TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሁሉ በሕግ እና በሕግ ብቻ ይሁን " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

እናት ፓርቲ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካለችበት ውጥንቅጡ የወጣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዞ ወጥታ፣ ችግሯ በዘላቂነት ተፈቶ፣ ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር እንድትሆን ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

ነገር ግን ሕጋዊ ሂደትን ባልጠበቀ እና በማናለብኝነት ውሳኔዎችን መወሰንና ተግባራዊ ማድረግ የገዥው ፓርቲ አሠራር ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየሆነ ነው ሲል ተችቷል።

የትኛውም አካል የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ሰው ከሕግ በታች መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው ያለው እናት ፓርቲ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብም ይሁን ድርጅት ህጋዊ ሂደት ሳይጠብቅ “ክስ ማቋረጥ” ማሰናበት በሕግ ተቋማት ሥራ ላይ ያለውን ጣልቃገብነት ከማሳየቱም ባሻገር የፈላጭ ቆራጭነት ማሳያ ነው ብሏል።

በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ፣ የአካል ጉዳት ያደረሱ፣ ንብረት ያወደሙ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ እና አፋር ሕዝቦችን ያፈናቀሉ እና ለትግራይ ሕዝብ ለአሥርት ዓመታት በሰቆቃ ሕይወት መኖር ተጠያቂ የሆኑ፣ እናቶችና ሕጻናት እንዲደፈሩ ያደረጉ አመራሮች ላይ ኢሕጋዊ በሆነ ሁኔታ ታሕሳሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የፓርቲውን አምባገነንነት የሚያሳይ ነው ሲል ፓርቲው ተችቷል።

ከብዙ ታሳሪዎች መካከል “ በእድሜ የገፉ ስለሆነ ” በሚል ምክንያት ሀገር ለሕልውና እያደረገች ያለውን ጦርነት ዓላማ የሳተ፣ የሕግ አሠራር ሂደትን የጣሰ፣ በግለሰቦችና ገዢው ፓርቲ ፍላጎት ብቻ ዜጎች የሚታሠሩበት እና የሚፈቱበት መሆኑን ማሳያ ነው ብሎታል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

በአሁኑ ሰዓት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የአውደ ውጊያ ውሎ የሜዳሊያ ሽልማት እና አዲሱ የመከለከያ ጠቅላይ መምሪያ ህንጻ ምረቃ እየተከናወነ ይገኛል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሰልፍ እና የአየር ትርዒትም ቀርቧል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#Update

ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
2. ጀነራል አበባው ታደሰ
3. ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሌ/ጀ አለምሸት ደግፌ

የአደዋ ድል ጀግና ከፍተኛ ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦

1. ጀነራል ጌታቸው ጉዲና
2. ሌ/ጀነራል በላይ ስዩም
3. ሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ
4. ሌ/ጀነራል መሰለ መሠረት
5. ሌ/ጀነራል ሹማ አብደታ
6. ሌ/ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል
7. ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ
8. ሌ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የመዘከሪያና የመከላከያ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት የማስመረቅ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

#PMOEthiopia #FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ?

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው።

አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ ጦርነር አቁሙ የሚል ስናቆም ተዋጉ የሚል አጓጉል ብልጣብልጥነት የሚያጠቃው እና እንብዛም ጆሯችንን የማንገልጥለት ቡድን ነው።

ሁለተኛው ቡድን በዜናው ድንገተኝነት የደናገጠ፣ በነበረው ተጋድሎ እና ሁኔታ ጊዜውን ፣ ገንዘቡን፣ ህይወቱን ለመስጠት የወሰነ ከያለበት ሀገር እና ክልል ተሞ ከሀገር እና ከህዝብ ጋር የዘመተ ይህን እኩይ ጠላት አምርሮ የሚጠላና ከዚህ ጠላት ጋር የሚደረግ ማንኛውም ንግግር ኢትዮጵያን ይጎዳል ብሎ የሚያምን ቅን ተቆጪ ነው። የዚህን ቅን ተቆጪ ኃይል መንግስት ሙሉ በሙሉ ይረዳል ያደምጣል ለማስገንዘብም ጥረት ያደርጋል።

እነዚህ ቅን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵየውያን በውስጥም በውጭም የሚገኙ የአንዳንዶችን ከኛ ይቅር ማለት አምርረው የጠሉና የደናገጡ ወንድም እና እህቶቻችን እንዲገነዘቡልን የምንፈልገው ይህ ጉዳይ እኛም መጀመሪያ ስንሰማው ያስደነገጠ መሆኑን ነው።

ነገር ግን ደጋግመን ስናመነዥገው ግራ ቀኙን ስንፈትሽ ለኢትዮጵያ የሚበጅ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም የሚያግዝ፣ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ጠላቶች የሚቀንሥ ፣ በአውደ ውጊያ ያገኘነውን ድል በሰላሙ መድረክ እንድንደግም የሚያደርግ የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን የማያረጋግጥ በመሆኑ እየመረረን የዋጥነው እውነት ነውና እናተም ለሀገራችሁ ዘላቂ ድል ስትሉ ፣ ለሀገራችሁ ክብር እና አሸናፊነት ስትሉ ደጋግማችሁ በማሰብ ይህን ውሳኔ እንድትቀበሉ በትህትና ጠይቃችኃለሁ።

ውሳኔውን ለምን ? ለምትሉ ይህ ውሳኔ የተወሰደው ኢትዮጵያን በጠንካራ አለት ላይ ለማኖር ነው። ጠላቶቿን ለመቀነስ ነው። ጉልበት ለመሰብሰብ ነው። ያልገባውና የሚከተል ማህበረስብ ካለ አይኑን ገልጦ ማየት እና ከጥፋት ጎዳና እንዲመለስ ለማድረግ ነው። ሌላም ባርካታ ምክንያቶች አሉት።

ነገር ግን ትላንት ክስ አቋርጠን ከእስር ቤት እንዲፈቱ ያደርገናቸው ግለሰቦች ሁሉም በሚባል ደረጃ የመንግስት ስልጣን ይዘው በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተሳተፉ ፣ በቀጥታ የሚወስኑ፤ በቀጥታ የሚያዙ አይደሉም።

አንዳንዶች በታሪካቸው ምክንያት አግዝፈን የምናያቸው ቢሆንም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከሁሉም የውሳኔ ሰጭነት መድረክ በቀጥታ የማይሳተፉ ኃይሎች ናቸው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን እና ጀግንነታችን ሽማግሌዎች በእስር ቤት እንዲሞቱ የሚፈልግ ፣ የሚፈቅድ አይደለምና ጀግኖች ስለሆንን አዛውንቶች ሲቻል ወደገዳም ፣ አልያም ወደቤታቸው እንጂ በእስር ቤት እንዳይቆዩ ወስነናል።

ይህ ውሳኔ ዛሬ የሚመረንም ቢሆን እንኳን ውሎ ሲያደር ልጆቻችንን የሚያኮራ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያፀና መሆኑን ቅንጣት አንጠራጠርም። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
#ተጨማሪ

ከእስር ስለተፈቱት ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን ተናገሩ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... ክስ የተቋረጠላችሁ ወገኖች ስላሸነፍን መበቀል እየቻልን ይቅር ማለትን ስለመረጥን ክስ አቋርጠን እናተን ሳይሆን ከእናተ ጀርባ ያለውን ህዝብ አክብረን የወሰን መሆናችንን አውቃችሁ ይህን እድል ሳታበላሹ እንድትጠቀሙበት ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ።

ክስ ማቋረጥ ማለት ምህርተ መስጠት ማለት አይደለም። ክስ የተቋረጠለት ሰው በአግባቡ መጠቀም ካልቻለ መልሶ የክስ መዝገቡን መምዘዝ የሚቻል ስለሆነ።

በዚህ ጉዳይ ያዘኑ፣ የተቆጡ፣ የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች እንዲገነዘቡ የምፈልገው የወሰድነው መድሃኒት ማስታገሻ አይደለም የወሰድነው መድሃኒት ፈዋሽ በመሆኑ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ፤ ይጎረብጣል ያማል ! ለማዳን ብቻ ሳይሆን በጎንም የመጎርበጥ ባህሪ አለው።

ለጊዜው የሚያስታግስ ሳይሆን ለልጆቻችንም የድልና የአሸናፊነት መንፈስ የሚያላብስ ስለሆነ እንደኛ ደጋግማችሁ ስታስቡት ጠቀሜታው ጎልቶ ይታያችኃል እናም ደግማችሁ ለማሰብ ልባችሁና አእምሯችሁ እንዲከፈት ዋናው አላማ የምትወዷትን ሀገር ኢትዮጵያን አንድ አድርገን ለማፅናት ካለን ፍላጎት አንፃር ብቻ የመነጨ መሆኑን እንድትገነዘቡ ቢያንስ ቢያንስ ጉቦ በልተን እንዳለቀቅናቸው እንድታስቡ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ። "

@tikvahethiopia
#TPLF

ጠቅላይ ሚኒስትሩ TPLFን በተመለከተ ምንድነው ያሉት ?

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... አሁን ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀን የማንገባበት በርካታ ምክንያቶች ያሉን ቢሆንም አንገባም ብለን ከቆምን በኃላ ነገሩን በተለየ መንገድ ለማየት ጥረት እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት አሁንም TPLF አላረፈም። አሁንም TPLF በግራ በቀኝ ሊነካካን ይፈልጋል። 

ለ7ኛው ስህተት የሚጓዘው TPLF በፍፁም ድል ማግኘት የማይችል እንኳን ቢሆን በወጣቶች የትግራይ ልጆች ላይ በህይወት የመቀጠፍ የመቁሰል አደጋ የሚያስከትል ስለሆነ 7ኛው ስህተቱ መስመር ስቶ ሳይሄድ መማር የሚችልበት እድል መፍጠር የራሱ (TPLF) ቢሆንም እንኳ እንደባላንጣ አትንኩን ፤ እረፉ ለማለት እወዳለሁ።

የነካካችሁን እንደሆነ በተለመደው መንገድ የከፋ ቅጣት ይደርስባችኃልና።

ትላንትና እንኳን ክስ አቋርጠን እስረኞች ይውጡ ስንል የTPLF ጀሌዎች ከፊሉ የአማራ አካውንት ከፊሉ የኦሮሞ አካውንት አስመስሎ በመክፈት እኛን ለማባላት ሳይተኙ አድረዋል። አማራ መስለው ፣ኦሮሞ መስለው ብዙ ጥረት አድርገዋል። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-01-09
#Amhara

ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ከተፈናቀሉት ዜጎች ውስጥ፣ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደ ቀደመ መኖሪያቸው መመለሳቸቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ በአሁኑ ወቅት ህወሓት በሰሜን ጎንደር አልፎ አልፎ በሚያደርገው ትንኮሳ ምክንያት በቅርቡ እንደሚመለሱ ከሚጠበቁትና በደባርቅ መጠለያ ውስጥ ከሚገኙት 200 ሺህ ተፈናቃዮች ውጪ፣ በሌሎች አካባቢዎች በመጠለያ የነበሩት ተፈናቃዮች ሙሉ በሙሉ ተመልሰዋል ብለዋል።

በጦርነቱ ከተፈናቀሉት በተጨማሪ ቀደም ሲል በአጣዬ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የተፈናቀሉ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቤንሻንጉል ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በሚንቀሳቀሰው ኃይል የተፈናቀሉ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ ጥቃት ደርሶባቻው ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 900 ሺ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ህወሓት በከፈተው ጦርንት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱትን ጨምሮ ተወረው በነበሩ አካባቢዎች በደረሰው ዝርፊያ፣ ውድመትና የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 11.4 ሚሊዮን መድረሱን አክለዋል፡፡

ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ዜጎች ወደአምራችነት እስኪገቡና መቋቋም እስኪችሉ ለመመገብ በየወሩ 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ምግብ የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን መቅረብ የቻለው 426 ሺ ኩንታል ምግብ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ክልሉ የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራ በማከናወን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ባለሙያዎችና ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማት መሪዎች የተካተቱበትና 6 ቡድን የያዘ የአጥኚዎች ስብስብ በአጠቃላይ በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት እያጠና ነው።

@tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ተጠናቋል።

35 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የመጀመሪያው 14 ኪሎ ሜትር ከቢሻን ጉራቻ በመነሳት ወደ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሄድ ነው።

መንገዱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የወሰደው 592 ሚሊየን 84 ሺህ ብር ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፥ የመንገዱን ግንባታ አለም አቀፉ የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ አከናውኖታል።

በማማከርና በቁጥጥር ስራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን መሳተፉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

@tikvahethiopia
#Timket

የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናቶች ቀርተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት የሚከበርበት የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ሥራ በመፋጠን ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ወቅታዊ የግንባታ ይዘቱ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

Photo Credit : EOTCTV

@tikvahethiopia