TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ! በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገንዘብ በመክፈል ሁከት የፈጠሩትን አካላት መንግስት እያጣራሁ ነው ብሏል። የመከላከያ ሰራዊት ወንጀለኞችን የመያዝ እና ህዝቡን የማረጋጋት ስራ እየሰራ ነው።

*በአሶሳ በተፈጠረው ሁከት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 49 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
ጉንችሬ⬆️በጉንችሬ ሊደረገ የታቀደው የድጋፍ ሰልፍ እውቅና አግኝቷል። ሁሉም እንዲሳተፍም አስተባባሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ህዝብ ክብሩ ክብራችን፥ ስኬቱ ስኬታችን፥ ችግሩ ችግራችን መከራው መከራችን ነው ብለን የምናምን ወገኖቻችሁ መኖራችንን አትርሱ። የሰፊው ሕዝብ ክብር በጥቂት ሆዳሞ በስሙ በሚነግዱ ሆዳሞች አይፈርስም አብረናችሁ ነን።

ክብር ለሀውዜን ሰማዕታት!

ሕዝብና ሆዳም ፖለቲከኛን የለየ

ኑ እንደመር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወጣቶ! ነገ ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚደረጉት የድጋፍ ሰልፎች በሰላም እንዲጠናቀቁ ሁሉም ወጣት ለአንድነቱ እና ሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል። የቀብ ጅቦቹ መዋያቸው አይታወቅም እና በትዕግስት እና በጥንቃቄ ሰልፎቹ ሊደረጉ ይገባል። ማንኛውንም አጠራጣሪ ነገር ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሀይላት በማሳወቅ የደጋፍ ሰልፎቹ በድማቅ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ማድረግ ይገዋል።

ከዶክተር አብይ አህመድ ጋር ወደፊት!

ከአለም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦምብ ተያዘ የሚባለው ውሸት ነው! "በባህርዳር ከተማ በመጭው እሑድ የሚደረገውን የድጋፍ ሰልፍ ለማወክ ቦምብ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች
በቁጥጥር ስር ዋሉ” እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ከዕውነት የራቀ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት አንድ
የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ ከ10 የሚበልጡ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በተቋቋመው ቡድን ምርመራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ”እስካሁንም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ምንም አይነት የመገናኛ ሬዲዮም ሆነ ቦምብ የለም” ሲሉ ኮማንደር ዋለልኝ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮማንደር ዋለልኝ⬆️"እስካሁንም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ምንም አይነት የመገናኛ ሬዲዮም ሆነ ቦምብ የለም።”

#BahirDar #ባህር_ዳር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀይቅ⬆️ለነገ ቅደሜ የዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ በደቡብ ወሎ ሀይቅ ከተማ ወጣቶች ህዝቡን ለሰልፍ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ።
©አሚር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍኖተ ሰላም⬆️ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ለእሁዱ የዶክተር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

©Chacha
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ - ሰሚት⬆️

"ሰሚት ጋር ተጋጭተው ነው። ፀግሽ ይሄ ምን ይባላል ቆይ ስንት ሰው ወርዶ በእግሩ እንደሄደ ብታይ በአንድ ሰው ጥፋት።"

ፎቶ ©Beki
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ⬆️በወልዲያ ከተማ ሊደረግ የተጠየቀው የድጋፍ ሰልፍ ፍቃድ አግኝቷል። ሁሉም እንዲሳተፍ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪውን ያቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Defend አድርጋለች⬆️

ወ/ሮ እህታፈራዉ የጥናት ወረቀቷን Defend አድርጋለች።

ከፈነዳዉ ቦምብ ይልቅ የፈነዳዉ ፅናት ይበልጣል!

እህታችን ወ/ሮ እህታፈራዉ ዉብሸት ሰኔ 16/2010 በመስቀል አደባባይ በተደረገዉ የመደመር፣የፍቅርና የምስጋና ቀን በመስቀል አደባባይ ተገኝታ ነበር።

ይሁን እንጂ በተፈፀመዉ የሽብር ጥቃት እግሯ ላይ የአጥንት ስብራት ደርሶባት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ የህክምና አገልግሎት እያገኘች ነዉ።

ወ/ሮ እህታፈራዉ በleadership & management በሁለተኛ ዲግሪ የዘንድሮ ተመራቂ ናት።

ከደረሰባት ጉዳት በመነሳት የጥናቷ defense እንዲራዘምላት ብትጠየቅም "አይሆንም የደረሰብኝ ጉዳት ያጠነክረኛል እንጂ ከዕቅዴማ ወደኃላ አልልም” በማለት ከነጉዳቷ ረዕቡ ዕለት የጥናቷ ፅሁፍ defend አድርጋለች። በጥናት ወረቀት ዉጤቷም #Excellent አስመዝግባለች።

ከፈነዳዉ ቦምብ ይልቅ የፈነዳዉ ፅናት ይበልጣል!

ምንጭ፦ አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቴዲ አፍሮ...⬆️

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው አርማዬ
ልጄ ብለሽ ጥሪኝ አለሁ ኢትዮጵያዬ
ስቀሉት አርማዬን እንደማርያም ልጅ
ስቀሉት አርማዬን አውጡና እንጨት ላይ
ፍቅር ከሰው ሁሉ ከፍ በሎ እንዲታይ #Ethiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia