TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያየ!

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።

በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከትናንትናው እለት ጀምሮ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራውና የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ የተካተተበት ልኡኩ በዛሬው እለትም ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ እያደረገ ያለው ጉብኝት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል።

(FBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
እንኳን ደስ አለን 500,000 ደረሰናል!

ውድ ቤተሰቦቻችን ለዚህ መድረሳችን ትልቁን ድርሻ የምትወስዱት እናተ ናችሁ። ጥላቻ የምትፀየፉ፣ ስድብን የምትፀየፉ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የምትጨነቁ፣ ለሀገር ሰላም እንቅልፍ የምታጡ፣ ሰው የምታከብሩ፣ ስሜታዊነት የማየጠቃችሁ፣ እርቆ አሳቢ የሆናችሁ፣ መረጀዎችን አመዛዝናችሁ የምትቀበሉ፣ የተቸገሩትን የምትደግፉ፣ ሁሌም ለመልካም ስራ ቀድማችሁ የምትገኙ ውድ፣ እንቁ የሀገራችን ዜጎች ናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ለናት ተነግሮ፣ ተፅፎ የማያልቅ ክብር አለን!

በያካባቢያችሁ ያሉትን ሁኔታዎች በመሳወቅ፣ መረጃዎች ሳትደብቁ የምትገልፁ፣ በመንግስት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ ስራዎች አፍረጥርጣችሁ የምትገልፁ፣ በዚህ ሀገር በየትኛውም ቦታ በክቡር የሰው ልጅ ላይ የሚፈፀሙ ብደሎችን ሳትፈሩ የምትጠቁሙ፣ አንደኛው ሌላኛው አከባቢ ስላለው ጉዳይ እውነቱን እንዲያውቅ በማድረግ፣

ሀሰተኛ ነገር እንዲህ በበዛበት ሰዓት በማስረጃ እያስደገፈችሁ የሚመለከታቸው ሰዎች እንዲደርሳቸው በማድረግ ትልቅ ተግባር እየፈፀማችሁ ነው።

ዛሬ በኛ መብዛት፣ በናተ ተፅኖ ፈጣሪነት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ገፁን እየተከታተሉ እንደሆነ፣ የሚተላለፉ ጥቆማዎችን እየተመለከቱ መፍትሄ ለመስጠት እየሰሩ እንደሆነ እናምናለን።

እኛ መረጀዎችን ከተለያዩ ገፆች እየሰበሰብን ስናቀርብላችሁ በተለይ በፌስቡክ ላይ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን፣ የሰው ክብር የሚነኩ ስድቦችን፣ ማንነት ላይ የነጣጠሩ እና ሰዎችን ለግጭት ከሚገፈፉ መልዕክቶችን በጥቂቱም ቢሆን እድትርቁልን ለማድረግ እየሞከርን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የስራ እንዲሁም የትምህርት ሰዓታችሁ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይባክን ሚዛናዊ መረጃዎችን ከተለያዩ እውቅና ካላቸው ገፆች መርጠን እዚህ እየሰበሰብንላችሁ ነው።

በተጨማሪ...

በጋዜጠኝነት ስራቸው ክብር ያገኙ፤ ሞያቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለህዝብ አብዝተው የሚጨነቁ፣ ሚዛናዊ፣ ለሀቅ የቆሞ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የተመረጡ መረጃዎችን እንዲያቀርቡልን በትብብር እየሰረን ነው ለምሳሌ፦ (ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00-1:00 - ኤልያስ መሰረት ታዬ)

በቅርቡ ሌሎች ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የቤተሰቡ አባላት መረጃ በማድረስ ከአንባቢነት ወደ ፀሃፊነት እንዲመጡ የምናደርግ ይሆናል።

ከ500,000 ለምትበልጡ ለቤተሰባችን አባላት ከፍተኛ ክብር አለን፤ ሁላችንም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ነን! ያንተ ችግር የኔ ነው። ያንተ ደስታ የኔ ነው። አብሮነታችን ቤተሰባዊ ስሜታችን ነገም ይቀጥላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጀርባው ያለው የሚደግፈው፣ የሚግዘው፣ ዋጋ የሚከፍልለት፣ ስለእውነት የሚቆረቆርለት አካል ዛሬ 500,000 ደርሷል!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የግለሰብ፣ የግል ድርጅት፣ የመንግስት ወይም የሌላ አካል አይደለም የቲክቫህ ባለቤቶች 500,000 የምትልቁት ቤተሰቦቻችን ናችሁ፤ ከየትኛውም አካል ጥገኛ ሳንሆን እርስ በእርሳችን ተደጋግፈን ብሩህ ጊዜ እስኪመጠ እንሰራለን። ይህ ገፅ የግለሰቦች ፍላጎት ማንፀባረቂያ፣ የግለሠቦች እውቅና መገንቢያ፣ አንድ ሰው አመለካከት መጫኛ አይደለም 500,000 የተከበሩ ዜጎች የሚገኙበት እንዚህ ላይ የምናስተባብረው ሰዎችም እንደ አንድ የቤተሰቡ አባላይ ከማንም ባልተለየ መልኩ ድምፃችን የሚሰማበት ብቻ ነው።

ምስጋና!

•ለመላው ክቡር ሆናችሁ ቤተሰቦቻችን፣ እውነተኛ ጉዳዮች በማስረጃ አስደግፋችሁ በማሳወቅ፣ ሁሌም ለእገዛ ቀድማችሁ ለምትገኙ፣ ጥቆማዎችን የምታደርሱ፣ ሚዲያዎች ሽፋን የማይሰጧቸውን ጉዳዮችን የምታሳውቁ፣ የሚሰራጩ መረጃዎች የምታርሙ፣ የምታስተካክሉ፣ ከስሜታዊነት ርቃችሁ የምትተቹ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ!

•በዚህ ፈታኝ ሰዓት ጥቂት ለሆናችሁ ሀቀኛ፣ እውነተኛ፣ ተማኝ፣ የሙያ ስነምግባራችሁ ጥንቅቃችሁ ለምታውቁ፣ ጊዜያችሁን ለሀገር ሰላም እየሰጣችሁ ላላችሁ ጋዜጠኞች (በተለይም የቤተሰባችን አባላት)

•ከስሜታዊነት ርቃችሁ እያመዛዘናችሁ ለሀገር ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን ለምታቀርቡ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ላላችሁ ወጣቶች!

•ከድክመታችሁ ጋር ግል እና የመንግስት ሚዲያዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች!

•በድጋሚ ለናተ ለጨዋዎቹ፣ በሀገራችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ለምታደርጉን ሰው አክባሪዎች 500,000 ቤተሰቦች!

ምስጋና በቅርቡ በቤተሰባችን ከአንባቢነት ወደ ፀሃፊነት ለተሸጋገሩት፦

(@tikvahethiopia የአሶሼትድ ፕሬሱ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ታዬ)

(@tikvahethsport ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍሬው አስራት እንዲሁም ጢሞትዮስ ባዬ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde
500,000 + Tikvah Family !

Pic. Elias Meseret

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ2019 የፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ ቀን “ማኅበረሰቡ የለውጥ አቅም ነው” በሚል መሪ ቃል በዓለምቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡

PHOTO:ሮይተርስ

#WAD2019

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CocaCola

ኮካ ኮላ ኩባንያ መንግሥት ለሽያጭ ከሚያቀርባቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል የተወሰኑትን ለመግዛት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የግዥ ፍላጎቱን ለመንግሥት በማስታወቅ የጨረታ ሒደቱ ይፋ የሚደረግበትን ጊዜ እየተጠባበቀ መሆኑ ገልጿል፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
«መንግሥት ስለ ቫይረሱ አስገንዝቦ ተስፋ ያለዉ ትዉልድን ካላነፀ ማንን ሊመራ ነዉ» - ቫይረሱን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች

አሳሳቢዉ የኤድስ ስርጭት!

በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ፀረ-ስርጭት ቀንን መጠበቅ የለብንም ሲሉ ቫይረሱን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ገለፁ።

«የኤድስ ስርጭትን ለመከላከል በየዓመቱ የፀረ ኤድስ ቀን በሚታሰብባት በኢትዮጵያ ትኩረቱ ከርዳታ ድርጅቶች በሚገኘው ገንዘብ ላይ እንጂ የኤድስን ስርጭት ለመግታት እና ግንዛቤ ማስጨበጡ ላይ አይደለም» ሲሉ አንድ ከኤድስ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ተናግረዋል። «ወጣቱን ትዉልድ መድሃኒት የሚዉጥ ተስፋ አልባ ትዉልድ ለማድረግ እየታሰበ ነዉ» ሲሉም ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ከስድስት ሰባት ዓመታት በፊት የኤድስ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት፤ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በቫይረሱ የተያዙትን ለመርዳት፤ በመላ ኢትዮጵያ 430 ማኅበራት እንደነበሩ ያስታወሱት ግለሰቡ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ግማሹ ያህል እንኳ መኖራቸዉ እጠራጠራለሁ ብለዋል። «መንግሥት ስለ ቫይረሱ አስገንዝቦ ተስፋ ያለዉ ትዉልድን ካላነፀ ማንን ሊመራ ነዉ» ሲሉም ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day1 #ኡቡንቱ #Ubuntu

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - #ኡቡንቱ በሚል ርዕስ ያዘጋጀነው የግንዛቤ መፍጠሪ መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ስኬታማ ነበር። ሁሉንም አካላት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን! ከወጣቶች ጋር የምናደርገው ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እስከ ህዳር 27 ይቀጥላል።

“Ubuntu is about a community coming together to help one another.”— Paul Pierce

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ፒስሞዴል
#ጋሞዞንአስተዳደር

"ኡቡንቱ" ላይ የምንሰራቸው ሀገር አቀፍ ስራዎች ላይ አስተያየታችሁ፣ ሃሳባችሁን አካፍሉ። በምን በኩል ብንሰራ ውጤት እናመጣ ይሆን? ልታግዙን ይምትችሉ አካላትም አናግሩን! @tsegabwolde
@tikvahethiopiaBot 0919743630
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ!

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ። አራቱ ሴናሪዎች /እጣ ፈንታ/ ይፋ የተደረጉት ትናንት ማምሻውን (ህዳር 23/2012 ዓ.ም) በስካይላይት ሆቴል "የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032" በሚል ርእስ በተደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የዴስቲኒ ኢትዮጵያ በአገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ክልሎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ምሑራን የተውጣጡ 50 ሰዎች በጥንቃቄ በመምረጥ ላለፉት ስድስት ወራት ዝግ ስብሰባዎችን በማካሄድ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት አገራችን ሊገጥሟት የሚችሉ አራቱን ሴናሪዎች መቅረፁን የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ንጉሴ አክሊሉ ተናግረዋል። አራቱ ሴናሪዎች አፄ በጉልበቱ ፣ ሰባራ ወንበር ፣ የፋክክር ቤት እና ንጋት ናቸዉ።

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ-ባሕር ዳር የቦይንግ አውሮፕላን በረራ በድጋሚ ተመጀረ!

ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ - ባሕር ዳር የቦይንግ አውሮፕላን የበረራ አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ መርሃ-ግብር መሰረት ቦይንግ ወደ ባሕር ዳር በሳምንት አራት ቀን ማለትም ማክሰኞ፣ ሐሙስ፣ ቅዳሜና እሑድ የሚበር ይሆናል።

ቦይንግ ወደ ባሕር ዳር በረራ መጀመሩ ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለቱሪዝም ፍሰቱ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የገለፁት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ናቸው።

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በዋጋ መውደቅ ምክንያት ሰሊጥ ወደ ምርት ገበያ ድርጅት ማቅረብ አቋርጠናል" –ሰሊጥ አቅራቢ ነጋዴዎች

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ ሰሊጥ አቅራቢ ነጋዴዎች በዋጋ መውደቅ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ያቀርቡት የነበረውን የሰሊጥ ምርት ማቋረጣቸውን ገለጸ።

አቅራቢዎች እንዳሉት መንግስት ባስቀመጠው የመግዣ ዋጋ ተንተርሰው ለተከታታይ ወራት ከአምራቹ በመግዛት ለምርት ገበያ ድርጅቱ ቢያቅቡም ከፍተኛ ኪሰራ ስለደረሰባቸው ምርቱን ማቅረብ ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስረድተዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‹‹አባሎቼ ይለቀቁልኝ›› አብን!

‹‹አመራርና አባሎቼ በግፍ ታስረውብኛል›› ሲል መንግሥት እንዲለቃቸው የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተቃውሞውን በአድማና ሰልፎች እንደሚገልፅ አስታወቀ፡፡

በሰኔ 15ቱ የባለሥልጣናት ግድያ ትክክለኛ ተጠያቂዎች ተይዘዋል ብሎ እንደማያምን የገለፀው ንቅናቄው አባላቱ እንዲፈቱለትና መንግሥት በወንጀሉ ፈፀሚዎች ላይ አሁንም ጠንካራ ምርመራ እንዲደርግ ጠይቋል፡፡ ይህ ካልሆነና አባሎቹ ካልተፈቱ ግን የአደባባይ ሰልፎችና የተለያዩ አድማዎችን በማድረግ በተቃውሟቸው እንደሚቀጥሉ ሊቀ መንበሩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥት ምርመራ ቡድን በሰኔ 15ቱ የባለሥልጣናት ግድያ ላይ ጥልቅ ምርመራ ማድረጉንና ተሳትፎ እንዳለቻው ባመነባቸው ግለሰቦች ላይ ክስ እንደሚመሰርት ከሳምንታት በፊት መግለፁና ክስም መመስረቱ ይታወቃል፡፡

የአብን ሙሉ መግለጫ👇
https://telegra.ph/NMA-12-04

(NMA - AHADURADIO)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር በኢትጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር ድራሆሚር ስቶስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ አነጋግረዋል፡፡

በሁለትዮሽ ውይይታቸውም በአገራቱ መካከል ለረጅም አመታት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር ድራሆሚር ስቶስ እንደገለጹት በሁለቱ አገራት መካከል ለዘመናት የቆየውን ትስስር ተከትሎ አሁንም የስሎቫኪያ ባለ ሃብቶች በኢትዮጰያ በሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KOKA

የእንቦጭ አረም በቆቃ ሐይቅ ላይ እየተስፋፋ ያለበት ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡ የቆቃ ግድብ፣ ኤሌክትሪክ ከማመንጨትም በተጨማሪ፣ ለቱሪስት መስህብነት እንዲሁም በዓመት ከ625 ቶን በላይ የዓሳ ምርት የሚገኝበት ነው፡፡ አረሙን በዘላቂነት ለማስወገድ፣ ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ መሆኑም ተሰምቷል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

More(ENA)👇
https://telegra.ph/ETH-12-04-2

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot