟል

የኢፌዲሪ የህዘብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ከታህሳስ 26/2014 - ጥር 6/2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ እስካሁን ዕጩ ኮሚሽነሮችን ለመጠቆም ዜጎች ያሳዩት ተነሳሽነትና እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ የሚያበረታታ ነው ብሏል።

ይሁንና ኮሚሽኑ ከሚኖረው ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት አንፃር ተጨማሪ ዕጩዎችን ህዝቡ እንዲጠቁም እንዲሁም የአገሪቱን ብዝሃነት ታሳቢ በማድረግና በተለያዩ ምክንያቶች መጠቆም ላልቻሉ ዜጎች ዕድሉን ለመስጠት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ እስከ ጥር 13/2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ለመጠቆም በም/ቤቱ ድህረ ገጽ
http://www.hopr.gov.et/web/guestpublicatons-acticles ወይም በ FB ገጽ http://www.facebook.com/hoprpariament ላይ የተቀመጠውን አድራሻ ይጠቀሙ፡፡

(የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት)

@tikvahethiopia
#ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፥ ካናዳ ሞንትሪያ በሚገኘው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩትን አቶ ጌታቸው መንግስቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

አቶ መንግስቱ ንጉሴን ደግሞ የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸው መንግስቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ረዘም ላለ ጊዜ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛውን በመተካት ነው።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#COOP #MICHU

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ምቹ የተባለ አዲስ ያለዋስትና ብድር ማግኘት የሚያስችል ዲጂታል ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል።

በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነው ምቹ ዲጂታል ዋስትና አልባ የብድር አገልግሎት በዋስትና ምክንያት የብድር አገልግሎት ማግኘት የማይችሉትን በዝቅተኛና መካከለኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን በእጅጉ ይጠቅማል ተብሎ ይታመናል።

ምቹ የብድር መጠየቂያ እና ማግኛ መተግበሪያ ሲሆን አጠቃቀሙም በሞባይል ስልክ ላይ በመጫን ነው፡፡

ብድር ጠያቂው በመተግበሪያው ላይ ጥያቄው ያቀርባል፣ ብድሩን ለማግኘት የሚጠየቁ መስፈርቶች ይሞላል መተግበሪያው በደቂቃዎች ውስጥ ውጤቱን ያሳውቃል ተብሏል፡፡

ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ የሥራ መስኮች ያለ ዋስትና ብድሩ የቀረበላቸው ሲሆን እንደ ስራው ዓይነትና የመመለሻ ጊዜ የብድር መጠኑ ከ30 ሺ ብር እስከ 150 ሺ ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ አውጥቶ ነበር። በዚህም መግለጫው ላይ TPLF ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኖ መቀጠሉን አስገንዝቧል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " እንደ ዓለም ጤና ድርጅት አይነት ለሁሉም ሰው በእኩል ቆመናል የሚሉ አለምአቀፍ ተቋማት ግን አሸባሪው ቡድን የአማራና አፋር ክልሎችን በወረረበት ወቅት ሀስፒታሎችንና የጤና ጣቢያዎችን ሲዘርፍና…
#ETHIOPIA

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ጉዳይ የግላቸውን አቋም እንዳያንጸባርቁ ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ትናንትና ረቡዕ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ላሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ አግዷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በራሱ ዜጎች ላይ ምግብ፣ መድሃኒት እና ሌሎች የህይወት አድን ድጋፎችን እንዳያገኙ እገዳ ጥሏል ሲሉም ነበር ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

ይህን ተከትሎ በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ፖለቲካዊ ውግንና አላቸው ያላቸው ዶ/ር ቴድሮስ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁና ገለልተኛ እንዲሆኑ ጠይቋል፡፡

የተሰጣቸውን ዓለም አቀፋዊ ሚና ከመወጣት ይልቅ ከፖለቲካዊ እና ግለሰባዊ ፍላጎት የመነጨ ውግንናቸውን እያንጸባረቁ ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ የተመድ ኤጀንሲዎች ስራም በዚሁ ምክንያት እየተስተጓጎለ ይገኛል ብሏል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያን ከተመለከቱ የትኞቹም ጉዳዮች ራሳቸውን እንዲያርቁም ነው በተመድ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ጽ/ቤት የጠየቀው፡፡

ኢትዮጵያ በጦርነቱ ምክንያት የጤና ተቋማት ሲወድሙ ምንም አላለም በሚል የዓለም ጤና ድርጅትን መውቀሷ ይታወሳል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AFCON2021 ⚽️ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇨🇲 ካሜሮን 🗓 ዛሬ ጥር 5 / 2014 ዓ/ም ⌚️ ማታ 1:00 🏟️ ፖል ቢያ ስታድየም 📍 ካሜሩን - ያዉንዴ 🖥 ሱፐር ስፖርት / ስካይ ስፖርት እና ኢቲቪ መዝናኛ ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ! #HanaG. More : @tikvahethsport
#AFCON2021

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው የመጀመሪያ ጎሏን አስቆጠረች።

ኢትዮጵያ ከካሜሮን ጋር ፍልሚያዋን እያደረገች ትገኛለች።

ጨዋታው ከተጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች የተቆጠረ ሲሆን በዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት በዘንድሮ ውድድር የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች።

ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ቀጥሏል።

በስፖርት ገፃችን ተከታተሉ : @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#AFCON2021 ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው የመጀመሪያ ጎሏን አስቆጠረች። ኢትዮጵያ ከካሜሮን ጋር ፍልሚያዋን እያደረገች ትገኛለች። ጨዋታው ከተጀመረ ጥቂት ደቂቃዎች የተቆጠረ ሲሆን በዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት በዘንድሮ ውድድር የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች። ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ቀጥሏል። በስፖርት ገፃችን ተከታተሉ : @tikvahethsport
#AFCON2021

#ኢትዮጵያ እና #ካሜሮን መካከል እየተደረገ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ፍልሚያ የመጀመሪያ አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በመጀመሪያ አጋማሽ አስደሳችና እጅግ ማራኪ የሚባል እንቅስቃሴ አሳይታለች።

በዘንድሮ ውድድርም የመጀመሪያ ጎል አስቆጥራለች።

ድል ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

More : @tikvahethsport
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር መክሯል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ለአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ለጉባኤው እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ለጉባኤው ስኬት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ነገሮች ከማዘጋጀት ባለፈ የተሳታፊዎች ጤንነት መጠበቅን ለማረጋገጥ የኮቮድ-19 ምርመራ እና ክትባት መስጫ የጤና ማእከላት በመንግስት መቋቋማቸውን ነው የገለፀው። 

የአፍሪካ ሀገራት ለኢትዮጵያ ላሳዩት አጋርነትም ምስጋናውን አቅርቧል። 

በዛሬው የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ በተደረገው ገለፃ ላይ ስለተነሱት ጉዳዮችም ለየሀገሮቻቸው መንግስታት እንዲያሳውቁም አሳስቧል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AFCON2021

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 2ኛ ጨዋታ በካሜሮን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።

More : @tikvahethsport
#ALERT🚨

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 10,073
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 2,131
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 19
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 835
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 433

ዛሬ እና ትላንት በድምሩ የ43 የሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopia
" ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ጨዋታ አቁሙ !! " - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፦

" ... እሱ ውጭ ሆኖ ወይም ደግሞ ጥግ ይዞ ወይም ህወሓት አዲስ አበባ ይጋባል ብሎ ሻንጣ ሲያዘጋጅ የቆየ መከላከያን ሊገመግም ይፈልጋል።

በዚህ ወጣ፣ በዚህ ወረደ፣ ይሄን አላደረገም፣ እንዲህ ነው እንዲያ ነው እያለ ይገመግማል።

ለምሳሌ መከላከያ ለምን ጠላት ወደ አማራ ክልል እንዲሰፋ አደረገ ይልሃል ፤ ጦርነት እግር ኳስ ይመስለዋል። ሁለቱ ቡድኖች የሆነ ስታዲየም ተሰርቶ እዛ ውስጥ ተገብቶ በግራ እና ቀኝ በሜትር ተሰምሮ እና ተለክቶ እዛ ውስጥ የምትጋጠም አድርጎ የሚያስብ አለ።

ጦርነት የእግር ኳስ ግጥሚያ አይደለም። አጥር የለውም። ልክ እንደእግር ኳስ ስታዲየም አጥር የለውም። ከአጥሩ ለምን ወጣህ የሚል ህግ የለውም። ሲመችህ ጠላትን ትገፋለህ 400 ኪ/ሜ ታስለቅቀዋለህ፤ ሳይመችህ ደግሞ እስኪመችህ ትከላከላለህ።

ጦርነትን እንደ አዲስ አበባ ስታዲየም ተከልሎለት የምትገጥም የሚደረግ ግጥሚያ አድርጎ የሚረዳ ሰው ነገሮችን የሚረዳበት መንገድ በጣም ደካማ ነው ወይም ሆን ብሎ ነው ለማበጣበጥ ሊሆን ይችላል። ሆን ብሎ ለማበጣበጥ ደግሞ ግንባር ቀደም ተዋናይ TPLF ነው፤ ወገን መስሎ፣ አማራ መስሎ፣ ኦሮሞ መስሎ ሰራዊቱን ለመገምገም ይሞክራል።

ሰራዊት ለመገምገም ቢያንስ 40 ዓመት ሰራዊት ውስጥ ማገልገል አለብህ። ጦርነት ለመገምገም ጦርነት ማወቅ አለብህ፤ ሳይንስ ጥበብ ማወቅ አለብህ። ወጥተህ ወርደህ የሰራዊትን ስነልቦና ማወቅ አለብህ።

ብድግ ብሎ የማንም እንትን ... Balloon ሲፈነዳ የሚደነግጥ ሰው ሰራዊት መገምገም የለበትም። ሰራዊት የመጨረሻ ምሽግ ነው። የሉአላዊነት የመጨረሻ ምሽግ ነው። ሰራዊት ብሄር የለውም። ሰራዊት ኢትዮጵያዊነት ነው ያለው።

ሰራዊት ውስጥ ገብተህ በፈተፈትክ ቁጥር ፣ ለማጋጨት በሰራህ ቁጥር ፣ በብሄር በከፋፈልከው ቁጥር ፣ በጓደኛ አንዱን ከፍ አድርገህ አንዱን ዝቅ ባደረከው ቁጥር ሀገር ላይ ነው አደጋ የምትፈጥረው። በነገራችን ላይ የኛ ሰራዊት ለእንደዚህ አይነት ነገር ፣ ለአሉባልተኛ ቦታ የለውም፤ ቦታ አይሰጥም። የተገነባባት መሰረቱ ግንቡ ጠንካራ ነው። ለዛ ምቹ አይደለንም እኛ። ለጎጥ፣ ለብሄርተኝነት ምቹ አይደለንም።

እኛ ብሄር የለንም ብለን ቃል ገብተናል፣ ለኢትዮጵያዊነት ነው የምንሞት ያለነው። ለኢትዮጵያዊነት ነው ሰው 48 ሰዓት ሳይበላ ሳይጠጣ የሚዋጋ ያለው። ለሀገሩ ነው። ኢትዮጵያን ከመበታተን ለማዳን ነው። እኛ እንደኢትዮጵያ ነው የምናስበው።

ለመተቸትም እውቀት ያስፈልጋል። ያለእውቀት የሚተች ወይ ጠላት ነው ሆን ብሎ ለመከፋፈል፣ ለማዳከም፣ ሞራሉን ለማድቀቅ ፣ አመራሩን ለመከፋፈል ጠላት የሚሰራው ነው በአብዛኛው እሱ ነው ብዬ ገምታለሁ። ሌላው ይሄን በማድረግ ትርፍ የሚገኝ እየመሰለው ሊሆን ይችላል ወይ ሌላው ሲያራግብ ጠላት ሲያራግብ የእሱ ወገን ያራገበ መስሎት እያሟሟቀ ይሆናል።

ተውት መከላከያን ! መከላከያ ለእያንዳንዳችን ዋስትና ነው። ስለዚህ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ጨዋታ አቁሙ፤ sensitive የሆነ ቦታ እየመረጥክ የምትጫወተው ጨዋታ የጠላት ጨዋታ ነው። ተው !! ተው !! አሁን በኃላ በማያገባው ገብቶ የመከላከያን ህልውና የሚፈታተን ነገር ላይ የተሳተፈ ከሆነ እራሳችንን ለመከላከል እንገደዳለን "

@tikvahethiopia
#MIAM

በመላው አለም በኬሚካል ምርት አንቱታን ካተርፉ አገራት አለም አቀፍ የጥራት ደረጃቸዉን ያሟሉ የኬሚካል ምርቶችን ለአገር ውስጥ ገበያ እናቀርባለን።

Tel: 📞 +251911546231
📞 + 251930115522

📩 ፡ millionamakele@gmail.com

JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL
https://publielectoral.lat/MIAMPOLYMERS
#JustinTrudeau #OlusegunObasanjo

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ልዩ መልዕከተኛው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ እና በሁሉም አካላት መካከል ውይይት እንዲፈጠር ለማበረታታት የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።

ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በአፍሪካ መሪነት ለሚደረገው የሽምግልና ጥረቶች ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ እና ካናዳ በዚህ ረገድ የአፍሪካ ህብረትን ስራ ለመደገፍ ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች ያለ ምንም እንቅፋት ሰብዓዊ ዕርዳታ በማድረስ ሂደት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሰላማዊ ዜጎችን መጠበቅ፣ ህይወት ማዳንና የሰብአዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለተፈናቃይ ወገኖች 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አደረገች።

ቤተክርስቲያኗ ህወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ነው 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የፊኖ ዱቄት ድጋፍ ያደረገችው።

የስዊድን እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የጅማ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ሌሎች አባቶች ደባርቅ ከተማ በሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች፤ ወደፊትም የተጎዱ ወገኖችን መደገፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።

ፎቶ ፦ EOTC

@tikvahethiopia