TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ላሊበላ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መውደሙ ተገለፀ።

የታሪካዊቷ እና የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ላሊበላ ከተማ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጿል።

የጋይንት ጋሸና ግንባር ኮማንድ ፖስት የህወሓት ቡድን የኤርፖርቱን መሰረተ ልማት እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ማውደሙን አሳውቋል።

የላሊበላ ከተማ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር መዋሏ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በህወሓት ተይዘው የነበሩ ተጨማሪ ቦታዎች ነፃ ማውጣቱ ተገልጿል። የፀጥታ ኃይሎች ጥምረቱ ፦ - የመሐል ሜዳ፣ - ጨፋ ሮቢት፣ - ሐርቡና መኮይ ከተሞችና አካባቢውን ነጻ እንዳወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል። የኢትዮጵየ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " ጥምር የጸጥታ ኃይሎቹ በጥልቀት ገብተው…
#Update

ተጨማሪ ከተሞች ነፃ መውጣታቸው ተገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፥ " በጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በ "ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" ባካሄደው ኦፐሬሽን ተጨማሪ ከተሞችን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ አውጥቷል ፤ በጥልቀት በመግባትም የአሸባሪውን ጀሌዎች የመማረክና የመደምሰስ ተግባሩን ቀጥሏል " ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት በጋሸና ግንባር ቀውዝባና ጭላ ከተሞችና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በወረኢሉ ግንባር በተደረገው ኦፐሬሽን አጅባር፣ ተንታ እና ዶባ ከተሞችና አካባቢያቸው ነጻ ወጥተዋል።

በከሚሴ ግንባር ማጀቴን ፣ ጭረቲን ፣ ከሚሴን ፣ ርቄን ፣ ወለዲን ፣ አልቡኮ ከተሞችን እና የቃሉ ወረዳን አብዛኛውን ክፍል በመቆጣጠር፣ ጥምር ጦሩ ወደ ኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " ዛሬ እና ትናንት በተደረጉት ከፍተኛ የማጥቃት ኦፐሬሽኖች አብዛኛው የአሸባሪው ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲበተን ተደርጓል " ያለ ሲሆን አስቀድሞ ነጻ በወጡት በምሥራቅ፣ በምዕራብና በመሐል ግንባር በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች መንግሥታዊ አስተዳደር ተመልሶ በመደራጀት ሥራውን ጀምሯል ብሏል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,125 የላብራቶሪ ምርመራ 144 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 214 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
" አደጋው ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል የሃሰት እና የሽብር መረጃ ለማህበረሰቡ የማዛመት ስራ እየተሰራ ነው " - አንበሳ የከተማ አውቶቡስ

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ማምሻውን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅቱ አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልፅ የሃሰት መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ድርጅቱ ፥ " መረጃው ከእውነት የራቀ እና ከሁለት አመታት በፊት የተፈጠረውን አደጋ ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል የሃሰት እና የሽብር መረጃ ለማህበረሰቡ የማዛመት ስራ እየተሰራ ነው፤ ማህበረሰቡም ይህን እንዲያውቅ " ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱ የገጠማትን ፈተና የተዛባ መረጃ በመንዛት ግጭቱን ለማባባስና የሃሰት ወሬዎችን በማናፈስ ሁከት ለመፍጠር የሚጥሩ በርካታ ግለሰቦችም ሆነ ሚዲያዎች ስላሉ ሁሉም ሰው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራትም ሆነ በመረጃዎቹ ከመረበሽ መቆጠብ አለበት ብሏል።

አላስፈላጊ ሽብር ለመፍጠር የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አደጋው ዛሬ የተፈጠረ በማስመሰል የሃሰት እና የሽብር መረጃ ለማህበረሰቡ የማዛመት ስራ እየተሰራ ነው " - አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ማምሻውን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የድርጅቱ አውቶብስ ላይ አደጋ መድረሱንና የሰው ህይወት ማለፉን የሚገልፅ የሃሰት መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ አሳውቋል። ድርጅቱ ፥ " መረጃው ከእውነት የራቀ እና ከሁለት አመታት…
" ዜናው የውሸት ነው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፥ "ዛሬ ማምሻውን 11:30 ሰዓት አካባቢ 60 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከፒያስ ወደ ፈረንሣይ ሌጋሲዮን ይጓዝ የነበረ 12 ቁጥር አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ፍሬን ተበጥሶ ድልድይ ውስጥ በመገልበጡ የተነሳ ሾፌሩን ጨምሮ የ39 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል " ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሳዘን የተለቀቀ የውሸት መረጃ ነው ብሏል።

ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ተብሎ በምጠራዉ አከባቢ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ኮድ 3-09978 አ.ማ ቅጥቅጥ ድጋፍ ሰጭ ተሸከርካሪ ፍሬን እምቢ ብሎት ከግኡዝ ነገር ጋር ተጋጭቶ በአሽከርካሪው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶ ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

የአ/አ ፖሊስ ከዚህ ውጭ ምንም አይነት ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ ሀሰተኛ ወሬ ሆነ ብለው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምስል በማቀነባበር ተሰራጭቷል ብሏል።

ፖሊስ የተሳሳተ መረጃ የሚለቁትን አካላት ተከታትሎ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ማመን እንደሌለበት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ከስራ ገበታቸው ውጭ የሆኑ መምህራን ...

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ቢያንስ ከ45 ሺ በላይ መምህራን ከሥራ ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አስታወቀ፡፡

ማህበሩ ይህ ያስታወቀው ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ነው።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፥ በጦርነቱ ሳቢያ ያለ ሥራ የተቀመጡና በችግር ውስጥ የሚገኙ የመምህራን ብዛት ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ጦርነቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በነበሩበት አካባቢ መቀጠል ባለመቻላቸው በርካታ መምህራን ከትግራይ ፣ አማራ ክልል ፣ አፋር ክልሎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተዘዋውረው እንዲሠሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ያነሱት ዶ/ር ዮሃንስ ማኅበሩ ጥያቄውን ተቀብሎ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ  ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ችግሩ ከማኅበሩ አልፎ ከአገር አቅም በላይ ስለሆነ፣ በርካታ ፍላጎቶች ቢቀርቡም፣ ማኅበሩ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር የመፍትሔ ሐሳቦችን ከማፈላለግ ውጪ የተለየ ነገር ማድረግ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠው የመምህራን ደመወዝ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ተመልሶ እንዲከፈላቸው፣ ከየክልሎቹ የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር መነጋገራቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በመላው አገሪቱ ከ600 ሺህ በላይ አባላት እንዳሉት ይነገራል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ በእርሻ ማሳ ውስጥ አደገኛ እፅ ተከለው የተገኙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ አደገኛው የካናቢስ እጽ በእርሻ ማሳቻው ላይ ተክለው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳውቋል።

እጹ ሊያዝ የቻለው በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ገንደ- ገበሬ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ተጠርጣሪ ግለሰብ በእርሻ ማሳ ውስጥ የተተከሉትን አደገኛ እፅ በመኮትኮት ላይ እንዳለ መሆኑ ተገልጿል።

ፖሊስ ወደ ቦታው የደረሰው በአካባቢው ላይ ሌላ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞ ሲሆን የአካባቢው ሚሊሻዎች ግለሰቡ እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ተመልክተው ለፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሰረት ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ከተከሉት በርካታ እጽ ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከተማው ውስጥ ይሄንኑ አደገኛ እጽ የመሸጥ ስራ ከምትሰራ ሌላ ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋር ግንኙነት በማድረግ ግለሰቧ አደገኛ የካናቢስ እጽ ስትሸጥ ተገኝታ ምርመራ ተጣርቶ ውሳኔ ማግኘቷን ፖሊስ ገልጿል።

በድሬዳዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛ የካናቢስ እጽ ዝውውርን ለመግታት ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑ ያሳወቀው ፖሊስ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል እየጎዳ የሚገኘውን አደገኛ እጽ ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
" የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል ነው " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ኢትዮጵያን የማዳከም ዘመቻ አካል በመሆኑ “ህጋዊ የምንዛሬ አማራጮችን ብቻ መጠቀም ይገባል” አሉ።

አቶ አቤ ፥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚመነዘር የውጭ አገር ገንዘብ በአመዛኙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሚሰሩ ኃይሎች እንደሚውል ነው ብለዋል።

ይህም ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ የማዳከም ዘመቻ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ድርጊቱ በሁለት መልኩ አገርን እንደሚጎዳ አብራርተዋል፡፡

በአንድ በኩል ጦርነት ከፍተው አገር እየወጉ የሚገኙ የውስጥ ጠላቶችን አቅም ለማጎልበት የሚውል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር እንዲሸሽ በማድረግ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

በዚህም የውጭ አገር ገንዘብን በጥቁር ገበያ መመንዘር ለጥቂት የገንዘብ ጭማሪ ሲባል አገርን የሚጎዱ ኃይሎችን መተባበር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ገንዘብን በህጋዊ መንገድ ብቻ በመመንዘር የኢትዮጵያን ህልውና ለመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና መወጣት አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት በመቆም የአገራቸውን ህልውና ለመጠበቅ ዋጋ እየከፈሉ ባሉበት በዚህን ወቅት የውጭ አገር ገንዘብ በህጋዊ መንገድ መላክ ከአገር ወዳድ ዜጎች የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ወደ አገር ውስጥ ከሚላከው የውጭ አገር ገንዘብ መካከል በህጋዊ መንገድ የሚመነዘረው ከ30 በመቶ እንደማይበልጥ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#DrDanielBekele

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከሰሞኑን ከአል ዓይን የአማርኛው አገልግሎት ጋር ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

ዶ/ር ዳንኤል በዚሁ ቃለ ምልልስ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተጠይቀው ዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።

በቃለ ምልልሱ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ?

- በቅርቡ ስለተሸለሙት የጀርመን አፍሪካ ሽልማት።

- ኢሰመኮ ከዚህ ቀደም ሪፖርት ሲያደርጋቸው የነበሩ የመብት ጥሰቶችን ተከትሎ የመጣ ተጠያቂነት ይኖር ስለመሆኑ ?

- ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ከተመድ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ጋር በጋራ ስለተሰራው ምርመራ። የምርመራውን ውጤት የህወሃት ቡድን ያልተቀበለበት ምክንያት።

- በምርመራዎቹ እና በሌሎች የኢሰመኮ ስራዎች ላይ ከመንግስት አካላት ጫና ይደረግባችሁ ነበር ? ወይ ተብለው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

- ህወሃት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለመንግስት ያደላሉ እያለ ስለሚያቀርበው ቅሬታ ምላሽ ሰጥተዋል።

- የጣምራ ምርመራ በአፋርና አማራ ክልሎች ይቀጥል እንደሆነ ተጠይቀው መልሰዋል።

- ምርመራ አድረጋለሁ ብሎ የነበረው የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከምን ደርሶ ይሆን ?

- በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ስለሚገለፀው በተለይ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እስር ጉዳይ አስተያየት ሰጥተዋል።

- ኢትዮጵያ አሁን ስላለችበት ሁኔታ ምልከታቸውን አጋርተዋል።

ያንብቡ : https://am.al-ain.com/article/ehrc-chief-says-there-is-no-interference-from-government-in-its-work

@tikvahethiopia
#Kenya

አልሸባብ በፈፀመው ጥቃት 2 የኬንያ ፖሊስ አባላት ተገደሉ።

አልሸባብ በማንዴራ ባደረሰው የአድፍጣ ጥቃት ቢያንስ 2 የኬንያ ፖሊስ አባላት ሲገደሉ አስር የሚደርሱ መቁሰላቸው ተሰምቷል።

በሌላ መረጃ ፦ በዚህ ሳምንት የኬንያ መርማሪዎች በህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላት የተባለች አንዲት ሴት በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተሰምቷል።

የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ይፋ ባደረገው መረጃ በቁጥጥር ስር የዋለችው የ22 ዓመት እድሜ ያላት ሴት ስትሆን ስሟ በደህንነት ምክንያት ወዲያው አልተገለፀም።

በቁጥጥር ስር የዋለች ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ በስተ ምዕራብ 300 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ናንዲ ካውንቲ በሶጎር፣ ቲንዴሬት ውስጥ ነው።

በተጨማሪም ኬንያ በዚህ ሳምንት የአልሸባብን ስጋት ለመከላከል በሶማሊያ አቅራቢያ በሚገኘው በማንዴራ ቡላሃዋ ድንበር ላይ ተጨማሪ የጸጥታ ሃይሎችን ማስፈሯን ጋሬዎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሊ ክልል መንግሥት ለ12ተኛ ጊዜ ፣ በጀረር ዞን ብርቆት ወረዳ ያለው ሻለቃ ከድር የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸው ልዩ ኃይል አባላት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተገኙበት አስመርቋል።

ፎቶ፦ SRTV

@tikvahethiopia