TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ የሚገኘዉ “ደብሊዉ ኤ” የዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ ግንባታው በ2006 ዓ.ም የተጀመረው የምግብ ዘይት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ 85 በመቶ እንደደረሰ ታውቋል፡፡ ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በቀን ከ130 እስከ 150 ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል እንደፈጠረ ነው የተገለጸው፡፡ የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንግዳወርቅ መኮንን #ለአብመድ እንደገለፁት ፋብሪካው ሥራ ሲጀምርም አራት ዓይነት የምግብ ዘይት ለማምረት ነው የታቀደው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#COVID19ETHIOPIA

በደሴ ከተማ 30 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል!

በደሴ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዘ ግለሰብ መገኘቱን ተከትሎ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 30 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ #ለአብመድ አሳውቋል።

የጅቡቲ የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ የናሙና ምርመራ ተደርጎለት ግንቦት 15/2012 ዓ.ም የኮሮና ቫይረስ እንዳለበት ተረጋግጧል፡፡

አሽከርካሪው አማራ ክልል ከገባ በኋላ መጋቢት 10/2012 ዓ.ም ጋሼና ከተማ ጭነት አራግፎ፣ ወልድያ አድሮ በማግስቱ ወደ #ደሴ ከተማ አስተዳደር መሄዱ ታውቋል፡፡

ወደ ከተማ አስተዳደሩ በገባ በማግስቱ የጤና ባለሙያዎች ጥቆማ ደርሷቸው ወደ ቤቱ ቢሄዱም ስላላገኙት ለሁለት ቀናት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ግንቦት 11/9/2012 ዓ.ም ወደ ከተማው የገባው ግለሰቡ በ13/2012 ማለዳ በግል ሆስፒታል ለህክምና በሄደበት ተገኝቶ ነበር ወደ ለይቶ ማቆያ የገባው፡፡

በዕለቱ አሽከርካሪውን ጨምሮ ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አምስት (5) የሆስፒታሉ ሰራተኞች ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል https://telegra.ph/AMMA-05-25

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ትናንት ሌሊት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት የንፁኃን ሕይወት አለፈ! (አብመድ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት 10፡00 ገደማ ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ የንፁኃን ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የበንገዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ደምለው በንገዝ ለአብመድ ተከታዩን ብለዋል…
#FDREDefenseForce

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ላይ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ የደረሰው ማለዳ 12:00 እንደሆነ በመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ለአብመድ አሳውቋል።

የምዕራብ ዕዝ 22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ስለጉዳዩ #ለአብመድ (AMMA) ተከታዩን ብለዋል ፦

- ዳንጉር ወረዳ በንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊት 10:ዐዐ ጥቃት መፈጸሙን መረጃ ያገኘነው ማለዳ 12:00 ነው።

- ሠራዊቱ አካባቢውን በመቆጣጠር ጥቃት አድራሾችን የማሰስ እና እርምጃ የመውሰድ ተግባር ፈፅሟል።

- ሽፍቶች በደፈጣ ውጊያ በማድረግ ከሠራዊቱ ለመሰወር ጥረት አድርገዋል ፤ ሠራዊቱ ስምንት (8) ሽፍቶች ላይ እርምጃ ወስዷል።

- የመከላከያ ሠራዊቱ በአካባቢው ተደራጅተው ንጹሐን ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሽፍቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የተሰጠውን ሕዝባዊ አደራ በቁርጠኝነት ይወጣል።

PHOTO : FDRE Defense Force (FILE)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia