TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመንገድ መዘጋቱና የሰልፉ መነሻ ምንድነው?

ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ የOMN ዋና ዳይሬክተር ጀዋር መሀመድን ጠባቂዎች በሌሎች ለመቀየር ትዕዛዝ መተላለፉን እና ውሳኔው ለምን እንደተላለፈ ግልፅ እንዳልሆነለት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። ይህንን ተከትሎ ነው በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መንገድ የመዝጋት እና ሰልፍ የማድረግ እንቅስቃሴ የተጀመረው።

Via Maleda Media
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ADAMA | በአዳማ ከተማ ፍራንኮ አካባቢ አሁን ያለው ሁኔታ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል። የአዳማ የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት በአካባቢው መንገድ ተዘግቷል። የንግድ ተቋማትናንት የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
BOLE | "አሁን ቦሌ አከባቢ በሚገኘው የአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት ለድጋፍ የመጡ ወጣቶች ይታያሉ። Ibro /Tikvah Family/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
BOLE | ቦሌ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንደገለፁት የOMN ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ መግለጫ ከሰጠ በኃላ ወደተሰበሰቡት ወጣቶች ሄዶ አነጋግሯቸዋል። ወጣቶችም እንዲረጋጉ መልዕክት አስተላልፏል።

Via Ibro/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጀሞ አንድ ኮንዶሚንየም አካባቢ ሱቆች ተዘገተዋል። ድንጋይ የሚወረውሩ ወጣቶች በፌዴራል ፓሊስ እንዲበተኑ እየተደረገ ነው። ወላጆች ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት እያስወጡ ነው። በተመሳሳይ ፉሪ አካባቢ መንገድ ተዘግቷል።

Via ተስፋዬ ጌትነት/ካፒታል ጋዜጣ/
PHOTO: Furi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⚠️ካራ ቆሬ፣ ኬንቴሪ፣ ወለቴ አካባቢ አትላስ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ወደቤታቸው መሄድ አልቻሉም፤ ወላጆችም ልጆቻቸውን መጥተው መውሰድ አልቻሉም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA | የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በአዳማ ከተማ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል። በሌላ በኩል የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መንገድ በመዘጋጋቱ ምክንያት ለተማሪዎች እንጀራ ወደግቢው ማድረስ እንዳልተቻለ ገልጿል። መንገድ ተከፍቶ እንጀራ እስኪቀርብ ድረስ ተማሪዎች እንዲታገሱትም ጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጃዋር ጥበቃ መነሳት ወሬና የቀሰቀሰው ቁጣ!

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ተመድበውለት የነበሩት የደህንነት ጥበቃ አባላት በምሽት እንዲነሱብኝ ታዘዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስተላለፈው መልዕክት ቁጣና ተቃውሞን ቀሰቀሰ።

በዚህም ሳቢያ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የተቃውሞ ሰልፎች ያጋጠሙ ሲሆን በርካታ ወጣቶችም ድርጊቱን በመቃወም አዲስ አበባ በሚገኘው የጃዋር መሀመድ ቤት አቅራቢያ ተሰብስበዋል። የጸጥታ ኃይሎችም በአካባቢው ተሰማርተው እንዳሉ የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ቀርበው እንደተናገሩት በማንኛውም ፖሊስ የተወሰደ እርምጃ የለም። አቶ ጃዋር ተወሰደብኝ ያሉት ርምጃም ስህተት ነው ያሉ ሲሆን ፖሊስ መደበኛ ስራውን እየሰራ ነው ብለዋል። የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱና መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንዲቀጥሉ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ፖሊስ የሕግ ማስከበር ሥራውን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-10-23

Via BBC AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ! #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

• በአዲስ አበባ ዙሪያ መንገድ የተዘጋው አክቲቪስት ጀዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው ያስተላለፉት መልዕክት ስለነበረ ነው፡፡

• መልዕክቱ በዋናነት ልታሰር ነው፤ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው የሚል ሲሆን በመንግስትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደባቸውም፤ እንደወትሮው የየዕለት ተግባራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

• ፖሊስ ለውጡን ተከትሎ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የተለያዩ ድርጅቶችና አክቲቪስቶች በሚኖሩበት አካባቢ እና በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ችግር እንዳያጋጥማቸው የጥበቃ ከለላ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

• አገሪቱ ውስጥ ይንፀባረቁ የነበሩ የተለያዩ ችግሮች ከጊዜ ወደጊዜ እየተፈቱ ሰላማዊ ሁኔታ እየተረጋገጠ በመምጣቱ እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰላም ተንቀሳቅሰው መኖር የሚችሉ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የግል ጥበቃዎችን የማንሳት ስራ ስንሰራ ቆይተናል፡፡

• ለወደፊቱም ባሉን አሰራሮች መሰረት አስፈላጊ የሆነበት ቦታ እና አስፈላጊ ያልሆነበት ቦታ በመለየት ይህ ስራ በፖሊስ ውስጥ ሲከናወን የነበረ ተግባር ነው፤ ለወደፊቱም ይከናወናል፡፡

• ስለዚህ በፖሊስ እርምጃ ተወሰደብኝ ብለው ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው፤ በየትኛውም ፖሊስ የተወሰደ እርምጃ የለም፤ በየትኛውም የመንግስት አካል የተወሰደ እርምጃ የለም፡፡

Via EBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ የሚገኘውን የእውቁን የኦሮሞ አክቲቪስት እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ቁጥራቸው በርከት ባሉ ወጣቶች አሁንም ተከብቦ እየተጠበቀ ነው። ወጣቶቹ የተቃውሞ መፈክርም በማሰማት ላይ እንደሚገኙ የጀርመን ድምፅ ራድዮ /DW/ ዘግቧል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #GERMANY

ኢትዮጵያና ጀርመን የ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የእርዳታ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሳደግ፣ የስራ ፈጠራን ለማስፋት እንዲሁም ከስደት የተመለሱ ዜጎችን ለማቋቋም ይውላል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያና የጀርመን ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ በፊርማው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #RUSSIA

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ አላማ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት በሩሲያ ሶቺ ተፈራረሙ፡፡ የሁለትዮሽ ስምምነቱ በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደው ካለው የአፍሪካ ሩሲያ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ነው የተፈረመው፡፡ የስምምነቱን ፊርማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተቃውሞ ሰልፎቹን ተከትሎ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አጋጠመ!

ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ለተቃውሞ ሰልፎች አደባባይ ወጥተዋል። የተቃውሞ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ አዳማ እና ሻሸመኔ ከተሞች ይጠቀሳሉ። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

#አምቦ

በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመተዋል ተብሏል። በአምቦ በተቀሰቀሰው ግጭት ነዋሪዎች አምስት ሰዎች በጥይት መመታታቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፤ የሆስፒታል ምንጮች በበኩላቸው ሦስት ሰዎች ለሕክምና ወደ አምቦ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሌሊቱን በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት ተፈጸመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል። ለተቃውሞ የወጡትን ሰዎች ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ከተኮሱ በኋላ ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ መወርወር እንደጀመሩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

ይህ ተከትሎም ነዋሪዎች አምስት ሰዎች በጥይት መመታታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደበበ ፈጠነ በበኩላቸው ሦስት ሰዎች በጥይት ተመተው ለህክምና ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-23-2

Via BBC
@tsegabwolde
#ADAMA

በአዳማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። የተቃውሞ ሰልፎቹ ባህርያቸውን በመቀየር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ሰዎች መካከል ግጭት መከሰቱን ተሰምቷል። የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና ኦሮሚያ ፖሊስ በሁለት ቡድን ተከፍለው ወደ ግጭት ባመሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። እስካሁን በአዳማ በተከሰተው ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በግልጽ ማወቅ ባይቻልም የሰው ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ የተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን "ሰው ሳይገደል እንዳልቀረ መረጃው ደርሶናል። ማን እና በምን ሁኔታ እንደተገደለ ግን እስካሁን ግልጽ መረጃ የለኝም" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በከተማዋ የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ ሱቆችን የመዝረፍ፣ የሥርዓት አልበኝነት ተግባራት ሲፈጸሙ እንደነበር ቢቢሲ ገልጿል። ይሁን እንጂ የንግድ እንቅስቃሴዎች ከመቆማቸውም በላይ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች ዝግ ናቸው።

Via BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
​​#ADAMA

የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አክቲቪስት እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ጣቢያ ዋና ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድን መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ተሰማርተዋል መባሉን ተከትሎ በአብዛኞቹ የኦሮሚያ ከተሞች ውጥረት ነግሷል።

ድርጊቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገባቸው ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች መካከል አንዱ በሆነችው አዳማ አንድ ሰው መሞቱን እና ንብረት መውደሙን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በአዳማው ተቃውሞ ከየት እንደተተኮሰ ባልታወቀ ጥይት የአንድ ግለሰብ ህይወት ማለፉን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው የችግሩን መፈጠር አምነው የተጣራ መረጃ በእጃቸው እንደሌለ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-23-4

Via የጀርመን ድምፅ ሬድዮ/DW/
PHOTO: Tikvah Family
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ በሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች መንገድ በመዘጋቱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት ጉዞዎች አሁንም ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጡ ይገኛሉ።

በቢሻን ጉራቻ፣ በአርሲ ነገሌና በቡልቡላ ከተሞች የሚገኙ የአይን አማኖች ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ እንደገለፁት አዲስ አበባን ከሀዋሳ የሚገናኘው መንገድ ከዛሬ ጠዋት ረፋድ ጀምሮ በአካባቢው ወጣቶች በድንጋይና በግንድ እንደተዘጋ ይገኛል።

ዛሬ ጠዋት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምረው የነበሩ በርካታ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች በመንገዶቹ መዘጋት ምክንያት ከመንገድ ተመልሰው ተሳፋሪዎቻቸውን አውርደው ለመቆም ተገደዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ/DW/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት እንዳደረጉት ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ የሚወስደው መንገድ ሆለታ ላይ ተዘግቷል። #ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

አዳማ ከተማ ከሰዓታት በፊት ከነበረው አለመረጋጋት አሁን ላይ አንፃራዊ መረጋጋት እየታየባት እንደሆነ የቤተሰባች አባላት ግልፀዋል። አልፎ አልፎ የመኪና እንቅስቅሴም ይታያል።

በነገራች ላይ፦ የከተማውን ወጣቶች ወደግጭት እንዲገቡ ለማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተገቢ ያልሆኑ የፉክክር የሚመስሉ መልዕክቶች እየተሰራጩ በመሆኑ ሁሉም የአዳማ ከተማ ወጣት ነገሮችን በእርጋታ ሊመለከት ይገባል።

ሰላም ለሀገራችን!

PHOTO: Fitse ከፍራንኮ/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ጥዋት ከነበረው አንፃር በአሁን ሰዓት አንፃራዊ መረጋጋት እየታየበት ይገኛል። እንቅስቃሴዎች የተቀዛቀዙ ቢሆንም ሁኔታዎች መረጋጋት ጀምረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Harar በተመሳሳይ በሀረር ከተማ ጥዋት የነበረው ከፍተኛ ውጥረት ረገብ እያለ የመጣ ይመስላል፤ የቲክቫህ ሀረር ቤተሰቦች ሁኔታዎች ከጥዋቱ አንፃር መሻሻል ማሳየታቸውን ገልፀው ወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ ተማፅነዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እና አደጋ አሁንም እየቀጠለ መሆኑንፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተናገሩ። ፓትርያርኩ ዛሬ የተጀመረውን የአመቱን የሲኖዶሱን ምልአተ ጉባኤ ሲከፍቱ እንዳሉት «በሃገራችን በተፈጠረው ያለመረጋጋት አብያተ ክርስትያናት ተቃጥለዋል፣ ካህናትና ምእመናን ተገድለዋል አሁንም ስጋቱ እንዳለ ከቀረበልን የአህጉረ ስብከት ሪፖርት ሰምተናል በአይናችንም አይተናል» ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia