TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DireDawa

በድሬዳዋ በእርሻ ማሳ ውስጥ አደገኛ እፅ ተከለው የተገኙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አደገኛው የካናቢስ እጽ በእርሻ ማሳቻው ላይ ተክለው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

እጹ ሊያዝ የቻለው በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ገንደ- ገበሬ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ተጠርጣሪ ግለሰብ በእርሻ ማሳ ውስጥ የተተከሉትን አደገኛ እፅ በመኮትኮት ላይ እንዳለ መሆኑ ተገልጿል።

ፖሊስ ወደ ቦታው የደረሰው በአካባቢው ላይ ሌላ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ሲሆን የአካባቢው ሚሊሻዎች ግለሰቡ እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ተመልክተው ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሰረት ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ከተከሉት በርካታ እጽ ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከተማው ውስጥ ይሄንኑ አደገኛ እጽ የመሸጥ ስራ ከምትሰራ ሌላ ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋር ግንኙነት በማድረግ ግለሰቧ አደገኛ የካናቢስ እጽ ስትሸጥ ተገኝታ ምርመራ ተጣርቶ ውሳኔ ማግኘቷን ፖሊስ ገልጿል።

በድሬዳዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛ የካናቢስ እጽ ዝውውርን ለመግታት ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ ያሳወቀው ፖሊስ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ የሚገኘውን አደገኛ እጽ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
" የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል ነው " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል በመሆኑ “ህጋዊ የምንዛሬ አማራጮችን ብቻ መጠቀም ይገባል” አሉ።

አቶ አቤ ፥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚመነዘር የውጭ አገር ገንዘብ በአመዛኙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሚሰሩ ኃይሎች እንደሚውል ነው ብለዋል።

ይህም ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ የማዳከም ዘመቻ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ድርጊቱ በሁለት መልኩ አገርን እንደሚጎዳ አብራርተዋል፡፡

በአንድ በኩል ጦርነት ከፍተው አገር እየወጉ የሚገኙ የውስጥ ጠላቶችን አቅም ለማጎልበት የሚውል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር እንዲሸሽ በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

በዚህም የውጭ አገር ገንዘብን በጥቁር ገበያ መመንዘር ለጥቂት የገንዘብ ጭማሪ ሲባል አገርን የሚጎዱ ኃይሎችን መተባበር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ገንዘብን በህጋዊ መንገድ ብቻ በመመንዘር የኢትዮጵያን ህልውና ለመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና መወጣት አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም የአገራቸውን ህልውና ለመጠበቅ ዋጋ እየከፈሉ ባሉበት በዚህን ወቅት የውጭ አገር ገንዘብ በህጋዊ መንገድ መላክ ከአገር ወዳድ ዜጎች የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከሚላከው የውጭ አገር ገንዘብ መካከል በህጋዊ መንገድ የሚመነዘረው ከ30 በመቶ እንደማይበልጥ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#DrDanielBekele

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከሰሞኑን ከአል ዓይን የአማርኛው አገልግሎት ጋር ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

ዶ/ር ዳንኤል በዚሁ ቃለ ምልልስ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተጠይቀው ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

በቃለ ምልልሱ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ?

- በቅርቡ ስለተሸለሙት የጀርመን አፍሪካ ሽልማት።

- ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ሪፖርት ሲያደርጋቸው የነበሩ የመብት ጥሰቶችን ተከትሎ የመጣ ተጠያቂነት ይኖር ስለመሆኑ ?

- ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ከተመድ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ጋር በጋራ ስለተሰራው ምርመራ። የምርመራውን ውጤት የህወሃት ቡድን ያልተቀበለበት ምክንያት።

- በምርመራዎቹ እና በሌሎች የኢሰመኮ ስራዎች ላይ ከመንግስት አካላት ጫና ይደረግባችሁ ነበር ? ወይ ተብለው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

- ህወሃት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለመንግስት ያደላሉ እያለ ስለሚያቀርበው ቅሬታ ምላሽ ሰጥተዋል።

- የጣምራ ምርመራ በአፋርና አማራ ክልሎች ይቀጥል እንደሆነ ተጠይቀው መልሰዋል።

- ምርመራ አድረጋለሁ ብሎ የነበረው የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከምን ደርሶ ይሆን ?

- በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ስለሚገለፀው በተለይ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እስር ጉዳይ አስተያየት ሰጥተዋል።

- ኢትዮጵያ አሁን ስላለችበት ሁኔታ ምልከታቸውን አጋርተዋል።

ያንብቡ : https://am.al-ain.com/article/ehrc-chief-says-there-is-no-interference-from-government-in-its-work

@tikvahethiopia
#Kenya

አልሸባብ በፈፀመው ጥቃት 2 የኬንያ ፖሊስ አባላት ተገደሉ።

አልሸባብ በማንዴራ ባደረሰው የአድፍጣ ጥቃት ቢያንስ 2 የኬንያ ፖሊስ አባላት ሲገደሉ አስር የሚደርሱ መቁሰላቸው ተሰምቷል።

በሌላ መረጃ ፦ በዚህ ሳምንት የኬንያ መርማሪዎች በህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላት የተባለች አንዲት ሴት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተሰምቷል።

የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ይፋ ባደረገው መረጃ በቁጥጥር ስር የዋለችው የ22 ዓመት እድሜ ያላት ሴት ስትሆን ስሟ በደህንነት ምክንያት ወዲያው አልተገለፀም።

በቁጥጥር ስር የዋለች ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ በስተ ምዕራብ 300 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ናንዲ ካውንቲ በሶጎር፣ ቲንዴሬት ውስጥ ነው።

በተጨማሪም ኬንያ በዚህ ሳምንት የአልሸባብን ስጋት ለመከላከል በሶማሊያ አቅራቢያ በሚገኘው በማንዴራ ቡላሃዋ ድንበር ላይ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎችን ማስፈሯን ጋሬዎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሊ ክልል መንግሥት ለ12ተኛ ጊዜ ፣ በጀረር ዞን ብርቆት ወረዳ ያለው ሻለቃ ከድር የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸው ልዩ ኃይል አባላት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተገኙበት አስመርቋል።

ፎቶ፦ SRTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በዛሬው ዕለት ደብረ ሲና፣ ጣርማ በር፣ የለን፣ ተሬ፣ ራሳ፣ ኩማሜ እና ሌሎች በሸዋ ሮቢት ዙሪያ ያሉት የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሀል ሜዳ፣ ሞላሌ፣ ወገሬ እንዲሁም ሌሎች በአካባቢያቸው የሚገኙ ሳተላይት ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Update

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት / የጥምር የፀጥታ ኃይሉ / ከህወሓት ነፃ በማድረግ መቆጣጡሩን የገለፃቸው አካባቢዎች ዝርዝር ፦

- ጋሸና
- ላሊበላ
- አርቢት
- አቀት
- ዳቦ
- ጃማ ደጎሎ
- ወረኢሉ
- ገነቴ
- ፍንጮፍቱ
- አቀስታ
- መዘዞ
- ሞላሌ
- ሸዋሮቢት
- ራሳና
- ለምለም አምባ
- ጀውሐ
- ሰንበቴ
- አጣየ
- ካራ ቆሬ
- ኮን
- ዳውንት
- ልጓማ
- መሐል ሜዳ
- ጨፋ ሮቢት
- ሐርቡ
- መኮይ
- ቀውዝባ
- ጭላ
- አጅባር
- ተንታ
- ዶባ
- ማጀቴ
- ጭረቲ
- ከሚሴ
- ርቄ
- ወለዲ
- አልቡኮ
- የቃሉ ወረዳ አብዛኛውን ክፍል መቆጣጠሩን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት /ጥምር የፀጥታ ኃይሉ / ተቆጣጥሮ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች የመለሰባቸው፦
- ካሳጊታ
- ቡርቃ
- ዋኢማ
- ጭፍራ
- ጪፍቱ
- ድሬሮቃ
- አለሌ ሱሉላ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Update

ከህወሓት ነፃ በሆኑ የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ላሊበላ፣ ጋሸና ፣ ዋድላ ፣ ላስታ ፣ ዳውንት እና ሌሎች በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ ወረዳዎች የህብረተሰቡን ህይወት ወደ ቀደመው ለመመለስ ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።

ፎቶ : ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር ፦ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ። ዝግ የሚሆኑት ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ነው። #ምክንያት ፦ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው። ት/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት…
#ትምህርት_ሚኒስቴር

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነገ ህዳር 27 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 3 ድረስ ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ ያድረጋሉ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በማይናማር ወታደሩ ስልጣን ተቆጣጠረ። በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰምቷል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የኖቤል ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተለቅመው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል። በሚየንማር በወታደሩ እና በሲቪሊያን አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት…
#Update

ኦንግ ሳን ሱ ኪ የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው።

ከስልጣናቸው በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የተነሱት የማይናማር መሪ ኦንግ ሳን ሱ ኪ የ4 ዓመት እስር ተፈረደባቸው።

የማይንማር ፍርድ ቤት ከስልጣን የተነሱት የሲቪል መሪ አውንግ ሳን ሱ ኪ በወታደራዊ ኃይሉ ላይ ተቃውሞ በማነሳሳት/ግጭት በመቀስቀስ እና የኮቪድ ህጎችን በመጣስ የ4 አመታት እስር ፈርዶባቸዋል።

የማይናማር ጁንታ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ በሰጡት ቃል የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚ ኦንግ ሳን ሱ ቺ በሁለቱ ክሶች የሁለት ሁለት አመት እስር ይቀጣሉ ብለዋል።

ኦንግ ሳን ሱ ኪ 11 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዊን ሚይንትም በተመሳሳይ ክስ የ4 ዓመታት እስር እንደተፈረደባቸው የማይናማር ጁንታ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia