TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰላም ድርድሩ መቼ ይጀመር ይሆን ?

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም ድርድር እንዲቋጭ ከፍተኛ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል።

በፌዴራል መንግሥት እንዲሁም በህወሓት በኩል ለሰላም ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው በርካቶች ሰላም ይሰፍናል የሚል ትልቅ ተስፋን አሳድሮባቸዋል።

በሁለቱም በኩል ተደራዳሪዎች መሰየማቸው ከተሰማ በርካታ ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን መቼ ድርድሩ ይጀምራል የሚለው ትክክለኛ መልስ አላገኘም።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሞሊ ፊ ግን የሰላም ንግግሩ በነሐሴ ወር ሊጀመር ይችላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፊ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሽምግልና ለመፍታት ቁልፍ ሚና አላት ባሏት #ኬንያ ውስጥ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ድርድሩ እንደሚጀመር ጥንቃቄ የተሞላበትን ተስፋቸውን ለአገራቸው ም/ቤት ኮሚቴ መናገራቸውን AFP ፅፏል።

በኬንያ ሊካሄድ የተቃረበው ምርጫ በድርድሩ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መዛባትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ ገልጸዋል።

ኬንያ ነሐሴ 3/2014 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

በሌላ በኩል በተለያዩ አገራት ጉብኝታቸውን የጀመሩት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር "ድርድሩ ወደፊት እንዲራመድ አሜሪካ ምን ማድረግ እንደምትችል ከሁለቱም ወገኖች ጋር ይወያያሉ" ሲሉ ሞሊ ፊ ለኮሚቴው ተናግረዋል።

በተጨማሪ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ #ከአጎዋ መታገድን እያጤነው መሆኑን ተናግረዋል።

የጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ አንጻር ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለማድረግ የተሻለ ሁኔታ መኖር አለመኖሩን " በቅርበት እያጤነ ነው " ሲሉ ፊ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ፦ telegra.ph/AFP-07-29

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#KenyaElection🇰🇪 የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ? ኬንያ እያካሄደች ያለችውን 5ኛው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ይገኛሉ። 🇪🇹 አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገውን 'ብሬንትረስት ፋውንዴሽን'ን በመወከል ምርጫውን እየታዘቡ ናቸው። አቶ ኃይለማርያም…
#Kenya🇰🇪

የኬንያ ምርጫ ውጤት ከምን ደረሰ ?

ጎረቤት ሀገር #ኬንያ ከቀናት በፊት ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳደረገች ይታወቃል።

እስካሁን ድረስ የምርጫው አሸናፊ አልታወቀም። ቆጠራውም አልተጠናቀቀም።

የውጤት ቆጠራው ምርጫው ከተጠናቀቀበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ እየተካሄድ ይገኛል።

እስካሁን ያለው ውጤት ከላይ ተያይዟል።

ከላይ በምስሉ ላይ የተያያዘው የምርጫ ውጤት የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ክፍል ምርጫውን ከሚያስፈጽመው ኮሚሽን ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ ዋቢ አደርጎ ያሰራጨው ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኬንያ

የኬንያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እስካሁን ድረስ ይፋ አልሆነም።

ከሰዓታት በፊት ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት ሊያሳውቅ አልቻልም።

ውጤት በሚገለፅበት ቦማስ የድምፅ ቆጠራ ማዕከልም እስከ መደባደብ የደረሰ አለመግባባት ተፈጥሯል።

በጎረቤታችን ኬንያ እየሆነ ስላለው ጉዳይ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ የኬንያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እስካሁን ድረስ ይፋ አልሆነም። ከሰዓታት በፊት ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ኮሚሽኑ የምርጫውን ውጤት ሊያሳውቅ አልቻልም። ውጤት በሚገለፅበት ቦማስ የድምፅ ቆጠራ ማዕከልም እስከ መደባደብ የደረሰ አለመግባባት ተፈጥሯል። በጎረቤታችን ኬንያ እየሆነ ስላለው ጉዳይ ተከታትለን እናሳውቃለን። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኬንያ

በኬንያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ይፋ ይደረጋል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ አለመግባባት እና ውዝግብ ተፈጥሯል።

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን ውጤት ያሳውቃሉ ተብለው በሚጠበቁት የኮሚሽኑ ባለሥልጣንት መካከል ክፍፍል መፈጠሩ ነው የተነገረው።

በዚህም 4 የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በይፋ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ከሚነገርበት ማዕከል ውጪ መሃል ናይሮቢ በሚገኘው ሴሬና ሆቴል ውስጥ ሂደቱን ጥያቄ ላይ በሚጥል ሁኔታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ከ6ቱ ኮሚሽነሮች አራቱ በሰጡት መግለጫ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት አያያዝ “ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ፣ ውጤቱን በኃላፊነት ለመውሰድ አንችልም” በማለት ገልጸዋል።

ውጤት በኮሚሽነሩ ዋፉላ ቺቡካቲ አማካይነት ይፋ ይደረግበታል በተባለው የቦማስ ማዕከል ውዝግብና ግብግብ ተፈጥሮ ታይቷል።

ለደቂቃዎች በአዳራሹ የነበረ ውጥረት ረግቦ በአሁን ሰዓት በአዳራሹ መርሀግብሩ ቀጥሏል። በአዳራሹ ውስጥ ሩቶ ቢገኙም ዋነኛ ተፎካካሪው ራይላ ኦዲንጋ የሉም።

በተለያዩ የኬንያ አካባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱም ተነግሯል።

Via BBC
Video Credit : CitizenTV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኬንያ

የተመራጩ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት እንግዶች ወደ ኬንያ በመግባት ላይ ናቸው።

እስካሁን ባለው ፦
- የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠ/ ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣
- የሩዋንዳ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፣
- የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣
- የሞዛምቢክ ፕሬዜዳንት ፊሊፕ ኒዩሲ ፣
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመትን ጨምሮ ሌሎችም እንግዶች ገብተዋል።

በቀጣይ ሰዓታትም ተጨማሪ እንግዶች ኬንያ ይደርሳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ከቀናት በፊት ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ለሩቶ በዓለ ሲመት የኢትዮጵያን መሪ ጨምሮ በአጠቃላይ ከ40 በላይ የሃገራት መንግሥታት እና የመንግሥታት ተጠሪዎችን መጋበዛቸው ይታወሳል።

Photo Credit : የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል። @tikvahethiopia
#UK

የሀገራችን ኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤ የጎረቤታችን ኬንያ፣ ሶማሊያ ፣ ሱዳን መሪዎች ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መጓዛቸው ተሰምቷል።

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በንግስቷ ህልፈት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ለንደን የገቡ ሲሆን ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ፤ ዛሬ ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ስርዓተ ቀብር ወደ ለንደን በረዋል። ፕሬዜዳንቱ በስርዓተ ቀብሩ ላይ ከታደሙ በኃላ ወደ ኒውዮርክ በማቅናት 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚታደሙና ከዓለም መሪዎች ጋር እንደሚቀለቀሉ ገልፀዋል።

በንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈት #ኬንያ የ3 ቀን ብሄራዊ ሀዘን አውጃ እንደነበር ይታወሳል። በንግስቷ ሞት በኬንያ ሀዘን መታወጁ በቅኝ ግዛት ወቅት ከተፈፀሙ ግፎች ጋር በተያያዘ በርካቶች ሲቃወሙ ነበር።

በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ለንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ድርዓተ ቀብር ዛሬ ለንደን ገብተዋል። ለንግሥቲቱ በተዘጋጀ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ላይም ሀዘናቸውን እንደገለፁ ተሰምቷል።

የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃንም ወደ ለንደን አቅንተዋል።

@tikvahethiopia @officialtikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አምባሳደር ማይክ ሐመር ኬንያ ይገኛሉ። የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ሩቶ ከአሜሪካው አምባሳደር ሐመር ጋር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ " ሰላምና መረጋጋት ለአገሮች ልማትና ብልፅግና የግድ አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን ኬንያ ፤ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም…
#Update

አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ማይክ ሐመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር #ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።

አቶ ደመቀ መኮን በውይይቱ ወቅት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በበኩላቸው፤ አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " በውይይቱ ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል " ሲል አሳውቋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከቀናት በፊት #ኬንያ እንደነበሩና ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

አሜሪካ አምባሳደር ሐመርን ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ወደ ኬንያ#ደቡብ_አፍሪካ ፣ ኢትዮጵያ እንደላከች ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ #እንዲያዙ_ለጠቆመ 10,000,000 (አስር ሚሊዮን) ዶላር ወሮታ ሰጣለሁ ያለቻቸው የአልሻባብ የሽብር ቡድን አመራሮች እነማን ናቸው ?

የአሜሪካ መንግሥት ሶስቱን (በፎቶ ያሚታዩትን) የአልሸባብ ቡድን መሪዎች ለመያዝ የሚያግዝ መረጃ ለሚሰጡ ሰዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ወሮታ እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ማሳደጉን አስታውቋል።

የአሜሪካ ዜግነት ያለውን ግለሰብ እና ለላፉት 14 ዓመታት የቡድኑ ከፍተኛ መሪዎች የሆኑትን ሁለቱን ግለሰቦች ጨምሮ አህመድ ድሪዬ፣ ማሃድ ካራቴና ጂሃድ ሙስጠፋ የተባሉትን ሶስቱን ሰዎች ፍለጋ የሶማልያ ዜጎችና በአካባቢው የሚገኙ ሀገሮች እንዲተባበሩ የአሜሪካ መንግሥት ጠይቋል፡፡

ሶስቱ ግለሰቦች በ #ሶማልያ እና #ኬንያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለሞቱባቸው ጥቃቶች በተጠያቂነት የተከሰሱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሶማልያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ላሪ አንድሬ ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የ10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ከዚህ በፊት ከነበረው ወሮታ #በእጥፍ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ ፤ የሶማልያ መንግሥት ከአልቃይዳጋር ግንኙነት ያለውን አልሻባብን ድል በመንሳት እያደረገ ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ኬንያ

በጎረቤት ኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አንድ ሰው ተገደለ።

የኬንያ ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ የኑሮ መወደድን እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገው ደጋፊዎቻቸው ዛሬ ሰኞ መጋቢት 11/2015 ዓ.ም. ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ ጠርተው ነበር።

የኬንያ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፉ ሕገወጥ እና ያልተፈቀደ ነው ቢልም፣ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ውስጥ በአንስተኛ ደረጃ ወደ ጎዳና የወጡ ተቃዋሚዎች ታይተዋል።

ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን ከፍተኛ ኃይል ያለው ውሃ እና አስለቃሽ ጋዝ የተጠቀመ ሲሆን፣ እስካሁን አንድ ሰው ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መሞቱ ተዘግቧል።

የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት ክሳቸውን ውድቅ ቢያደርገውም ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተካሄደው ምርጫ ተሰርቋል የሚለውን ክሳቸውን አሁንም እያቀረቡ ነው።

በተጨማሪም ሥልጣን ከያዘ ስድስት ወራትን ያስቆጠረው የዊሊያም ሩቶ መንግሥት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለውን የኑሮ ውድነት መፍትሄ ሊያበጅለት አልቻለም በማለት ደጋፊዎቻቸውን ለአደባባይ ተቃውሞ ጠርተዋል።

በተለይ ኦዲንጋ ከፍተኛ ደጋፊ ባላቸው የናይሮቢ የድሆች መኖሪያ በሆነው ኪቤራ አካባቢ ፖሊሶች ከተቃዋሚዎች ጋር ተጋጭተዋል።

በማዕከላዊ ናይሮቢ የሚገኙ የንግድ ተቋማትም የፀጥታ ችግሩን በመፍራት ዝግ ሆነው አስከ እኩለ ቀን ድረስ የቆዩ ሲሆን፣ ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጋዝ በትነዋል።

በማዕከላዊ የከተማዋ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የኬንያታ ጎዳና ላይም አንዳንድ ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ መታየታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia