TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጉዳት አድራሿ ጦጣ በአ/አ⬇️

ከአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ አምልጣ ወጥታ በአካባቢው ሰዎች ላይ ጉዳት ያደረሰችዋ ጦጣ እስከ አሁን አለመያዟ እንዳሳሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተማሪ ነቢዩ ኢሳኢያስ በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ አንድ ነዋሪ ነው፡፡ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ በአቅራቢያው ወዳለ ሱቅ በማምራት ላይ ሳለ ጦጣዋ ከኋላው ዘላ እግሩን ነክሳው ጉዳት አድርሳበት አምልጣለች፡፡

በግል ስራ እንደሚተዳደር ወጣት ድልነሳው ይገዙ እንደተናገረው ደግሞ ወደ ስራ ለመሄድ ፊቱ በመታጠብ ላይ ሳለ ይሕችው ጦጣ ከኋላው በኩል እግሩን ነክሳ #ከፍተኛ የሚባል ጉዳት አድርሳበታለች፡፡ በጦጣዋ ከፍተኛ ጉዳት በማስተናገዱ መንቀሳቀስ እንደማይችል የገልጿል። ወጣት ድልነሳው በመሃል ከተማ ከሚገኝ ፓርክ እንስሳት በዚህ መልኩ ማምለጥ መቻላቸው #አሳሳቢ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የልጆችን ጩኸት ሰምቶ ወደ ውጪ በወጣበት ጊዜ ከጦጣዋ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጠው ህጻን አቤኔዘር አጥናፉ ራሱን ለማዳን የግቢውን በር ቢዘጋም በአጥር ዘልላ ታፋውን እንደነከሰቸው ነው ተናግሯል፡፡

የወላጅ አቤኔዘር እናት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ተክሌ ለኢዜአ እንዳሉት ፓርኩ የእንስሳት ማቆያ እንደመሆኑ መጠን በቂ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባ ነበር፡፡ የጦጣዋ አለመያዝ #አሁንም ድረስ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

የስድስት ዓመት ህጻን ልጃቸው በጦጣዋ ጉዳት እንደረሰበት የተናገሩት ወይዘሮ አጃይባ ዋባ በበኩላቸው ልጃቸውን ለማሳከም 3 ሺህ 500 ብር ማውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላዋ የአካባቢው ነዋሪ ወይዘሪት ሶፊያ አወል እንዳለችው ሰዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በላይ የጦጣዋ ጤንነት አሳስቧታል፡፡

ተቋሙ መሰል እንስሳት አምልጠው ከዚህም የባሰ ጉዳት እንዳያደርሱ የጥበቃ ስራውን ሊያጠናክር እንደሚገባም ጠቁማለች፡፡

የአንበሳ ግቢ መዝናኛ ፓርክ አስተባባሪ አቶ ይርጋለም አያሌው ጦጣዋ የማደሪያዋን ኮርኔስ ገንጥላ ማምለጧን ገልጸው ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት ቢደረግም አለመሳካቱን አምነዋል፡፡

አሁንም ዳርት /ማደንዘዣ/ በመጠቀም ጦጣዋን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያብራሩት አስተባባሪው ካልተሳካ ሌሎች አማራጮችን እንደሚጠቀሙ አረጋግጠዋል፡፡

ፓርኩ በሚቀርብለት ደረሰኝ መሰረት ተጎጂዎች ያወጡትን ወጪ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ኦሮሚያ‼️

በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ #አድማሱ_ዳምጠው በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ
ሰጥተዋል።

አቶ አድማሱ በመግለጫቸውም፥ የክልሉ መንግስት ህዝቡን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እየሰራ ያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ #አሳሳቢ መሆኑን እና በአፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ያለበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ይገነዘባል ያሉት አቶ አድማሱ፥ በዚህ ላይም እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ አድማሱ አክለውም፥ የክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል አቋም እንደሌለው እና ማንኛውንም አካል በመማረክ የማስተዳደር ፍላጎት እንደሌለውም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት በኦሮሞ ስም ተደራጅተው ከሚንሰቃቀሱ አካላት ጋር ሰለማዊ በሆነ መንገድ በመወያየት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አድማሱ፥ ወደ ፊትም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመከባበር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ፥ የክልሉ መንግስትም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመመለስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚወያይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን እየመጣ ያለውን ለውጥ ጠብቀው በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡም አቶ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ🔝

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በቡድን በታጠቁ ኃይሎች ሰዎች በጅምላ #እየተገደሉ ነው ሲሉ ገለፁ። ከአንድ ቤተሰብ እስከ ስምንት ሰው የተገደሉበት መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች ችግሩ #አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አስተዳደር ስለ ጉዳዮ ምንም አለመስማቱን ቢገልፅም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት መረጃው እንዳለው እና እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ...

"ፀግሽ እንዴት ነው አዲስ አበባ ውስጥ የመብራት፣ የውሀ እና የሌቦች የዘረፋ ጉዳይ በጣም #አሳሳቢ ሆኗል ምን ተሻለን!? እኔ ከባንቢስ ሱፐር ማርኬት ከፍ ብሎ በሚገኝው የኡራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው ያለሁት ሱቆችን ሰብሮ መዝረፍ እንደ ደቡብ አፍሪካ ሀገር #ኖርማል ሆኗል ተደጋጋሚ ብዙ ሱቆች #ተዘርፈዋል። ጥበቃ ቢኖራቸውም ጥበቆቹን እስኪበቃቸው ደብድበው ሚፈልጉትን ይዘው ይሄዳሉ በጣም ሚገርምህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከንጋቱ 11:00 ሰአት በኋላ ይመጣሉ ማንንም አይፈሩም የተደራጁ ናቸው ይህው ዛሬ ደግሞ በግምት 11:30 መጥተው ነው ሰዉንና ጥበቆችን በድንጋይ አባረው ዘርፈው የሄዱት ህዝቡ በህግ አስከባሪው አካላት ተስፋ ቆርጧል ለማመልከት እንኳን ጣቢያ አይሄድም ምክንያቱም እዛም ተባባሪ ስላላቸው ሀንግ ደግሞ ተወው ገና በጊዜ ይጀመራል ሰዉ ነፍሴን ካተረፍኩ የፈለጉትን ይውሰዱ ከማለት ውጪ አማራጭ የለውም እባክህ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ ስራ እንዲሰራ ለሚመለከተው አካል አሳውቅልን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ #የመምህራን ፍልሰት #አሳሳቢ ሆኗል፤ ባለፉት 2 ወራት ብቻ እስከ 10 የሚደርሱ ሲኒየር መምህራን ዩኒቨርሲቲውን ለቀዋል ሲሉ አንድ ስማቸውን እንዲገለፅ ያልፈለጉ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባል ተናግረዋል። ለመምህራኑ ዩኒቨርሲቲውን መልቀቅ እንደ ምክንያትነት የሚነሳውም የአካባቢው ፀጥታ ሁኔታ/TEPI/፣ የመምህራን አያያዝ እና የአስተዳደር ችግር ነው። ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሲነፃፀር ወደኃላ ቀርቷል ጉዳዩ ትኩረት ይፈልጋል ሲሉ መልዕክቱን ያደረሱት የቤተሰባችን አባል ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዳማ ከተማ 1 በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ተገኘ!

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሃይል ገለጸ፡፡

ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው 24 ሰዎች ተለይተዋልም ነው የተባለው። ግብረ ሃይሉ በህብረተሰቡና በተቋማት የሚታየው ቸልተኝነት አሁንም #አሳሳቢ ነው ብሏል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከለይቶ ማቆያ የሚያመልጡ የኮቪድ-19 ተጠርጣሪዎች!

በጋምቤላ ክልል በኮሮና የተጠረጠሩ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ እየጠፉ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኡጁሉ እንደተናገሩት በለይቶ ማቆያነት ከሚያገለግለው ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜያት ያመለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ደርሷል።

ሰዎቹን ፈልጎ ማግኘቱ አስቸጋሪ እንደሆነ የጠቀሱት ሃላፊው ከመካከላቸው እስካሁን የተገኘ አለመኖሩን አስረድተዋል።

የክልሉ ነዋሪዎች በሽታው የለም መመርመሪያውም በትክክል አይመረምርም የሚሉና ሌሎች የተሳሳቱ አመለካከቶችን እንደሚያንጸባርቁ የገለጹት ዶ/ር ኡጁሉ ህዝቡ ስለ በሽታው ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን #አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

አብዛኛዎቹ የኮሮና ታማሚዎች ምልክት ስለማያሳዩ ብዙዎች በሽታው የለም የሚል እምነት እንዳደረባቸው ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

በጋምቤላ ክልል እስካሁን በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር 180 የደረሰ ሲሆን 54 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የዶቼ ቨለ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...በኢትዮጵያ በቀን 30 በዓመት 11 ሺ እናቶች ከወሊድ ጋር በተገናኘ ይሞታሉ" - ጤና ሚንስቴር

ኢትዮጵያ በእናቶች ሞት ቅነሳ መልካም ውጤት ብታስመዘግብም አሁንም በዓመት 11 ሺህ እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የእናቶች ጤና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዘነበ አካለ ፥ "በኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በፊት 30 ሺ እናቶች በወሊድ ጋር በተያያዘ ይሞቱ ነበር ፤ በተሰራው ሥራ የእናቶችን ሞት 72 በመቶ መቀነስ ተችሏል" ብለዋል።

የተገኘውን ውጤት ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ዕውቅና የሰጡት ቢሆንም አሁንም የእናቶች ሞት #አሳሳቢ እንደሆነ ነው የገለፁት።

በወሊድ ምክንያት በቀን 30 በዓመት ደግሞ 11 ሺህ እናቶች ሕይወታቸውን እንደሚነጠቁ የገለፁት ቡድን መሪው ፣ የትኛውም አደገኛ የሆነ የወረርሽኝ በሽታ የእናቶችን ሞት ያህል ሕይወት አይነጥቅም ብለዋል።

እናቶች የሚሞቱበት ምክንያት ሲታይ 50 በመቶ ያህሉ ያለ ጤና ተቋም በቤት ውስጥ በመውለዳቸው፤ የተሟላ የመንገድ መሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጤና ድርጅት / ጤና ተቋም ለመሄድ ረጅም ርቀት ስለሚጓዙ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እናቶች በእርግዝና ወቅት፣ በወሊድ ጊዜና ከወሊድ በኋላ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወታቸው ያልፋል ያሉት ቡድን መሪው፤ ከሚሞቱት እናቶች 50 በመቶ የሚሆኑት በደም መፍሰስ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል። ~ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የድሬዳዋ አስተዳደር ለነዋሪዎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በድሬዳዋ ዴልታ በመባል የሚታወቀውና በዓለማችን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የኮቪድ ዝርያ እንዲሁም ደንጊ ፣ ቺክንጉኒያ እና ወባ #አሳሳቢ በሚባል ደረጃ በመከሰቱ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የከተማው አስተዳደር አስጠንቅቋል።

ከዚህ ተደራራቢ ችግር ሊወጣ የሚቻለው ማህበረሰቡ አሁን ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ እንደ አንድ በመሆን እርምጃዎች ሲወስድ ብቻ ነው ብሏል አስተዳደሩ።

ማህበረሰቡ ሊወስድ ይገባቸዋል ያላቸው እርምጃዎችም ፦

1ኛ. ሁሉም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀቀስ የአፍን እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ፣ አካላዊ እርቀትን መጠበቅና የእጆችን ንፅህና መጠበቅ።

2ኛ. ዘወትር አካባቢን ማጽዳት፣ ንፅህናዉን በሚገባ መጠበቅና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማፍሰስ።

3ኛ. ከትንኝ ንድፊያ የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል በጸረ ትንኝ መድሃኒት የተነከሩ አጎበሮችን መጠቀም የሚሉት ናቸው።

@tikvahethiopia
#ደራ_ወረዳ #ትኩረት

በደራ ወረዳ ያለው የፀጥታ ችግር አሁንም #አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ፣ የሰዎች ህይወት እያለፈ ፣ ንብረትም እየወደመ መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል የልጆቻቸው እናት የሆነች ሚስታቸውን ከ " ኦነግ ሸኔ " ታጣቂዎች ጋር በመወገን ገድለዋል ብለዋል።

አንድ ቃላቸውን ለ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' የሰጡ የሟች የቅርብ ቤተሰብ ነኝ ያሉ ግለሰብ ፤ " በደራ ጁሩ የተባለ አካባቢ አንድ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል የፓሊስ አባል ከኦነግ ሸኔ ጋር በመወገን የአራት ልጆቹን እናትና የ5 ወር ነፍሰጡር ሚስቱን ገድሏል " ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው የሟች የቅርብ ቤተሰብ ይህ ግድያ በጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ፤ " ጁሩ " የተባለ አካባቢ ላይ እንደትፈጸመ አስረድተው፣ " የሟቿን እናት ጨምሮ ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል። እኛም ልባችን ተሰብሮ አለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛው የዓይን እማኝ #ጥቅምት_9 በገለጹት መሠረት፣ በደራ ወረዳ " ቆሮ ግንደ በርበሬ " ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ጦር አካባቢውን እና መንደሩን ካቃጠለ 2 ሴቶችን እና አንድ ወንድ ገድሏል ሲሉ ከሰዋል።

እንደ ነዋሪው ገለፃ ን በታጣቂ ቡድኑ የተገደሉት ፀጋ እምነት፣ ጌታው አቤቱ እና ለግዜው ስሟን ያላወቁት ሴት ናቸው።

እኚሁ እማኝ ፤ " በመንግሥት ይሁንታ #የደራ_ህዝብ ከፍተኛ የዘር የፍጅት እየደረሰበት ነው " ብለዋል።

ይኸው ዘገባ እየተዘጋጀበት እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ታጣቂ ቡድኑ ያለበትን ሁኔታ ሲያስሩዱም፣ " አሁንም በተለያዩ ቀበሌዎች እንደቀጠለ ነው። መንግሥት ምንም እርምጃ አልወሰደም። አድማሱን እያሰፋ ይገኛል " ነው ያሉት።

እኚሁን ምንጭ ጨምሮ ሌሎች የኦሮሚያ እና የአማራ ተወላጅ የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣  አሙማ ገንዶ፣ ኢሉ ጎደ ጨፌ ፣ ሀርቡ ደሶ ፣ ዴኙ ወቤንሶ ፣ ጁሩ ዳዳ፣ ሀቼ ኩሳዬ፣ ካራ፣ ጎዲማ ሶስት ዋርካ፣ ጊሊ ወዲሳ፣  ቆሮ ግንደ በርበሬ፣ በዮ ኖኖ፣ ደንቢ ብርጄ፣ ባቡ ድሬ፣ ወሬ ገበሮ፣ መንቃታ፣ የተባሉና ላሎችም ቀበሌዎች እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) በታጣቂ ቡድኑ ስር ናቸው ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ቃላቸውን በስልክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ፣ መከላከያ በአካባቢው እንዳለ፣ እንደ አጠቃላይ ግን ነዋሪው የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደሆነ አስረድተው ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀዋል።

ሌላኛው ነዋሪ በበኩላቸው ፤ " ፋኖ ታጣቂዎችም አልፎ አልፎ ጥቃት እያደረሱ  ነው። በመካከል እየተጎዳ ያለው ንጹሐኑ ነው። መንግሥት እርምጃ ቢወስድ ምን አለ ? " ሲሉ ተይቀው ተጨማሪ ሀሳብ ለመስጠት ተቆጥበዋል።

የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ባለፉት ሳምንታት በርካታ ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ እንደታገቱ ፣ ከእገታ ለመለቀቅም ከ500 እስከ አንድ ሚሊዮን ብር እየተጠየቀባቸው እንደነበር፣ በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ፣ በርካታ ቤቶች እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት እንደተቃጠሉ መግለፃቸው ይታወሳል።

የኦሮሚያ ተወላጆችም ፤ " የፋኖ ታጣቂዎች በርካታ ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎችን ገድለዋል " ማለታቸው አይዘነጋም።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ በሚጠራው የታጣቂ ቡድን ታገቱ የተባሉ ሰዎች ከምን እንደደረሱ፣ የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ፣ የቤት ቃጠሎ ጥቃቱ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ ፣ " ከ500 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር የከፈሉ ተለቀዋል፣ ያልከፈሉትን ገድሏል " ብለዋል ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ታማኝ ምንጭ።

ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚሰነዝሩትን ግድያ፣ ቃጠሎ፣ እገታ እንዳላቆሙ የሟቾችን ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደተገደሉ አስረድተው፣ ይህን ልጓም ያጣ ጥቃት መንግሥት ቸል ብሎታል የዓለም መንግሥታት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይወቁልን ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ደረሰ እና አልቆምመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአቶ ሺበሺን በስልክና በአጭር ጽሑፍ እንዲያብራሩ ጥያቄ ቢያቀርብም #ምላሽ_ለመስጠት_ፈቃደኛ_አልሆኑም

አቶ ሺበሺ ከዚህ በፊት ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ችግሩን ለመቅረፍ የጸጥታ ኃይል እጥረት እንዳለ አስረድተው ነበር።

በተጨማሪ ከዞኑ አስተዳደር፣ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ የተደረገው ተመሳሳይ ሙከራ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በደራ ስላለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ያነጋገረ ሲሆን " ክትትል ተጀምሯል ግን ገና አላለቀም " የሚል አጭር ምላሽ አግኝቷል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia