TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
95% ተማሪዎች ወደሀገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ...

በቻይና ውሃን ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መካከል 95 በመቶ ያህሉ ወደ ሀገሩ መመለስ እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ይህ የታወቀዉ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ በቻይና ውሃን ከተማ ከሚገኘው የኢትዮጵያውን ተማሪዎች ህብረት ጋር ባካሄደዉ ቃለ-ምልልስ ነዉ።

በዉሃን ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመጓጓዣ ወጪያቸውን ራሳቸው ሸፍነው ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተብሏል።

ተማሪዎቹ ይህን ለማድረግ ግን አሁንም የሀገራቸው ትብብር እንደሚስፈልጋቸዉ እየገለፁ ነዉ። ተማሪዎቹ አስፈላጊውን የመውጫ ፍቃድ መንግሥታቸው እንዲያመቻችቸው ይሻሉ። 

በሌላ በኩል ተማሪዎቹ ከሚኖሩበት ቤት መውጣት እና ከሰው ጋር መገናኘት አለመቻላቸው ሌላው ጭንቀታቸዉ መሆኑም ታዉቋል።

[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ቴሌቪዝን ቀርበው ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሀገራቸውና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረውና ለአንድ ዓመት ተኩል የዘለቀው መዳጃዊ ግንኙነት መልካም ጅምር እንደሆነ አመልክተዋል። የተከናወነ ብዙ ሥራ ግን አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሁለቱ ሀገሮች መካከል ለቆዩት ችግሮች ተጠያቂ ያደረጉት በስም የፈጠሯቸውን የውጭ ኃይሎች ሲሆን አሁን እየተጓተቱ ላሉ ኝኙነቶች እነዚያኑ ኃይሎችና የህወሓትን መሪዎችን ከሰዋል።

[VOICE OF AMERICA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን አሉ?

- ባለፈው አንድ አመት ተኩል ትልቅ ነገሮች ባይሰራም እንደ አንድ የለውጡ መነሻ ጥሩ ጅማሬ እንደሆነ ተናግረዋል።

- በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ላለፉት 80 ዓመታት የተለያዩ ኢትዮጵያ ላይ በነበሩ ስርዓቶች ተደጋጋሚ ጦርነትና ግጭት ሲፈጠር እንደነበር ጠቅሰው መነሻው ምንድነው በሚለው ላይ ደግሞ የውጭ ኃይሎች በአካባቢው ሰላም እንዳይኖር፣ ሁለቱ ሀገሮች ተስማምተው እንዳይኖሩ እንቅፋት በመፍጠር ከተለያዩ ስርዓቶች ጋር ስምምነት በማድረግ ጉዳዩን እዚህ ደረጃ ላይ አድርሰውታል ብለዋል።

- ላለፉት 20 ዓመታት በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው የድንበር ግጭት ዋነኛ መነሻው ከውጭ ኃይሎችና በ20 ዓመቱ ወቅት ስልጣን ላይ የነበረው በህወሓት የተፈጠረ ችግር ነው።

- በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት ለመቀልበስ አሁንም በየጊዜው የተለያዩ ችግሮች እየተፈጠሩ፤ የተለያዩ አዳዲስ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ግንኙነቱን ለማደናቀፍ እየተሞከረ እንደሆነ ነው የጠቀሱት።

- በፕሬዘዳንቱ አገላለፅ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን ይመራ የነበረው የህወሓት መንግስት አሁንም ድረስ ዶ/ር አብይ ስልጣን ከተረከቡበት ሰዓት ጀምረው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ድንበሩ እንደሚሰመርና ሰላምም መተግበር እንዳለበት ቃል ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የህወሓት ድርጅት ይህንን ለማደናቀፍ እየሰራ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያና በኤርትራ የተጀመረውን ሰላም ወደ ሌላ ደረጃ እንዳይቀጥል እንደትልቅ እንቅፋት እንደሆነ ነው የገለፁት።

More https://telegra.ph/TIKVAH-02-08

[VOICE OF AMERICA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ጠባቂዎቼ ከእኔ ጋር ይቆያሉ" - አቶ ጃዋር ሞሐመድ

በመንግሥት ተመድበው ለረጅም ጊዜ ለጃዋር ሞሐመድ ጥበቃ ሲያደርጉ የነበሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት በእራሳቸው ፈቃድ ከእርሱ ጋር ለመቆየት መወሰናቸው ተነገረ።

በቅርቡ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) በመቀላቀል ከመብት ተሟጋችነት ወደ ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የገባው ጃዋር ሞሐመድ ለቢቢሲ እንደተናገረው መንግሥት የመደባቸውን ጠባቂዎቹን እንደሚያነሳ እንዳሳወቀውና ይህንንም ተከትሎ ጠባቂዎቹ ከመደበኛ ሥራቸው ይልቅ "እኔ ጋር መቅረትን መርጠዋል" ብሏል።

አቶ ጃዋር ለቢቢሲ እንደተናገረው የጥበቃዎቹን መነሳት በተመለከተ ከፌደራል ፖሊስ ኮማንደር ጋር መነጋገሩንና አባላቱ ለስልጠና እንደሚፈለጉና ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ መጠየቁን አመልክቷል።

ይህንንም ተከትሎ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው ጋር በተነጋገሩበት ጊዜ የእሱ ብቻ ሳይሆን በመንግሥት ጥበቃ የተመደበላቸው ሰዎች ጠባቂዎችን ማንሳት እንደጀመሩና የእሱንም ጥበቃዎች እንደሚያነሱ እንደነገሩት ገልጿል።

ይህ ከመሆኑ ቀደም ብሎ ለረጅም ጊዜ አብረውት ከቆዩት ጠባቂዎቹ ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ተነጋግሮ እንደነበር የሚናገረው አቶ ጃዋር "አነሱም ወደ ፌደራል ፖሊስ መመለስ እንደማይፈልጉና ከእኔ ጋር መቆየት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል። "ምክንያታቸውም ስምና ፎቷቸው በስፋት ሲሰራጭ ስለነበር ለደህንነታቸው በመስጋት እንደሆነ ነግረውኛል በማለት አቶ ጃዋር መሃመድ ተናግሯል።

[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው ክሶች ላይ መስክረውብኛል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት አባረሩ።

ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀምና የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በምክር ቤት ከታየ በኋላ ነጻ መባላቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ሂደት ምስክር በመሆን ስሜን አጥፍተዋል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከስራ አሰናብተዋል።

በዚህም በአውሮፓ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር ጎርደን ሰንድላንድ እና በፀጥታው ምክር ቤት የዩክሬንን ጉዳይ የሚከታተሉትን ሌተናል ኮሎኔል አሌክሳንድር ቪንድማንም ከኋይት ሀውስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥተዋቸዋል ነው የተባለው።

[ኤፍ ቢ ሲ፣ ቢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ...

ከድሬዳዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ላስ ዴሬ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ በ5 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ7 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በዚህ አደጋ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር በንብረት ላይም ጉዳት ማጋጠሙ ነው የተነገረው።

አደጋው ያጋጠመው በ3 ሚኒባስ እና በ2 ትራከር መኪኖች መሆኑን ፓሊስ ማስታወቁን ከድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

[ድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን]
@tikvahethiopiaBot @tikvhhethiopia
#UPDATE

ካናዳ በበርካታ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና ልዑካን ቡድናቸውን ዛሬ ማለዳ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PASSPORT

ባልተፈቀደ አግባብ የኢትዮጵያን ፓስፖርት በእጃቸው ያስገቡ 29 የውጭ ሀገር ዜጎች ፓስፖርቶችን እንደተሰረዘ የኢምግሬሽን ሃላፊዎች ማስታወቃቸውን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል፡፡

ፓስፖርት በገንዘብ የገዙ 3 የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር ተባረዋል፤ ሌላኛው ደሞ ሊወጣ ሲል ታስሯል፡፡ ፓስፖርት በሕ ወጥ መንገድ በመስጠት የተጠረጠረ የተቋሙ ሠራተኛ ታስሯል፡፡

[ሸገር ኤፍ ኤም፣ ዋዜማ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#የካቲት11

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የተመሰረተበት የየካቲት 11 ክብረ በዓል ላይ ከ150,000 በላይ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሏል። በበዓሉ ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን ለማስተናገድና በዓሉን በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የህወሓት ምስረታና የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል በደደቢት በረሃ የተመሰረተበት የካቲት 11 ዘንድሮ ለ45ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

- የካቲት 11 በመቐለ ከተማ በክልል ደረጃ 150,000 ታዳሚ በሚገኝበት ይከበራል።

- መቐለ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገች ትገኛለች።

- ከተማይቱ በኢትዮጵያ ባንዲራ፣ በትግራይ ክልል ባንዲራ፣ በህወሓት የትግል አርማ ደምቃለች። የተለያዩ በዓሉን የሚገልፁ ባነሮችም በተለያዩ ቦታዎች ተሰቅለዋል።

- ለካርኒቫሎች፣ ለተለያዩ ትርኢቶች፣ ኤግዝቢሽንና አጠቃላይ ለበዓሉ የሚደረጉ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
“አንድ ዕድል ነው ያለን! በሽታው [ኮሮና ቫይረስ] ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገባ መከላከል ካልቻልን ፤ አንዴ ይሄ ሕመም ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባ የጤና ተቋማቱ አቅቅም የተሟላ ባለመሆኑ - ‘ከገባ በኋላ እንሰራለን’ የሚል ሃሳብ እዚህ ላይ የሚሰራ አይደለም።” - ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ
.
.
“ይሄ በሽታ እየጨመረ መሄዱና የአንዳንድ አገሮች ደግሞ ያን የመቋቋም አቅም ጠንካራ አለመሆን በተለይ ለእንደ እኛ ዓይነት አገሮች አሳሳቢ ነው።” - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

#VOA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
13 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

በትላንትናው ዕለት ምሽት 13 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ማዋሉን በሃላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡

በሃላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዋና አዛዥ ሳጅን ሹክራላ ሸህ ሱጋቶ ከገለፁት የወሰድነው፦

- የጦር መዳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው በቀን 29/05/2012 ዓም ማለትም በትላንትናው ምሽት 2፡30 ገደማ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 15967 አዲስ አበባ የሆነ ሙዝ የጫነ አይሱዙ መኪና ነው።

- መኪናው መነሻውን አርባ ምንጭ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለ በሃላባ ዞን ዌራ ወረዳ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ጠንከር ያለ ፍተሻ ነው መሳሪያዎቹ የተያዙት።

- የተያዙት መሳሪያዎሽ በሞዴል M1 ሁለት መሳሪያ፥ ppsh ሁለት መሳሪያ እና 9 መንቶፍ መሳሪያ በድምሩ 13 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ፓንጎሊን የኮሮና ቫይረስ አስተላላፊ ያሆን?

ገዳይ የሆነ የኮሮና ቫይረስ ከለሊት ወፍ ወደ ሰው የተላለፈው በኢሲያ ውስጥ ለምግብነትና ለመድሃኒትነት በሚሸጠው ፓንጎሊን በሚባል አጥቢ እንስሳ ሊሆን እንደሚችል ተመራርማሪዎች መግለፃቸው ተሰምቷል። ይህ ግኝት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትልቅ ጥቅም እንዳለው የደቡብ ቻይና የግብርና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናግረዋል።

[ስካይ ኒውስ፣ አል-ኣይን]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

የምርጫ አስፈጻሚዎች ከፖለቲካ ተሳትፎ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆኑ ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ ለአገር አቀፉ ምርጫ ከ250 ሺህ በላይ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ለምርጫው በመላ አገሪቷ ከ48 ሺህ 500 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያም እስከ አምስት አስፈጻሚ እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሮ ብዙወርቅ ክተት የተናገሩት፦

- መጪውን ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአስፈጻሚዎች ምልመላ አካሔድ ዋነኛው ነው።

- ቦርዱ አስፈጻሚዎች ለመመልመል የምርጫ ህጉ በሚያዘው መሰረት በመስፈርቶቹ ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር ይሰራል።

- ቀደም ሲል ምርጫ አስፈጻሚዎች በወረዳ አስተዳደር በኩሉ ይጠቆሙ ነበር፤ “በዘንድሮ ምርጫ ይህን አሰራር ለመቀየር እየተሰራ ነው”

- ማስታወቂያ በማውጣት የምርጫ ክልል ኃላፊዎች ቅጥር ተፈፅሟል። ይህም ውድድርና ብቃትን መሰረት አድርጎ ከመከናወኑ ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎችም አስተያየት ሰጥተውበታል።

- በቦርዱ በኩል የምርጫ አስፈጻሚዎችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ተመልምለው ስልጠና የሚወስዱበት መንገድ እየተመቻቸ ነው።

- አዲሱ የምርጫ ሕግ በሚያዘው መሰረት በአሁኑ ወቅት 79 ፓርቲዎች ዳግም ምዝገባ አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል 32 በአገር አቀፍ ደረጃ፣ 47 ደግሞ በክልል ደረጃ የተመዘገቡ ናቸው።

- ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ የዋሉ ምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር፣ ስያሜና ቦታ እንዲሁም አሁን ያሉበት ሁኔታ ላይ እየተደረገ ያለው ጥናት እየጠተናቀቀ ነው።

- ከዚህ ጎን ለጎን እየተካሔደ ያለው አጠቃላይ ሪፎርም በቦርዱ ላይ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ምርጫውን በተሻለ ለማካሔድ የሚያግዝ ነው።

[ወይዘሮ ብዙወርቅ ክተት ለኢዜአ ከተናገሩት]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ኢትዮጵያ በዚህ አመት ለምታካሂደው ምርጫ ወደ ሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያስገቡ ሁኔታዎችን ከወዲሁ እንድትፈትሽ የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊና ሰዎች መብት ኮሚሽን መክሯል።

ዶክተር ሰለሞን አየለ የተናገሩት፦

- በተለያየ ደረጃ የሚከሰት ግጭት የሰብአዊ መብት ጥሰት ያስከትላል። እንደተፈጠረው የሰብአዊ መብት ጥሰትና እንዳስከተለው ችግር መፍትሄውም በዛው ልክ መቃኘት አለበት።

- በምርጫና በጦርነት ወቅት የሚከሰት የሰብአዊ መብት ቀውስ መፍትሄ የሚቃኝበት ሁኔታ የተለያየ መሆን አለበት።

- በምርጫ ወቅት በሰብአዊ መብት ዙሪያ የሚነሱ የመናገር፣ የመምረጥ፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ወሳኝ ናቸው።

- ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ፣ ለዜጎች መምረጥ የሚያስችላቸውን ሁኔታ ማመቻቸትና ከጥቃት መከላከል የሚመከታቸው አካላት ሃላፊነት ነው።

- በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ዜጎች ላይ ሃይል መጠቀም፣ ሰልፍ እንዳይደረግ መከልከልና በነጻነት የመናገር መብትን መከልከል በምርጫ ወቅት የሚከሰት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ናቸው።

- በኢትዮጵጰያ በነሃሴ ወር ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ ላይ ወደ ሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያስገቡ ሁኔታዎች ከወዲሁ እንዲፈቱ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

- ወደ ግጭትና አለመግባባት ከዛም አልፎ ወደ ሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያመሩ ሁኔታዎች ከምርጫ በፊት ካልተፈቱ ችግሮቹ በምርጫ መድረክ ላይ በመንጸባረቅ ዜጎች እርስ በርስ የሚጋጩበት ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

[ዶክተር ሰለሞን አየለ ለኢዜአ ከተናገሩት]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#nCoV #coronavirus

Nagummaa Nyaataa Eeguu Amaleeffadhaa!

- Haaduu fi gabatee irratti kukkuttan kan foon dheedhii fi kan nyaata bilchaatanii adda baasuun ittti fayyadamaa.

- Foon dheedhii yoo tuqxan nyaata bilchaate otoo him tuqiin harka kessan dhiqadhaa.

#SHARE

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#nCoV #coronavirus

ዘውትር የሚመገቡትን ምግብ ደህንነት ይጠብቁ!

- ለጥሬ ስጋና ለሚበስሉ ምግቦች የሚጠቀሙበትን ቢላዋና መክተፊያ ይለዩ።

- በጥሬ እና በበሰለ ምግብ አዘገጃጀት መካከል እጅዎን መታጠብዎን አይዘንጉ።

መልዕክቱን ለሚያውቁት ሁሉ ያጋሩ!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#HAWASSA

የሜሪ ጆይ 25ኛ አመት የብር ኢዩቤልዩ በዓል በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ ተከብሮ ውሏል። በክብረ በዓሉ ላይ ሲስተር ዘቢደር፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ዶ/ር ወዳጄነ ማሃረነ፣ ወጣት ገጣሚያን እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia