TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

ከነጩ ቤተ-መንግስት [ዋይት ሃውስ] ጥቂት ደቂቃዎች ርቀት ላይ ምትገኘው የሚሪላንድ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የመጀመሪያ በቫይረሱ [COVID-19] መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች በመገኘታቸው የክፍለ ግዛትዋ ሀገረ ገዢ ሌሪ ሆጋን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከታርጫ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦

"ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ የስታዲየሙን ንግግራቸውን ጨርሰው ከዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወጣጡ ህብረተሰብ ክፍል ጋር ውይይት ጀምረዋል።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ነዋሪዎች ውሃ በቁጠባ ተጠቀሙ ተብላችኃል!

ላለፉት 10 ቀናት በውሃ ማሰራጫ ጣቢያ ከኤሌትሪክ መቆራረጥ እና እንዲሁም ከሲስተም ጋር በተያያዘ ባጋጠመ ችግር የውሃ ስርጭት መቆራረጥ የተከሰተና ችግሩን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አሳውቋል።

በመሆኑም የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች 'የምታገኙትን ውሃ በቁጠባ እየተጠቀማችሁ በትግስት እንድትጠባበቁ' ሲል አሳስቧል። ተቋሙ ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮንትራት ሶስት!

በሞጆ - ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ግንባታ ከባቱ እስከ አርሲ ነጌሌ (የኮንትራት ሶሰት) የግንባታ ሂደት መጓተቱ ተገልጿል።

የመንገዱ ግንባታ ሂደት አሁን ላይ መድረስ ከነበረበት 37 በመቶ አፈፃፀሙ 6 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ መሆኑም ታውቋል።

የፕሮጀክቱ ምክትል አማካሪ የሆኑት ኢንጂነር ካሳሁን ጣሰው የመንገዱ ግንባታ የተጓተተው በግንባታ ግብዓት ፍቃድ ችግር፣ በወሰን ማስከበርና በወረዳ አስተዳደር ትብብር ማነስ መሆኑን ተናግረዋል።

ለግንባታው ግብዓት ለማግኘት ብቻ ከአንድ ዓመት በላይ እንደወሰደም ኢንጂነር ካሳሁን ገልጸዋል። ለመንገዱ ግንባታ የነበረውን አመለካከት ለመቀየር ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ መፍትሄ መምጣቱንም ተናግረዋል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ፦

በ4.8 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለውና 52 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአርሲ ነጌሌ ሀዋሳ መንገድ  የወሰን ማስከበር ችግር እንደገጠመው የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሉ ሆንግ ባኦ ለኢዜአ አስረድተዋል።

ከአዲስ አበባ እስከ ሀዋሳ የሚዘልቀው የኮንትራት አንድና ሁለት መንገዶች ግንባታ ግን በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የሥራ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።

ከዚህም ከሞጆ ሀዋሳ የሚዘልቀው የመጀመሪያው ኮንትራት 88 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት አምስት ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የመቂ-ባቱ 37 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ እስካሁን ከ79 በመቶ በላይ የተከናወነ ሲሆን፤ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጠናቀቅ የኮንትራት ሁለት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ፓርክ ጆንግ ገልጸዋል ። 

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

እንደ GulfNews.com ዘገባ በትላንትናው እለት በUAE 15 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች መገኘታቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ እና በሽታ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በቫይረሱ እንደተጠቁ የተነገረላቸው የተለያየ ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ተብሏል። በአሁን ሰዓት በUAE በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 45 መድረሱም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
UK ውስጥ በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞተ ሁለተኛው ሰው ትላንት ሪፖርት ተደርጓል። ሟቹ የ80 ዓመት አዛውንት እንደሆኑ ነው የተነገረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱ ተሰምቷል። ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ብቻ በኮሮና ቫይርስ 41 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እና ማእከላትን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ፣ በኢትዮጰያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ በየካ ኮተቤ ማእከል እና በአየር መንገድ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የሚቃኝ ነው።

በጉብኝ ላይ ከምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሊያ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባልደራስ፣ አብን፣ ኦነግ፣ ኦፌኮ ጥምረት ሊፈጥሩ ነው?

በዛሬው ዕለት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ እትም ላይ '13 የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምርት ለመፍጠር ምክክር ይዘዋል፤ ባልደራስ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ኦፌኮ ይገኙበታል' በሚል ይዞት የወጣው ዘገባ 'ነጭ ውሸት ነው' ሲሉ የባልደራሱ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል ገልፀዋል። ጋዜጣው ሀሰተኛ ዜና አሰራጭቷል፣ ማስተባበያ ይስጥ ይቅርታም ይጠይቅ ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች...

ዛሬ ጥዋት የሀዋሳ ከተማ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በከተማው የነዳጅ እጥረት ማጋጠሙን ሪፖርት አድርገዋል።

ላለፉት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ነዳጅ ለማግኘት ፈተና ሆኗል፤ በከተማው ረጃጅም የሞተር እና የመኪና ሰልፎች አሉ ብለዋል።

ነዳጅ ለማግኘት መጉላላት እና የስራ መስተጓጎል የየእለት የህይወታችን አንዱ ክፍል ከሆነም ሰንብቷል ሲሉ አማረዋል።

በተመሳሳይ ነዳጅ ለማግኘት በመሰለፍ በሚያጠፉት ጊዜ በአማካይ እስከ 150 ብር እንደሚያጡ በባሕር ዳር አብመድ ያነጋገራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ገልፀዋል፡፡

እናተስ የት ከተማ ይህ ችግር አጋጠማችሁ?

#AMMA #TikvahFamilyHawassa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጣልያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱ ተሰምቷል። ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ብቻ በኮሮና ቫይርስ 41 ሰዎች ሞተዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በነገራችን ላይ ጣሊያን ውስጥ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት የ49 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አሳውቋል፡፡ በጣሊያን በአንድ ቀን ይህን ያልህ ሰው በቫይረሱ ሲሞት ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሶስት ሰው ህይወት ጠፍቷል! ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው 'እናት ባንክ' የሚሰሩ ጥበቃዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የ3 ሰው ህይወት ማለፉን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ፖሊስ የማጣራት ስራ እየሰራ ይገኛል፤ በአካባቢው አምቡላንስ እየተመላለሰም እንደሆነ የቤተሰባችን አባላት አሳውቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው እናት ባንክ ዶ/ር ጀንበር ተፈራ ቦሌ ቅርንጫፍ ሲሰሩ በነበሩ ሦስት የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረ ለጊዜው መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ጸብ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት አካባቢ በሦስቱ የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረው ያለመግባባት አንደኛው የጥበቃ ሠራተኛ በያዘው ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ሁለት የጥበቃ ጓዶቹን ህይወት አጥፍቶ የራሱንም ህይወት አጥፍቷል፡፡ ሟቾች ዕድሜያቸው ከ30 አስከ 35 ዓመት የሚገመቱ ጎልማሶች ሲሆኑ የጉዳዩን መነሻ እየተጣራ ይገኛል።

በግለሰቦች መካከል ያለመግባባት ሲፈጠር በምክክርና በንግግር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ የሚገባቸው ሆኖ ከአቅም በላይ ከሆነ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ጉዳዩን ማሳወቅ እንጂ ወንጀል ውስጥ መግባት ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን ኮሚሽኑ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

[Addis Ababa Police Commission]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር፦

ለአባል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዛሬው እለት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል። በዚህም ስልጠና ላይ የማህበሩ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሞላ ፀጋዬ፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ኤባ ሚጀና ፣ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጅንሲ(HERQA) የእውቅናና ፍቃድ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብይ ተገኝተው ስልጠናውን ሲሰጡ ነበር።

በዚህም መሰረት፦

-በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአገር አቀፍ የትምህርት ማሻሻያ ሚና

-እውቅና እና የእውቅና ፍቃድ እንዲሁም የግል ትምህርት ተቋማትን ከማዘመን እና የአጠቃላይ ሀገራዊ አስተዋፅኦውን ከማጠናከር በተሻለ መልኩ ማስኬድ ስለሚቻልባቸው አጠቃላይ ግንዛቤዎች

- ተቋም ተኮር ኦዲትና የባለድርሻ አካላት (የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር፣ ትምህርት ሚ/ር፣ የአግባብነትና ጥራት ኤጀንሲን ባካተተ መልኩ) ሚና እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ሲመክር ነበር።

#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የነዳጅ ስለፍ...

የነዳጅ ሰልፍ ምን ባህር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች ብቻ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥም አለ፤ ስራ አቁመን ለነዳጅ የምንሰለፍበት ቀን ብዙ ነው ሲሉ የቲክቫህ አ/አ ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገዋል።

የአርባ ምንጭ፣ ዲላ ቲክቫህ ቤተሰቦችም ለነዳጅ መሰልፍ እየተደጋገመ መሆኑ አስገንዝበዋል። በዚህም በከፍተኛ ደረጃ የስራ ሰዓታቸውን እየተሻማ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

አንድ የባጃጅ ሹፌር የሆነ የኮምቦልቻ ቤተሰባችን ደግሞ እሱ ባለበት ከተማ ይሄ ነገር በተደጋጋሚ እንደሚከሰት ገልጿል።

'ስሜቱን አውቀዋለሁ ሰልፋ በጣም ስለሚያስጠላኝና የስራ ሰአቴን ስለሚሻማኝ ሌሊት 10:00 ሰአት እንቅልፌን አሸንፌ እነሳለሁ ነዳጅ ለመቅዳት፤ እሚገርመው ነገር ግን በዚያ ሌሊት ሄጄ እንኳን ሰልፉ እንዳለ ነው እና ይሄ ነገር መፍትሄ ቢሰጠው ባይ ነኝ' ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ET302 መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች የፊታችን ማክሰኞ እዚሁ ሀገራችን ላይ በሚደረግ የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ለመታደም ይሰባሰባሉ ተብሏል። #EsheteBekele @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከአንድ ዓመት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ምክንያት የአውሮፕላኑ የዲዛይን ችግር እንደሆነ መርማሪዎች ለአሜሪካ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ያዘጋጁት የአደጋው ረቂቅ ሪፖርት አመለከተ።

ሮይተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ በረቂቅ ሪፖርቱ ላይ ቅሬታ ወይም እንዲለወጥ የሚያቀርበው ሃሳብ ካለው ዕድል እንደተሰጠው፤ ሪፖርቱ ይፋ ስላልተደረገ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሰዎች ተናግረዋል።

የቦርዱ ቃል አቀባይ ኤሪክ ዌይስ ጊዜያዊው ረቂቅ ሪፖርትን እንደተቀበሉ ቢገልጹም ድርጅታቸው ለውጥ እንዲደረግ ይጠቅ እንደሆነ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቦይንግ ሪፖርቱን በተመለከተ ምላሹ ምን እንደሆነ በሮይተርስ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

ረቂቅ ሪፖርቱን ቀድሞ ይፋ ያደረገው ብሉምበርግ ኒውስ እንዳለው የሪፖርቱ ማጠቃለያ ስለኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ የበረራ ሰራተኞቹ አሰራርን በተመለከተ ውስን ወይም ምንም ነገር ባለማለቱ በምርመራው ላይ በተሳተፉ አንዳንድ ሰዎች ዘንድ ጥያቄን አስነስቷል።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ2 ሰው ህይወት የቀጠፈው የነቀምቴው እሳት አደጋ!

በነቀምቴ ከተማ በኬጀሞ በተባለ መንደር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከስቶ በነበረ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ከባድ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ ዋጋሪ ለኤፍ ቢ ሲ ከተናገሩት፦

- የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ ነው የደረሰው። ፖሊስ የእሳት አደጋው መነሻ ምናልባትም የኤሌከትሪክ  መቀጣጠል ሊሆን እንደሚችል መገመቱን እና ነገር ግን በቤት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ቤንዚን ቃጠሎውን አባብሶታል።

- በአደጋው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ህይወታቸው አልፏል፤ የአካባቢው ነዋሪ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ርብርብ የሁለት ሰዎችን ህይወት መታደግ ተችሏል። እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በነቀምቴ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ በሽታ [COVID-19] መስፋፋት “በእጅጉ ያሳስባል” ያሉ ሲሆን ሁሉም ሀገራት ለበሽታው ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፖላንድ ትላንት ምሽት ብቻ 4 በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ግለሰቦች በሀገሯ መኖራቸውን አረጋግጣለች። ይህም በፖላንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር ወደ 6 ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

• ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛውን የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ዛሬ ይፋ አድርጋለች።

• ማልታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ በሀገሯ መኖሩን ይፋ አድርጋለች።

• ትላንት በኔዘርላንድ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በጣሊያን የሴሪ አ እግር ኳስ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ውድድሮች ለአንድ ወር ያህል ለተመልካች ዝግ ሆነው እንደሚካሄዱ ተገልጿል። በተጨማሪም መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ይህንን በሽታ ለመግታት ሲል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ10 ቀናት እንዲዘጉ አዟል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia