TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የምርመራ_ሪፖርት

ፍትህ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ምርመራንና የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ምርመራው የተካሄደው በህወሃት ተይዘው በነበሩና በኃላም ነጻ በወጡ አካባቢዎች ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ፦
- የ96 ሰዎች ሞት
- 53 የአካል ጉዳት
- 29 አስገድዶ መደፈር
- 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ
- 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግልና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት ፈፅሟል ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች በድምሩ፦
- የ129 ሰዎች ሞት
- የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት
- በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገልጿል።

በአፋር ክልል ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት፦
- የ240 ሰዎች ሞት
- 42 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅሟል።

በሁለቱም ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ንብረት ላይ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት በስፋት መድረሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

እስከ አሁን በተደረሰበት ግን ሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች መፈጸማቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል። #አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ይደረጋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች ፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን…
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
3.8 MB
#የምርመራ_ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (EHRC) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (OHCHR) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

የEHRC እና OHCHR የጋራ ሪፖርት በትግራይ ግጭት ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያሳያል።

* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#የምርመራ_ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ በጥር 25/ 2015 ዓ.ም. በዋናነት #የሀገር_ውስጥ_ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ በተፈጸመ ጥቃት በሰው ሕይወት ፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በተመለከተ ከጥር 25 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ምስክሮችን፣ የመንግሥት አካላትን እና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ምርመራ አድርጓል፡፡

ኮሚሽኑ የላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#የምርመራ_ሪፖርት

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ፤ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " አኖ ከተማ በጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋናነት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ይህ በተመለከተ #ኢሰመኮ ምርመራ አድርጓል።

ምርመራውን በተመለከተ ከላከልን መግለጫ ፦

- ጥር 25/ 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የወታደር ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) መሆናቸው በነዋሪዎች የተገለጹ ታጣቂዎች በ3 አቅጣጫ ወደ " አኖ ከተማ " መግባታቸውን፤ በመቀጠል በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የሆነ የተኩስ ድምፅ መሰማት መጀመሩን እና የሲቪል ሰዎች ግድያና የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት መድረሱ ታውቋል።

- በጥቃቱ ዋና ኢላማ የተደረጉት ከ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው።

- በታጣቂ ቡድኑ በተፈጸመ ጥቃት አንድ የክልል የሥራ ኃላፊ ከነሾፌሩ፣ የከተማ ፖሊስ እና የቀበሌ ሚሊሻ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ ሃምሳ (50) ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚም መካከል 42 ተጎጂዎች በተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡

- ከሟቾች መካከል አራት #ሴቶች እና ሦስት #ሕፃናት ናቸው፡፡

- ታጣቂዎቹ ‘ሰኞ ገበያ’ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤት ለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል፡፡

- በከተማዋ ውስጥ የሚገኝ እና ቀደም ሲል የቀበሌ አስተዳደር ንብረት የነበረና ወደ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት ተፈናቃዮች መጠለያነት ተቀይሮ በማገልገል ላይ ይገኝ የነበረ ግቢ ውስጥ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት፤ በግቢው ውስጥ የነበሩ ማምለጥ ያልቻሉ ወንድ ተፈናቃዮችን መርጠው ገድለዋል። ከእነዚህም መካከል ከተገደሉ በኋላ #ሬሳቸው_በእሳት የተቃጠለ ሰዎች አሉ፡፡ በጥቃቱ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ሲሆን መጠለያውም በጊዜያዊነት ተዘግቶ ነበር፡፡

- የሟቾችን አስከሬን ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት እና በማግስቱ የአካባቢው ማኅበረሰብ መቅበሩን የተጎጂዎች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

- 8 ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

- በተፈጸመው ጥቃት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግለሰቦች የንግድ መደብሮች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አኖ ቅርንጫፍ እና ሌሎች ተቋማት መጠነ ሰፊ ዘረፋ እና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ 

ሙሉ ሪፖርትhttps://publielectoral.lat/c/1370522004/23484

@tikvahethiopia