TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሲስተም የለም⁉️

#ሲስተም_የለም በሚል ምክንያት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን የአዲስ አባባና አካባቢዋ አንዳንድ የካርድ ክፍያ ተጠቃሚዎች ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ካዛንቺስ ቅርንጫፍ ኢዜአ ካገኛቸው ነዋሪዎች መካከል ከቱሉ ዲምቱ እንደመጡ የሚናገሩት ወይዘሮ መስከረም ዲንሳሰ “ካርድ የምንሞላው አቃቂ ቢሆንም ባለፈው ሀሙስ አቃቂ ሲስተም የለም ተብዬ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ቢሄድም አገልግሎቱን ላገኝ አልቻልኩም” ነው ያሉት፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ከሶስት ቀን መጉላላት በኋላ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ ካዛንቺስ ብገኙም እስካሁን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ልሆኑ አለመቻላቸውን ነው የገለጹት።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔹 " እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው #በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው " የመ/ግ/ን/ባ

በመንግሥት የግዥ ሒደት እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆኑን፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘንድሮ በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሲስተም ተግባራዊ ተደርጎና አፈጻጸሙን ለማሳደግ፣ ከንግድ ማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ምን አሉ ?

- በመንግሥት በግዥ ሥርዓት ውስጥ፣ ከ80 እስከ ከ90 በመቶ በላይ ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው ብለዋል።

- ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የመንግሥት ተቋም #በጨረታ አንደኛ የወጣ ድርጅት እያለ ሦስተኛ ከወጣው ጋር ውል መግባቱን፣ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

- ከኮንስትራክሽን ጋር ተያይዞ ጨረታ የሚያወጡ የመንግሥት ተቋማት #የሚፈልጉዋቸው ተጫራቾች ካልመጡ እስከ #መሰረዝ እንደሚደርሱ አመልክተዋል።

- የመንግሥት ተቋማት ተጫራቾችን ሆን ብለው ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ሕጎችን እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሙ፣ ያሸነፉ ተጫራቾችንም #እንዲሰላቹ በማድረግ ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

- በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምክንያት የሚመጡ ክሶች መኖራቸውን ገልጸው በዓመት እስከ 150 የሚደርሱ ክሶች እንደሚስተናግዱ ተናግረዋል። በአብዛኛው ጨረታ የማውጣትና የሚገመገምበት መሥፈርት በመለያየቱ ምክንያት በርካታ ተጫራቾች ክስ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢጋድ አባል አገሮችና የነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ ምን አሉ ?

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ከታዩ ክፍተቶች አንዱ በጠቅላላ የመንግሥት ግዥ መባሉ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- የመንግሥት ግዥ ተብሎ ስያሜ ቢሰጠውም የመንግሥት ተቋማትና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚገናኙ በመሆናቸው ከስያሜ ጀምሮ ማስተካከያ ይፈልጋል ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ሙስናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጻዋል። ከዚህ ቀደም #በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ግዥዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እየቀረቡ እንደነበርና ሥርዓቱ መዘመኑ በተወሰነ መንገድ ችግሩን መቀረፉን አስረድተዋል፡፡

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ለሚታዩ የሙስና ብልሹ አሠራርን ከሥሩ ማድረቅ እንደሚገባ፣ በተለይ ተጫራጮች ወደ ተቋማት ሲሄዱ #ሲስተም_የለም የሚለው ቋንቋ የችግሩ መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- ተጫራቾች ወይም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለሙስና እንዳይጋለጡ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሞጋችና ተከራካሪ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የመንግሥት ግዥ የንብረት ባለሥልጣን የመንግሥት ግዥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ከበደ ምን አሉ ?

- የነባሩ የወረቀት የግዥ ሥርዓት የሙስና ተጋላጭነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መኖሩ የሚቀርፏቸው ችግሮች ሰፊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለብዙ ተጫራቾች ዕድል ከመስጠት አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

- የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት በ2015 ዓ.ም. ሲጀመር የተመዘገቡት የንግድ ማኅበረሰብ አባላት 100 ብቻ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከ15‚000 በላይ ተሻግረዋል።

- ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ 70 በመቶ የሚውለው ለግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ይህም በገንዘብ ሲቀየር 560 ቢሊዮን ብር ለግዥ እንደሚውል ተናግረዋል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

" ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ነው " እየተባለ ወደ ተለያዩ የባንኩ ደንበኞች ስልክ እየተደወለ የግል መረጃ መውሰድና የኦንላይን ዝርፊያ እየተሞከረ ይገኛል።

ቀደም ብሎ አንድ #አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ - ወንድ) ሳያውቀው ለባንክ ሰራተኛ ደውሎ ያጋጠመውን ክስተት አጋርተናል።

የዜጎችን ሀቅና ገንዘብ አታለው ለመዝረፍ ስልክ ከሚደውሉት መካከል #ሴቶችም ስለሚገኙበት ጥንቃቄ አድርጉ።

ከላይ ባለው የድምፅ ቅጂ የምትሰሟት አጭበርባሪ ግለሰብ (ጾታ-ሴት) ከንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት እንደደወለች በማስመሰል ፦ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ኔትዎርኩ please try again ፣ connection problem ፣ error ፣ service not available " የሚል ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ትገልጸለች።

በዚህ ምክንያት ባንኩ ከብዙ ደንበኞቹ ቅሬታ በመምጣቱ ፤ " ችግሩን በዋናው የንግድ ባንክ መ/ ቤት #ሲስተም ላይ ለማስተከል ነው " በማለት የደንበኛውን የግል መረጃዎች በመቀበልና በማታለል ዝርፊያ ለመፈፀም ሞክራለች።

አሁን ላይ እንዲህ ያሉት አጭበርባሪዎች ተበራክተዋል ተጠንቀቁ።

ለማንኛውም #የማታውቁት ስልክ የባንክ መረጃችሁን እንዳትሰጡ።

@tikvahethiopia