TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል!

ዎሕዴግ በላከልን ወቅታዊ መግለጫ ነሃሴ 3/2012 ዓ/ም የዞኑ ስራ ኃላፊዎች ስለአካባቢው ሰላምና መልካም አስተዳደር ጥንካሬን በማስመልከት በቁጥር 28 ከሚሆኑ አጋዥ ኃይሎች ጋር ሆነ በመመካከር ካሉበት አዳራሽ ታፍሰው እስር ቤት እንዲገቡ ተደርገዋል ብሏል።

ዎሕዴግ ከዚህ ክስተት በኃላ በዞኑ የሃያ አንድ (21) ሰዎች ህይወት እንዲቀጠፍ ተደርጓል ፤ በርካቶችም አካለ ጎዶሎ ሆነዋል ሲል በላከልን መግለጫ ላይ አስታውቋል።

የህዝቡን ተወካዮች በሐሰት የተቀነባበረ ማስረጃ እያቀረቡ መደበኛ ስራ ላይ ካሉበት ይዞ ወደ እስር ቤት ማስገባት እጅግ አሳዛኝ ተግባር ሆኖ አግኝቼዋለሁም ብሏል።

ምንም አይነት አመፅ ባልተካሄደበት ዞን ውስጥ ተደጋጋሚ ሁከት የተፈጠረ በማስመሰል ህዝቡን የሚያሸብር ገለፃ በመስጠት ሰላማዊ ሰዎችን ለእስራትና ለከፋ ጉዳት መዳረግ የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴን ክፉኛ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም አይደለም ብሏል ዎህዴግ።

ዎሕዴግ በመግለጫው በቁጥጥር ስር የዋሉ የዞን አስተዳደር ኃላፊዎች ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

በዞኑ ከተከሰተው አስከፊ ድርጊት ጋር በተያያዙ የንፁሃን ዜጎች ህይወት ያጠፉ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲደረግ አሳስቧል።

በዎላይታ ህዝብ ላይ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም እንዲሁም የዎላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄው በአስቸኳይ ተገቢው ህገ መንግስታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ዎሕዴግ ጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SputnikV

የሩስያ ጤና ሚንስትር ሚካኤሊ ሙራሽኮ በዛሬው ዕለት ሀገራቸው ይፋ ያደረገችው ክትባት “በጣም ውጤታማና ደህንነቱ የሚያስተማምን” ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ ክትባቱ የሰው ልጆች ኮቪድ-19ን ድል የሚነሱበት እርምጃ እንደሆነም መግለፃቸውን BBC ዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት፤ የሩስያ መንግሥት ክትባቱ ላይ ስኬታማ ምርምር እንዳካሄደ አስታውቆ ፤ በጅምላ ክትባቱን መስጠት እንደሚጀምር ይፋ አድርጎ ነበር።

በመላው ዓለም ወደ 100 የሚጠጉ ክትባቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ይገኛል። ከነዚህ መካከል በሰው ላይ ሙከራ የተካሄደባቸውም አሉ።

ክትባት የማግኘት ሂደት ፈጣን ቢሆንም በርካታ ባለሙያዎች እስከ ቀጣዩ ዓመት አጋማሽ ድረስ ክትባት በስፋት አይዳረስም ይላሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር “አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው” ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አያይዘው፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ አስምረውበታል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረውና ሸሽቶ በሃምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም አዳአ ድሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለው ከበደ ገመቹ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

በዛሬው ዕለት በነበረው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በተጠርጣሪው ላይ የሰራውን ምርመራ ስራ ገልጿል። እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች ተጨማሪ ምርመራዎች 14 ቀን እንዲሰጠውም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው በአስተርጓሚ አስተያየት ካለው እንዲያቀርብ የተጠየቀ ቢሆንም ፥ ምንም አይነት አስተያየት እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ መርመራ ለፖሊስ 14 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Tarik Adugan (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል!

'የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ' ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የሰራውን የምርመራ ስራ ገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ስራ ለመስራት ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነሃሴ 8/ 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ /ምክክር/ በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ የሚታገልባቸው የምርጫ ማኒፌስቶ 132 ገፅ የያዘ እና 70 አንቀፆች ያሉትን በማዘጋጀት ከነሀሴ 02 እስከ ነሀሴ 04 ቀን 2012 ዓ.ም (ለ3 ተከታታይ ቀናት) ከፍተኛ አመራሩ ውይይት አድርጎ ማሻሻያዎችን በማድረግ አፅድቋል በዚህ ጉዳይ ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በወላይታ ዞን የጸጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል ከመጠቀም ሊቆጠቡ ይገባል!" - ኢሰመኮ

በወላይታ በዞን አንዳንድ አከባቢዎች ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በተደረጉት ተቃውሞዎች የፀጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት እርምጃ ተመጣጣኝነት አጠያያቂ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ለሰልፍ ወጥተው ሞቱ ባላቸው 6 ሰዎችን አስመልክቶ ፈጣን ምርመራ የሚያስፈልግ መሆኑን በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቃል አቀባይ፣ አቶ አሮን ማሾ እንደገለጹት “የፀጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፎችን በሚቆጣጠሩበት ወቅት የሞት አደጋን የሚያስከትል የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጠቡ ይገባል፤ እንደነዚህ ያሉ እርምጃዎች ቀድሞውኑን የነበረ ውጥረትን ያባብሱ እንደሆን እንጂ መፍትሔ አይሆኑም” ብለዋል፡፡

በሰኞው እስር ወቅት በጠቅላላው 178 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 28ቱ የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሆናቸው እና በወላይታ ሶዶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ውስጥ በቁጥጥር ስር የሚገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢሰመኮ የታሳሪዎችን መብቶች ማክበርና በአፋጣኝ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ24 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 11,881 የላብራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 285 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 24,175 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 440 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,696 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ ጃዋር የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ!

የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገ።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የአራዳ ተረኛ ወንጀል ችሎት ላይ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

መርማሪ ፖሊስ ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ ማጠናቀቁን በመግለጽ፤ ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪው ላይ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እንደከፈተባቸው አስታውቋል። በመሆኑም የምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ ጠይቋል።

የአቶ ጃዋር ጠበቃ በበኩላቸው በደንበኛቸው ላይ ፖሊስ ባካሄደው የምርመራ ስራ ያገኘው ውጤት ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው እንዲጠበቅ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ጉዳዩን የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው ወደ ፊት ክስ የሚመሰረትባቸው ከሆነ የተጠረጠሩበት መዝገብ የሰው ህይወት የጠፋበትና ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።

ተጠርጣሪው (አቶ ጃዋር መሃመድ) ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት መብታቸውን መጠየቅ እንደሚችሉ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ተዘግቷል - ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለነገ ቀጠረ።

#MORE : telegra.ph/EskinderNega-08-11

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ!

የአማራ ብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት በክልሉና በሀገሪቱ ጉዳዮች በባህር ዳር ስብሰባ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ 'ከውስጥ ያገኘነው መረጃ' በማለት እየወጡ ያሉ መረጃዎች #ሀሰተኛ መሆናቸውን የአማራ ክልል ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ምርጫ ቅስቀሳ ነገ ይጀምራል!

የትግራይ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ ነሐሴ 5/2012 ዓ/ም መጀመር የነበረበት ቢሆንም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለፕሮዳክሽን ዝግጅት በአንድ ቀን እንዲገፋላቸው በጠየቁት መሰረት ከነገ ነሃሴ 6/2012 ዓ/ም ጀምሮ ቅስቀሳ ይጀምራሉ።

የድምፂ ወያነ ቲቪ፣ ትግራይ ቲቪ ፣ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ፣ ኤፍ ኤም መቐለ 104.4 ፣ ሞሞና ሬድዮ ጣቢያ፣ ድምፂ ወያነ ሬድዮ ፣ ብሄራዊ ኤፍ ኤም ሬድዮ እና መቓልሕ ጋዜጣ ቅስቀሳ የሚደረግባቸው ሚዲያዎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጫልቱ ታከለ ከእስር ተፈታች!

በዋስ እንድትፈታ ፍርድ ቤት ወስኖላት ከእስር ሳትፈታ የቆየችው ጫልቱ ታከለ በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈታ ከቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና የተያዙ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪዎች!

- በትግራይ ክልል እስካሁን ከ30 በላይ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በቫይረሱ ተይዘዋል ፤ አላማጣ ብቻ በላብራቶሪ ቴክኒሻንነት የሚሰሩ 7 ባለሞያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ በአይደር ሆስፒታል 3 ከፍተኛ የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ ብዙ ሃኪሞች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአማራ ክልል እስካሁን 23 የሚደርሱ የጤና ባለሞያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እስካሁን 21 የሚደርሱ የጤና ባለሞያዎች እና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በሲዳማ ክልል እስካሁን 13 የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ሁለት (2) የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በኦሮሚያ ክልል እስካሁን 34 የጤና ባለሞያዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ መደበኛ አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው። #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ይህን ተከትሎም ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡

በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ መዝገብ አስራ አራት (14) ሰዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጠርጥሮ ችሎት አልቀረበም፡፡

Via Tarik Adugna (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ደሴ ማረሚያ ቤት በተደረገ የኮቪድ-19 ምርመራ 10 ህግ ታራሚዎች ቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን የከተማው ጤና መምሪያ ኃላፊ ለቪኦኤ አስታውቀዋል። በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ወደ ቦሩ ሜዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና ተልከዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ከቀናት በፊት በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊንር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ቁጥራቸው ወደ ሃምሣ (50) የሚጠጋ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የምሥራቅ ባሌ ዞን አስተዳደር መረጃውን ለቪኦኤ ያረጋገጠ ሲሆን ከተጋላጮቹ ጋር ቅርበትና ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች እየተከታተለ መሆኑን እና ሌሎች እስረኞችም ለኮቪድ-19 እንዳይጋለጡ/በቫይረሱ እንዳይያዙ ለመከላከል የተለያየ ስራ እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia