TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ

" በምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት ሦስት ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል " - የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦
° 65 በመቶ የሚሆን #ገዳይ የወባ ዝርያ እንዳለ፣
° በአንድ ዓመት ውስጥ 101 ሰዎች በወባ እንደሞቱ፣
° ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋማት እንዲሄድና አጎበር የመጠቀም ልምዱን እንዲያዳብር የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ተስፋፅዮን ተረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ኩፍኝ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

* ምዕራብ ኦሞ ዞን ባለፉት 3 ወራት 9,000 #ህፃናት በኩፍኝ ተጠቅተዋል። 11 ሞት ተመዝግቧል። በክልሉ በአንድ ዓመት ውስጥ 12,700 የኩፍኝ ኬዞች ተገኝተዋል። 

* ከሌሎች ቦታዎች በተለዬ መልኩ በምዕራብ ኦሞ ዞን አሁንም ከፍተኛ ሥራ የሚጠይቅ የኩፍኝ ወረርሽኝ ስርጭት አለ። በመቀጠልም በቤንቺ ሸኮና ከፋ ዞኖች በተወሰኑ ወረዳዎች ይስተዋላል።

* አርሶ አደሮች በሚኖሩባቸው ( #በተለይም ምዕራብ ኦሞ)፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የክትባት አሰጣጡን አፌክት ያደርገዋል።

* #አርሶ_አደሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ ችግሩ እንዲቀረፍ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በአካባቢው ተንቀሳቀሰው ሕክምና እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።
 
* የኩፍኝ ኬዞች ያሉባቸው አራት ዞኖች ናቸው። ቤንቺ ሸኮ ዞን ላይ ወደ 3,000፣ ከፋ ዞን ከ1,000 በላይ ኬዞች ነበሩ ፤ አሁን መቆጣጠር ተችሏል።

* ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለማድረግ ጤና ሚኒስቴር ፈቅዷል። ከአምስት ዓመት በታች ለሚሆኑ ሕፃናት ክትባት ይደረጋል።
 
ወባ በምን ደረጃ ይገኛል?

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃልፊ አቶ ኢብራሄም ተማሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦

- ለሁለት ዓመታት #የወባ_ወረርሽኝ በክልሉ ተከስቶ ቆይቷል። የኩፍኝ ወረርሽኝም በተለይ በምዕራብ ኦሞ ዞን ልዩ ትኩረት ይሻል። ከእስከዛሬው ጋር ሲነጻጸር ግን ኬዞቹ እየቀነሱ ነው። ግን አሁንም ሥራ ይጠይቃል።

- የወባ ወረርሽኝ ቆዬ ስንል በርካታ ሥራዎችን ሰርተናል ከወባ ጋር ተያይዞ ወደ 1.2 ሚሊዮን የአጎበር ስርጭት ተካሂዷል። ከ6,000 ኪ.ግ በላይ እርጭት ተካሂዷል።

- አሁንም ውሃ ያቆሩ ቦታዎች ላይ እርጭት እያካሄድን ነው ፤ በጣም በተለየ መንገድ ምዕራብ ኦሞ ላይ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያለው ግብዓት አሰራጭተን የመከላከሉን ሥራ እየሰራን ነው።

አቶ ተስፋፅዮ በበኩላቸው ስለ ወባ ምን አሉ ?

* የተወሰኑ ወረዳዎችን ላያካትት ይችል ይሆናል እንጂ ሁሉም  ዞኖች በጣም ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ናቸው።

* በአመት ውስጥ #በ6_ዞኖች በወባ ወደ 101 ሞት ተመዝግቧል። አሁን ግን ማኅበረሰቡ  በአቅራቢያቸው ህክምና እያገኙ ስለሆነ የህመም (የኬዝ)፣ የሞት መጠኑ በዛው ልክ ቀንሷል።

* ላለፉት ሁለት ዓመት ለዚህ መንስኤ የሆኑ ጥናቶች ለማድረግ ሞክረናል፣ የምላሽ ሥራው ተሰርቷል።

* እስካሁን ባለው በአጠቃላይ ወደ 400,054 ሰዎች በአንድ ዓመት የወባ አይነቶች ተለይተው ህክምና ያገኙ ናቸው።

* በተሰሩ ሥራዎች በተለይ ከአራት ወራት በፊት እስከ 15,000 ሰዎች በወባ ይጠቁ ነበር። አሁን ባለንበት በሳምንት በወባ የመጠቃቱ ሁኔታ ከ7,000 እስከ 6,000 ሰዎች ዝቅ ለማድረግ ተችላል።

* በመከላከል ላይ ያለ ክፍተት ነው የወባ ቁጥር ከፍ ብሎ እዲታይ እያደረገ ያለው። ምዕራብ ኦሞ ፣ ካፋ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አርብቶ አደሮች ናቸው በተለይ ተጋላጭ የሆኑት።

* ከጤና ኬላ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሆስፒታል ድረስ የወባ ህክምና አለ።

* ሞት እያስከተለ ያለው ቆይተው ስለሚመጡ ነው። ቆይተው ሲመጡ ደግሞ በክልላችን #ከ65 ፐርሰት በላይ ፋልሲፋረም የሚባል በባህሪው #ገዳይ የሆነ ዝርያ ነው ያለው።

* በእኛ ክልል ላይ የሚበዛው ያ " ፋልሲፋረም " ነው። ሰዎች ወዳውኑ ምልክቱን እንዳዩ የመወሳሰብ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወደ ጤና ተቋማት ሂደው መታከም አለባቸው። ችግሩ ሲወሳሰብ ደም ሊፈልግ ይችላል፣ #ነፍሰ ጡሮችን በተለይ ወዲያው የመግደል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ለ2ቱም ወረርሽኞች ለሞት አደጋው መከሰት ምክንያቱ ፦

° የሕሙማን ወደ ሕክምና #ዘግይቶ መምጣት፣

° #የጤና_ኤክስቴንሽኖች ወረርሽኝ አካባቢዎች ላይ አክቲቭ አለመሆንና በወቅቱ ለይቶ አለመላክ ነበር።

* በዘላቂነት ችግሮቹን ለማስወገድ ክልሉ የንቅናቄ መድረክ እንያዘጋጀ ነው። አሁንም ዝናብ ወጣ እየገባ እያለ ስለሆነ ለወባ መራባት እጅግ በጣም ምቹ አጋጣሚ ስለሚፈጥር ማህበረሰቡ ጥንቃቄ ሊያደግ ይገባል።

ጥንቅሩ በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia