TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 45 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 45 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,517 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,166 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 749 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrEngSeleshiBekele የቀድሞ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተሹመዋል። @tikvahethiopia
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ጣልያን፤ ሮም ይገኛሉ።

በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሮም ከኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ም/ሚ/ር ና የልማት ትብብር ሚ/ር Mrs Maria Sereni ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች እና በህዳሴ ግድብ ግንባታና ድርድር ላይ ያተኮረ ሲሆን ቀጣይ የጋራ የትብብር ጉዳዮች ላይም ውይይት መካሄዱን ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፥ ነገ "Encounters with Africa 2021” የኢነርጂ ኮንፈርስ ከአፍሪካ አገሮች፣ ጣሊያንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በG20 የጣሊያን ፕሬዚዳንትነት ወቅት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ዛሬ ለተወሰነ ጊዜ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ እንደነበር አስታወቀ።

የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ ወጥቶ በነበረበት ሰዐትም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተላለፈ ነው የተባለ ሀሠተኛ መልዕክት ተለጥፎ እንደነበር አየር መንገዱ አስታወቋል።

አየር መንገዱ ጨምሮ እንደገለጸው ዋና ስራ አስፈጻሚው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይሁን በሌላ መንገድ ያስተላለፉት ምንም አይነት መልዕክት አልነበረም።

ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ በነበረው የፌስቡክ ገጽም ተለጥፎ የነበረው መልዕክት የዋና ስራ አስፈጻሚውንም ሆነ አየር መንገዱን እንደማይወክል አስታውቋል።

ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የነበረውን የፌስቡክ ገጽ በአሁኑ ሰዐት በአየር መንገዱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ተገልጿል።

Credit : https://ethiopiacheck.org/

@tikvahethiopia
#Tigray #Amhara #Afar

ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ መናሩን UNOCHA ገለጸ።

UNOCHA ባወጣው ሪፖርት በክልሉ "የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ እጥረት ፈታኝ ሆኗል" ብሏል።

በተጨማሪ የUNOCHA ሪፖርት በአይደር ሆስፒታል ውስጥ አንድ ሕጻንን ጨምሮ 18 ሰዎች ሄሞዲያሊሲስ ካቲተር በማጣታቸው መሞታቸውን ይገልፃል።

"መሠረታዊ የምግብ እና ሌሎችም አስፈላጊ ቁሳቁሶች ዋጋ መናር ነዋሪዎችን እየፈተነ ነው። ሥራቸውን ያጡ አቅመ ደካማ ሰዎች የመግዛት አቅማቸው ቀንሷል" ብሏል UNOCHA በሪፖርቱ።

ለአብነት ፥ የምግብ ዘይት በመቐለ 433 ፐርሰንት ፤ በሽረ ደግሞ በ220 ፐርሰንት ጨምሯል።

በተለይ ከሰኔ ወዲህ ሲቪል ሠራተኞች እና ሌሎችም ተቀጣሪዎች ደሞዛቸው ስለተቋረጠ መሠረታዊ አቅርቦት ለማሟላት ተቸግረዋል።

በባንኮች በቂ ገንዘብ ባለመኖሩ፤ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞችም ለወራት ደመወዝ እንዳልወሰዱ ሪፖርቱ ያሳያል።

"ታማኝ ሪፖርቶች እንደጠቆሙን ከሆነ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ እና በእርዳታ የተሰጧቸው ቁሳቁሶችን እየሸጡ ምግብ እየገዙ ነው" ብሏል።

በሌላ በኩል በአጎራባቾቹ የአማራ እና አፋር ክልሎችም ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን የUNOCHA ሪፖርት ያሳያል።

በአማራ ክልል ከሰሜን ጎንደር፣ ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከደቡብ ወሎ እና ከአዊ ዞኖች የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አፋጣኝ እርዳታ ያሻቸዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNOCHA-10-08

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹 vs #SouthAfrica🇿🇦

ነገ የሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር ይፋለማል።

ጨዋታው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ነው የሚካሄደው።

ለዚሁ ጨዋታ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ 28/01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ሲል ባህርዳር ደርሰዋል።

የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ የመጨረሻ ልምምድ በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አድርገዋል።

ከነገው ጨዋታ ጋር በተያያዘ የብሄራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዛሬ አመሻሽ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ (ስፖርት) በኩል ደግሞ ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ : https://publielectoral.lat/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

#ምንጊዜም_ኢትዮጵያ❤️

@tikvahethsport @tikvahethiopia
የድሬዳዋ አስተዳደር ለነዋሪዎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

በድሬዳዋ ዴልታ በመባል የሚታወቀውና በዓለማችን ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የኮቪድ ዝርያ እንዲሁም ደንጊ ፣ ቺክንጉኒያ እና ወባ #አሳሳቢ በሚባል ደረጃ በመከሰቱ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የከተማው አስተዳደር አስጠንቅቋል።

ከዚህ ተደራራቢ ችግር ሊወጣ የሚቻለው ማህበረሰቡ አሁን ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ እንደ አንድ በመሆን እርምጃዎች ሲወስድ ብቻ ነው ብሏል አስተዳደሩ።

ማህበረሰቡ ሊወስድ ይገባቸዋል ያላቸው እርምጃዎችም ፦

1ኛ. ሁሉም ሰው ከቤት ውጪ ሲንቀቀስ የአፍን እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ፣ አካላዊ እርቀትን መጠበቅና የእጆችን ንፅህና መጠበቅ።

2ኛ. ዘወትር አካባቢን ማጽዳት፣ ንፅህናዉን በሚገባ መጠበቅና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማፍሰስ።

3ኛ. ከትንኝ ንድፊያ የሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል በጸረ ትንኝ መድሃኒት የተነከሩ አጎበሮችን መጠቀም የሚሉት ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ሆኗል። #NobelPeacePrize2020 @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize2021

የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች ታወቁ።

የፊሊፒንስ ጋዜጠኛዋ ማሪያ ሪሳ እና ሩስያዊው ጋዜጠኛ ዲሚትሪ ሙራቶቭ የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች መሆናቸውን የሽልማት ኮሚቴው ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።

የሽልማት ኮሚቴው ጋዜጠኞቹ ሽልማቱን ያገኙት "የመናገር ነፃነት እንዲከበር ላረጉት አስተዋፅኦ" እንደሆነ አስታውቋል። ኮሚቴው አክሎም "የመናገር ነፃነት ለዴሞክራሲ እና ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው" ብሏል።

ማሪያ ራፕለር የተባለው ሚድያ ስራ አስኪያጅ ስትሆን ዲሚትሪ ደግሞ ኖቫያ ጋዜቴ የተባለ የሩስያ ጋዜጣ አርታኢ ነው። ሁለቱም ከሽልማቱ ጋር የ1.1 ሚልዮን ዶላር ሽልማት ያገኛሉ።

ሽልማቱን አምና የአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እንዲሁም ካቻምና ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ማግኘታቸው ይታወሳል።

Credit : Journalist Elias Mesert

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SemiraMohammed ከሰሞኑን በአንድ ቪድዮ ላይ ልጇ ፊት በፖሊስ አባላት ስትደበብ የተመለከትናት ሰሚራ መሐመድ የስራ ዕድል እንደተፈጠረላት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ተሰምቷል። ግለሰቧ በልመና ላይ ተሰማርታ በነበረበት ወቅት በፖሊስ አባላት በርካቶችን ያስቆጣ ኢሰብዓዊ ድርጊት ከተፈፀመባት በኃላ የከተማ አስተዳደሩ በከንቲባ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ለግለሰቧ የስራ እድል እንደሚመቻች አሳውቆ…
ሰሚራ መሀመድ መኖሪያ ቤት ተሰጣት።

በፖሊስ አባላት ድብደባ የተፈፀመባት ሰሚራ መሀመድ ከቀናት በፊት በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ ዕድል እንደተፈጠረላት ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷታል።

ሰሚራ መሀመድ ቤተሰቦች፤ አመራሮችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የቁልፍ ርክክብ ስነስርዓት ተከናውኗል።

የመኖሪያ ቤት ቁልፋን በስፍራው በመገኘት ያስረከቡት የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ሲሆኑ ፤ አስተዳደሩ ለሰሚራ የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ምንጭ፦ የአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ "እንኳን ደስ አለዎት! " መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የ "እንኳን ደስ አለዎት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ፥ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በቀጣይም ለኢትዮጵያ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የበለጠ እንደሚጨምር "አምናለሁ" ሲሉ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ትብብርን በተለያዩ ዘርፎች በማዳበር "ለህዝቦቻችን" ጥቅም እንሰራለን ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መልካም እና ስኬታማ የስራ ዘመን ተመኝተዋል።

Credit : Russia in Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሹመታቸው የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። አዲስ የተሾሙት ሚኒስትሮች ዝርዝር ፦ 1. አቶ ደመቀ መኮንን - የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 2. ዶ/ር አብርሃም በላይ - የሃገር መከላከያ ሚኒስትር 3. አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትር 4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የስራና ክህሎት ሚኒስትር 5. አቶ ኡመር…
አቶ ቀጀላ መርዳሳ የሥራ ርክክብ አደረጉ፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከቀድሞው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ለአዲሱ ሚኒስትርም የቀድሞዋ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶ.ር ኂሩት ካሳው እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በርክክቡ ወቅትም ለሚኒስትሩ ስለ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አደረጃጀትና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች እንዲሁም ለወደፊት የታቀዱ እቅዶች በዶ.ር ኂሩት ካሳው ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡

አቶ ቀጀላ መርዳሳ ፥ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በመመደባቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያን ገፅታ ሊቀይር የሚችል ሥራን ለመሥራት የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ካለው አመራርና ሠራተኛ ጋር በመወያየት እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የሚኒስቴሩ አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡

ምንጭ፦ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

@tikvahethiopia