TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቦሎ ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል ሊፈፀም ነው፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመታዊ የተሸከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ ለመሰብሰብ ከመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተሸከርካሪዎች ባለቤቶችን የዘመናዊ ክፍያ አሠራር ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የክፍያ አገልግሎቱን በባንኩ ቅርንጫፎች ፣ በፖስታ ቤት በሚገኙ የፖስ (POS) ማሽኖች እንዲሁም በኢንተርኔት የባንክ አገልግሎት በኩል በፍጥነት ያለእንግልት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ፦

• የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ - 5,557
• በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 980
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 760

* 392 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ አባላት በየትኛውም ቦታ ማስካችሁን ማድረግ እንዳትዘነጉ፣ ከሰዎች ጋር ያላችሁን አካላዊ ርቀት ጠብቁ ፤ የእጆቻችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትዘነጉ።

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NationalExam

በአ/አ ከተማ የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም እንከን እንዲካሄድ ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ።

ዛሬ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መቀጠል በሚችልበት ጉዳዮች ዙሪያ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኜ ገብሩ ርዕሰ መምህራን በየትምህርት ቤቱ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮችን በበላይነት መከታተል እና ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮችን የሚከታተል የአብይ እና ቴክኒክ ኮሚቴ እንደሚዋቀር አሳውቀዋል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀ ሁሉን ኃላፊነቱን ይወጣ ተብሏል።

በሌላ በኩል ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በየትምህርት ቤቱ የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት ከወዲሁ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TilahunGessesse🎤

በአዲስ አበባ ከተማ ከሸራተን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ ለክቡር አርቲስት ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ የሚሆን አደባባይ እና ሃውልት የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው በሸገር ወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ በሚገኝ 'ዝክረ አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ' በተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ነው።

የአ/አ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክቡር አርትስት ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ስም አደባባይና ሃውልት ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ይፋ ያደረጉ ሲሆን አርቲስቱ የበለጠ እንዲታወስና ህያው እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

"...የእጩ ተወዳዳሪዬ ቤት በጥይት ተደብድቧል" - የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ዛሬ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቋል።

መኢአድ በዘንድሮው ምርጫ በፌዴራል ደረጃ መንግስት ለመስረት በሚስችል የምክር ቤት ወንበር ቁጥር እንደሚወዳደር እና እጩዎችንም በዚህ ደረጃ ማስመዝገቡን አሳውቋል።

መኢአድ በእጩ ማስመዝገብ ሂደቱ በጎንደር የአንድ እጩ ተወዳዳሪው ቤት በጥይት መደብደቡ የገጠመው ከፍተኛው ችግር እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪው ማስፈራሪያና ዛቻ እንደደረሰበት አሳውቋል።

ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም ሂደቱ ጥሩ የሚባል እንደነበር ገልጿል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት እንዳስታወቀዉ እስከ ትናንት ድረስ በምርጫዉ ለመወዳደር ምልክት ከፀደቀላቸው 53 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩ ያስመዘገቡት 15ቱ ብቻ ናቸው።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦ - ትግራይ ነባር እና አዳዲስ ፖሊሶችን እያሰለጠነች ነው። ከፌዴራል ፖሊስ የሄዱ #ተጋሩ የፖሊስ አባላት ተደራጅተው በ6 ዞኖች መደበኛ 15 መሃል ወረዳዎች በመምረጥ ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታም እየተመቻቸ ነው። - ለትግራይ አዳዲስና ነባር ፖሊሶች ወንጀል ለመከላከል የሚሆን አስፈላጊ ትጥቅ መፈቀዱ። - የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል…
#BREAKING

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ #በትግራይ ጉዳይ ያለ ምንም ስምምነት መጠናቀቁን ዲፕሎማቶች መግለፃቸውን AFP ዘግቧል።

ሩስያ ፣ ቻይና እና ህንድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አስፈላጊ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል ፤ በዚህም የተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት ጥልቃ ከመግባት ትቆጠብ" - ሩስያ

አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡

ቡድኑ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆምም ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድኑ የአጋሮችን ፍላጎት ከግምት ሳያስገባ እና ሳያከብር የሚወስነው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን ነው ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የገለጹት።

twitter.com/mfa_russia/status/1367516464102723590?s=19

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MinistryOfHealth

ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባቷን እሁድ ወደ አገር ውስጥ እንደምታስገባ ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘገቧል።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኮቪድ - 19 ለመከላከል የሚውል የመጀመሪያው ዙር ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ የፊታችን እሁድ በ28/06/213 ዓ.ም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል።

በክትባቱ ርክክብ ላይ የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ሚንስቴሩ ገልጿል።

ይሁንና ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የክትባት መጠን አልተገለጸም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2ኛው ዙር የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ ተራዘመ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ፦
- በአዲስ አበባ
- በድሬዳዋ
- በኦሮሚያ
- በሃረሪ
- በጋምቤላ
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት መጠናቀቁን አሳውቋል።

የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልልሎች እና ቦታዎች ፦
- በአማራ
- በሶማሌ
- በአፋር
- በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣
- በደ/ብ/ብ/ህ
- በሲዳማ በመርሃ ግብሩ መሰረት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው አስታውሷል።

ነገር ግን በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ ፣ እንዲሁም የትራንስፓርት እና ሌሎች እክሎችን እና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል።

ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁም ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት ጥልቃ ከመግባት ትቆጠብ" - ሩስያ አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡ ቡድኑ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት…
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በይፋዊ ትዊተር ገፁ ይህን አስፍሯል ፦

"🇪🇹 🇷🇺 አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ አሜሪካ በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡"

@tikvahethiopiaBOT @tikvhaethiopia
ተማሪ የደበደበው መምህር በ4 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ ዕስራት ተቀጣ።

በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ በኩቢት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያስተምረው መምህር አነፀ ፍርዴን የ13 ዓመት ተማሪ ደብድቦ 2 የፊት ጥርስ በማውለቁ በአቃቢ ህግ ከሳሽነት በቀን 25/06/2013 ዓ.ም የመ/ላ/ም/ወ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት በ4 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ታውቋል።

@tikvahethiopia
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ።

ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል፦

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ የዘገበ ሲሆን በዘገባው ላይ ኡስታዝ አቡበክር በግል ይሁን በፓርቲ በምርጫው እንደሚወዳደሩ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥበቃ ያልተመደበላቸው የምርጫ ክልል ቢሮዎች በአስቸኳይ ጥበቃ እንዲመደብላቸው አሳሰበ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎችን በመክፈት የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ ነው።

የምርጫ ክልሎች ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ሃላፊነት የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች ነው።

ቦርዱ በተለያየ ጊዜ የምርጫውን ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች እና ንግግሮቸን እያደረገ የቆየ ሲሆን በዚህም መሰረት አብዛኛው የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ሊሟላላቸው እንደቻለ ገልጿል።

ነገር ግን አሁንም ፦

• በኦሮሚያ ክልል- 21 የምርጫ ክልሎች
• በሶማሌ ክልል- 31 የምርጫ ክልሎች
• አማራ ክልል- 40 የምርጫ ክልሎች
• በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል- 6 የምርጫ ክልሎች ጥበቃ እንዳልተመደበላቸው ገልጿል። በመሆኑም አስፈላጊውን የደህንነት ከለላ ከክልል መንግስታቱ እያገኙ አይደለም ብሏል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ክልሎች በአስቸኳይ ለቀሪ የምርጫ ክልል ቢሮዎች የጥበቃ ምደባ እንዲያከናውኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በጥበቃ ችግር ሊፈጠሩ የሚችሉ የምርጫ አፈጻጸም ችግሮች ክልል መስተዳድሮችና የጸጥታ አካላት ሃላፊነቱን ይወስዳሉ ሲል አስገንዝቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ !

ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።

ህብረቱ ዶክተር አርከበ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ ማቅረቡን ነው ያመለከተው።

የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት 38ተኛ መደበኛ ስብሰባ በየካቲት 24 እና የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ባደረገበት ወቅት ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ወክለው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።

ዶክተር አርከበ ባለፉት ሰላሳ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ላይ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDessalegnChanie

የቀድሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ /አብን/ ሊቀመንበር የነበሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያቸው ባሰራጩት መልዕክት ባህር ዳር ከተማን ፣ የባህር ዳርንና የአማራ ህዝብን ወክለው በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት ለመወዳደር መመዝገባቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ። እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ። ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል። በሌላ በኩል፦ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ…
ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

የህግ ምሩቅ የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 #በግል ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሃሩን ሚዲያ /Harun Media/ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ቀደም ብሎ በወጣው መረጃ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በዘንድሮው ምርጫ 2013 ላይ ለ ፓርላማ እንደሚወዳደሩ መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኦነግ በምርጫ 2013 ይሳተፋል ?

ትላንት በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የእጩዎች ምዝገባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንድም እጩ አላስመዘገበም።

የኦነግ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ፥ ኦነግ ምንም የእጩ ምዝገባ አለማድረጉ በምርጫው ላለመሳተፉ ጉልህ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ በቴ፥ "... በእኛ በኩል በተደጋጋሚ ስንገልፅ እንደነበረው ቢሮዎቻችን ፣ ዋና ፅ/ቤቶቻችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑ ፣ ነፃ እንቅስቃሴ እንደድርጅት መታገዱ ፣ አመራርና አባሎቻችን ያለህግ አግባብ መታሰራቸው ምርጫ ላይ በምናደርገው ተሳትፎ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸውና እነዚህ ችግሮች ሳይፈቱ መሳተፍ እንደማንችል ስንገልፅ ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም ስለዚህ በምርጫ ሂደቱ ተሳታፊ አይደለንም" ብለዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እስከ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባኤ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ከዚህ ቀደም የተነገረላቸው አቶ ቀጄላ መርዳሳ (የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) በበኩላቸው ፓርቲው ለ7 እና 8 ወር ችግር ላይ ስለነበር እጩ ለማቅረብ አስቸጋሪ እንደበር ገልፀዋል።

አቶ ቀጄላ ፥ ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤ የውስጥ ችግሮቹን ፈቶ በወጥ አመራር በምርጫ 2013 ለመሳተፍ እጬዎችን ለማስመዝገብ በተለየ ሁኔታ ጊዜ እንዲራዘምለት ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን አሳውቀዋል።

#EthiopiaElection2013 #DW #OLF
https://telegra.ph/Oromo-Liberation-FrontABO-03-05
#ማሳሰቢያ

በጢስ አባይ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚካሄደው ጥገና ምክንያት የጢስ አባይ ፏፏቴ ውሃ ከነገ የካቲት 27/2013 ዓ/ም ጀምሮ መጠኑ ጨምሮ ስለሚለቀቅ ከፏፏቴው ግርጌ በሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተብሏል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Alert😷

ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ዛሬ ሪፖርት ተደርጓል።

427 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,211 የኮቪድ - 19 ላብራቶሪ ምርመራ 1,119 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በዚሁ በ24 ሰዓት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል ፤ 228 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia