የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ "እንኳን ደስ አለዎት! " መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የ "እንኳን ደስ አለዎት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ፥ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በቀጣይም ለኢትዮጵያ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የበለጠ እንደሚጨምር "አምናለሁ" ሲሉ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ትብብርን በተለያዩ ዘርፎች በማዳበር "ለህዝቦቻችን" ጥቅም እንሰራለን ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መልካም እና ስኬታማ የስራ ዘመን ተመኝተዋል።

Credit : Russia in Ethiopia

@tikvahethiopia