TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዘፍመሽ ግራንድ ሞል የንግድ ማእከል ባለቤት ሙሃመድ አህመድ ለ180 ተከራዮች የ3 ወራት የኪራይ ክፍያ 50% ቅናሽ አድርገዋል። መልዕክቱ የተገኘው ከምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከል ኡማ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከጋዜጠኛ ሚልኪያስ ጌታቸው የተለካ ፦

በሀገራችን ብሎም በከተማችን በርካታ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እንዚህ ተቋማት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነጋዴዎች ብድር በማበደር የንግድ ስራቸወን አንዲያጠናክሩ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንዳላቸው እሙን ነው፡፡

የኮሮና ወረርሽን በሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ በሽታው በሰዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት አንዳለ ሆኖ የሰዎች እንቅስቃሴ በከፊል መቋረጥ አና በሌሎች የሽታው መተላለፊያ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች መካከለኛና አነስተኛ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ነጋዴዎቹ ይናገራሉ፡፡

ሆኖም ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ጋር የብድር ግንኙነት ያላቸው ነጋዴዎች በዚህ ስራቸው በተቀዛቀዘበት ወቅት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ነጋዴዎቹን ብድራቸውን እንዲከፍሉ ከፍተኛ ተፅእኖ አና አስገዳጅ ሁኔታዎችን እየጣሉብን ነው ይላሉ ከተለያዩ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር ግንኙነት ያላቸው ነጋዴዎች፡፡

ስራቸን በከፊልና በሙሉ የተቋረጠብን በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ለተበደርነው ብድር የምንከፍለው ቀርቶ እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን የምናስተዳድርበት በቂ ገቢ እያገኘን አይደለም።

ስለሆነም ይላሉ ነጋዴዎች መንግስት ችግራችንን በመረዳት ይህ ወቅት እስኪያልፍና ስራችንን እስክንጀምር ድረስ አበዳሪ ተቋማቱ የብድር መክፈያጊዜ ማራዘሚያ እንዲያደርጉልን ቢደረግ መልካም ነው ይላሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StayHomeSkillUp

ብሪቲሽ ካውንስል በላከልን መልዕክት የልጆች የእንግሊዝኛ ትምህርት የቴሌቪዥን ፕሮግራ። ፕሮግራም ከብሮድካስት አጋሮቹ መጀመሩን አሳውቆናል፡፡

ላለፉት ሶስት (3) ሳምንታት ወደ 26 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ማቋረጣቸው ይታወቃል።

ብሪትሽ ካውንስል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በሚሎዮኖች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ በቴሌቪዥን የሚሰራጭ የ20-30 ደቂቃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ያዘጋጀ ይገኛል።

የዚህ ፕሮግራም ይዘት የተወሰደው ማንም ሰው በቀጥታ ገብቶ በነጻ መማር ከሚችልበት የብሪትሽ ካውንስል ለርን ኢንግሊሽ ድህረ ገፅ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ፕሮገራሙ የሚተላለፈው በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ማሰራጫ ጣቢያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 እንደሆነ የተገለፀልን ሲሆን ፤ በኢትዮጲያ ልጆች ቴሌቪዥን ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2፡30 - 3፡00 እና በድጋሚ  ከ 10፡30 እስከ 11፡00 ይተላለፋል፡፡ ይህ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እድሜያቸው 6 እሰከ 11 አመት ለሆኑ ተማሪዎች የተዘጋጀ ነው፡፡
 
https://LearnEnglish.britishcouncil.org

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮ ቴሌኮም ላይ የቀረበ ቅሬታ!

ከኢትዮ ቴሌኮም ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ በገንዘባችን ከገዛነው ላይ ያለአግባብ እየቆረጠብን ነው ሲሉ የድርጅቱ ደንበኞች ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ተናገሩ፡፡

ደንበኞቹ ብዙዎቻችን ቤት በተቀመጥንበት በዚህ ሰዓት ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ ተቋሙ ገንዘባችንን ያለአግባብ እየቆረጠብን ነው ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ገንዘብ ካለአግባብ ከመቁረጥ ባለፈም የኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቆራረጠ እና ፈጣን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው አሰምተዋል፡፡

የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለደንበኞቻቸው የዋጋ ቅነሳ እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮምም እንደ ተቋም የዋጋ ቅነሳ ማድረግ ሲኖርበት ጭራሽ ያለ አግባብ ገንዘባችንን መቁረጡ አሳስዝኖናልም ብለውናል፡፡

ሬድዮ ጣቢያው ይህን 'ኢትዮ ቴሌኮም ያአግባብ ገንዘብ እየቆረጠብን ነው፣ የኢንተርኔት አገልግሎቱም ፈጣን አይደለም' የሚለው ቅሬታ ላይ ከኢትዮ ቴሌኮም ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ለጊዜው እንዳልተሳካለት አሳውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባደረገችው የጅምላ ምርመራ የተሳካ ውጤት ማስመዝገቧን ደቡብ አፍሪካ አስታውቃለች።

ሀገሪቷ ይህን ውጤት ያስነዘገበችው 10,000 የመስክ ሠራተኞችን በማሰማራት በአገር አቀፍ ደረጃ ቤት ለቤት ባደረገችው ምርመራ ነው ተብሏል።

ከፍተኛ የመንግስት አማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ በቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ እንዳመላከቱት ይህን መሰል አሰራር ከዚህ በፊት በሌሎች ሀገራት ያልተሞከረ ነው።

የመንግስት ዋና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አብዱል ከሪም እንደገለፁት ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰዎች ከቤታቸው እንዲቀመጡ መደረጉም ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል አበረታች ውጤት ተመዝግቦበታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሳዑዲ ዓረቢያ በአሁኑ ወቅት ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ሥራ መቀጠሏ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ሊያባባስ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ስጋቱን ገለጸ።

ሳዑዲ ዓረቢያ ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 2 ሺህ 870 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አዲስ አበባ መመለሷን የተመድ የፍልሰት ጉዳዮች ኤጀንሲ ያስታወቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ባለሥልጣንትም ይህንኑ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ፣ "ቀድመው ያልታቀዱ መጠነ-ሰፊ ፍልሰቶች የቫይረሱን ሥርጭት ቀጣይነት ያባብሳሉ፤ ስለሆነም መሰል ፍልሰቶች በጊዜያዊነት እንዲቆሙ እንጠይቃለን" ብለዋል።

የሳዑዲ የሚዲያ ባለሥልጣን በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጠት ለቀረበለት ጥያቄ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

ከስደት ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዳንዶቹ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለሮይተርስ ተናግረዋል፤ ትክክለኛ ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ግን አልገለጹም።

ከስደት ተመላሾች ሁሉ በተዘጋጀላቸው ለይቶ ማቆያዎች ውስጥ ለ14 ቀናት እንደሚቆዩ እና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚደረግላቸው በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሠራተኛ የሆኑት ዘውዱ አሰፋ ገልጸዋል።

ከስደት ተመላሾቹ በተጨናነቀ መልኩ ወደ ሀገር እንደሚገቡ የገለጹት አቶ ዘውዱ፣ "በአንድ በረራ ብቻ ከ300 እስከ 500 ስደተኞች አንድ ላይ ታጭቀው እየመጡ ነው፤ የተመላሽ ቁጥሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል" ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ተጨማሪ 8 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ስምንት (8) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት 447 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው በስምንቱ ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።  

ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 82 መድረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።    

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 447 የላብራቶሪ ምርመራ ስምንት (8) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቅላይ በሀገራችን በቫይረዱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ ሁለት (82) ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኤርትራዊ ከዩናይትድ ኪንግድደም የመጣና ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 2 - የ62 ኢትዮጵያዊና የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው።

ታማሚ 3 - የ16 ዓመት ኢትዮጵያዊትና የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 4 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊትና የአዲስ አበባ ነዋሪ የውጭ ሀገር ጉዞ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 5 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 6 - የ38 ዓመት እንግሊዛዊ ከዩናይትድ ኪንግደም የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 7 - የ37 ዓመት ሶማሊያዊ ከዩናይትድ ኪንግደም የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ታማሚ 8 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊና የአዲስ አበባ ነዋሪ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ የስራው ባህሪ ተጋላጭነት አለው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- መርካቶ ውስጥ የሚገኘው የአንፀባራቂ ኮከብ ሕንፃ ውስጥ ተከራይተው ለሚገኙ 76 ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበሩ የሚያዝያ ወር ወርሀዊ ኪራይ ነፃ ማድረጉን አክሲዮን ማህበሩ ገልጾልናል። በብር 504,730 ይደርሳል።

- የጀቡላኒ መሃል መርካቶ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የአንድ ወር የቤት ኪራይ (የሚያዚያ) ነፃ አድርጓል።

- ሀዋሳ 'ሰፈረ ሰላም' የሚገኘው አዲስ የገበያ ማዕከል የሁለት ወር የቤት ኪራይ ነፃ ማድረጉን አሳውቆናል። በገንዘብ 300,000 ብር ይደርሳል።

- አደይ አበባ የሚገኘው የማሜ ህንፃ ባለቤት 'መሃመድ አወል' የአንድ ወር የቤት ኪራይ 50 % ቀንሰዋል።

- ሄልዘር ቢዝነስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር በህንፃው ለሚገኙ ሁሉም ተከራዮች ቅናሽ በማድረግ የሁለት ወር (መጋቢት እና ሚያዚያ) የኪራይ ክፍያ ሙሉ በሙሉ እንደማያስከፍል አሳውቋል።

- ፌንድሺፕ የንግድ ማእከል ለ266 ተከራዮች የ3 ወር የኪራይ ክፍያ 50% ቅናሽ አድርጓል። መልዕክቱ ከኢ/ር ታከለ ኡማ የተገኘ ነው።

- 22 አከባቢ የሚገኘው KW የንግድ ማእከል ባለቤት ለ64 ለሚሆኑ ተከራዮች የአንድ ወር የኪራይ ክፍያ ነፃ አድርገዋል። መልዕክቱ ከኢ/ር ታከለ ኡማ የተገኘ ነው።

- Century Mall, የንግድ ማእከል 16.2 ሚልዮን ብር (የ3 ወራት ) የኪራይ ክፍያ 50 % ነፃ አድርገዋል። መልዕክቱ ከኢ/ር ታከለ ኡማ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዳፋ ሶፕ እና ዲተረጀንት በላከልን መልዕክት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚሰረገው ጥረት ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ አሳውቆናል።

በዚህም ፦

- 220,000 ብር የሚገመት ለፅዳት አገልግሎት የሚውል የዲተረጀንት ፓውደር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እገዛ አድርጓል።

- ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልል ለሚደረገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረገው ስራ 80,000 ብር የሚገመት የድርጅቱን ምርት እገዛ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዳሸን ባንክ በላከልን መግለጫ ሀገራዊ ኃላፊነቱን አሁንም አጠናክሮ እየተወጣ እንደሆነ ገልጾልናል ፦

- ባንኩ የኮሮና ቫይረስ ወደሀገራችን ከገባበት ዕለት አንስቶ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ምሳሌ የሆኑ በርካታ እርምጃዎችን በቀዳሚነት መውሰዱን አስታውሷል።

- ባንኩ ደንበኞቹንና ተጠቃሚዎቹን ሁሉ ያገናዘበ የታሪፍና የአገልግሎት ማሻሻያሰዎችን ተግባራዊ አድርጓል።

- ከዚህ ቀደም ወረርሽኙን ለመከላከል ለተቋቋመው ብሄራዊ ግብረ ኃይል 10,000,000 (አስር ሚሊዮን ብር) እገዛ አድርጓል።

- አሁን ደግሞ በብሄራዊ ደረጃ የሚከበሩ ህዝባዊ የደስታ በዓላትን አስመልክቶ ለወዳጆቹ ሁሉ ይልክ የነበረውን የእንኳን አደረሳችሁ ገፀ በረከት ፣ በሁሉም የባንኩ ደንበኞች ስም መታሰቢያነት ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከያ ብሄራዊ ድጋፍ ካሚቴ ለማስረከብ ወስኗል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ አባል ድርጅት የሆነው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ በላከልን መልዕክት ሀገራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጾልናል ፦

- የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረትን ለመደገፈ ያለመ ግምቱ ወደ  አምስት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር (5.5 ሚሊዮን ብር) የሆነ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ  ለተለያዩ የመንግስትና ምግባረ ሠናይ ድርጅቶች ድጋፍ አድርጓል።

- ከድጋፉ መካከል ሶስት ሚሊየን (3,000,000) የሚሆነው የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ቀይ-መስቀል ማህበር የተደረገ ሲሆን ቀሪው የሳኒታይዘርና ምግብ ድጋፍ ደግሞ ለአዲስ አበባ ፣ እንዲሁም ሌሎች የድርጅቱ ፋብሪካዎች ለሚገኙባቸው ለባህር-ዳር እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተደረገ ነው።  
 
- በድሬዳዋ እና ባህርዳር ከተማ አስተዳደሮች ደግሞ የምግብ እና የሳኒታይዘር ድጋፍ ተደርጓል።

- በተያያዘም ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ በዚህ ሳምንት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በሚገኙት የኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ የምርት ማከፋፈያዎች ማለትም በሃዋሳ ፣ በአዋሽ ሰባት እና በአዳማ ከተሞች ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ ድጋፎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ ያደርጋል።

https://telegra.ph/East-Africa-Bottling-04-14

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጤናችን ስንል እንጠንቀቅ!

በአንዳንድ አከባቢዎች ጭራሽ የቫይረሱ ስርጭት መጨምር የተረሳ ይመስላል። አንዳንድ አባቢዎች መኖሩ እንኳን የተወቀ አይመሰልም። መዘንጋቱ በጣም በዝቷል!

ከላይ የምትመለከቷቸው ከድሬዳዋና ሀዋሳ ከሚገኙ የቲክቫህ አባላት የተላኩልን ፎቶዎች ናቸው። ዛሬም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለው ሰልፍ አልቀነሰም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia