TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DOHA በከፍተኛ ትንቅንቅ...በአስደማሚ ፉክክር ኬንያ ወርቅ አገኝች!!! ሀገራችን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ በ3,000 ሜትር መሰናክል በለሜቻ ግርማ አማካኝነት የብር ሜዳልያ አግኝተናል!

Via @tikvahethsport
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከኮልፌ...

"ኮልፌ ኮምፕሬንሲቭ ትምህርት ቤት አካባቢ ህብረተሰቡ እና አመራሮች ለነገው የኢሬቻ በዓል ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ እንግዶችን ውሃና ዳቦ በማቅረብ በክብር እየተቀበሉ ነው።" #Amanuel

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተማሪዎች ቅናሽ አደረገ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተለያዩ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚጓዙ ተማሪዎች የ20% የአየር ትኬት ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል። ተማሪዎች የአየር መንገዱን የሞባይል መተግበሪያ እና ድረ ገፅ በመጠቀም FNH01 ፕሮሞ ኮድን በማስገባት የቅናሹ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አስታውቋል።

የሽያጭ ጊዜ : እስከ ጥቅምት 07 ቀን 2012 ዓ/ም
የበረራ ጊዜ : እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ህይወት ማለፉ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ የዘመናዊ በሙዚቃ ታሪክ ትልቅ አስተዋጽኦ የተጫወተው ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ዛሬ ማለዳ ህይወቱ ማለፉን ኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል።

Via Ethio FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል! #TIKVAH_ETHIOPIA

PHOTO: TESFAYE & ROBEL
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆራ ፊንፊኔ #Irreechaa2019

PHOTO: EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የሙዚቃው ሰው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረ አርቲስት ነው።

ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል። እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ ኤልያስ መልካ በፋና ላምሮት የድምፀውያን ተስጥኦ ውድድር ላይ #በዳኝነት ሲያገለግል ቆይቶ ነበር። ለሊቱንም በመኖሪያ ቤቱ ህይወቱ እንዳለፈ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ሰሞኑን በኢትዮ-ጠቢብ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ሲከታተል እንደነበረ ታውቋል።

RIP!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIP

ኤልያስ መልካ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታሪስት፣ ፒያኒስት ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለሀገራችን በማስተዋወቅና ችሎታቸውን ለይቶ በዚያ እንዲያልፉ በማድረግ ይታወቃል።

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተና ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ከዚያ በኃላ ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋር የሰራበት ጊዜ ነበር ። ከ30 በላይ ሙሉ አልበሞችን ልዩ አድርጎም አቀናብሯል።

ከመሃሙድ አህመድ፣ ከኩኩ ሰብስቤ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ ጋር የሰራ ሲሆን፥ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱ ጥቂቶቹ ናቸው። “ሙዚቃ በኤልያስ መልካ ከነሙሉ ክብሯ ታልፋለች”ይላሉ ብዙ ድምፃውያን።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETHIOPIA በታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹ እንዲሁም ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተያዘው የበጀት ዓመት 6.8 ሚሊዮን የሀገር ውስጥና 38ሺህ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በወላይታ ዞን ያሉትን የቱሪስት መስዕቦች ይጎበኛሉ ተብሎ መታቀዱን በዞኑ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ልማትና ብቃት መረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ አለሙ አሰሌ ተናግረዋል፡፡ የወላይታ ዞን እንደአንጃራ ፏፏቴ፣ ከ58 ሺህ ዓመት በፊት የሰው ልጅ ይኖርበት የነበረው ዋሻ፣ የአባያ ፍል ውሃ፣ አባያ ሀይቅ፣ የተፈጥሮ ድልድይ፣ የወላይታን ህዝብ ባህልና ዕሴትን በስፋት የሚያስተዋውቅ ሙዚየም እና ሌሎችም በርካታ የቱሪስት መስዕቦች እንዳሉ አቶ አለሙ ገልፀዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

አትሌት ደምስ ፀጋው አረፈ!

ባለፉት በርካታ አመታት ሀገሩ ኢትዮጵያን ወክሎ በተለያዩ ውድድሮች ሲወዳደር የነበረው አትሌት ደምስ ፀጋው ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አትሌቱ ኢትዮጵያን በመወከል በሀገር አቋራጭ እና የአስፓልት ላይ ውድድሮችን በርካታ ጊዜ ያደረገ ሲሆን በአደረበት ህመም ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡

አትሌት ደምስ #በግሉ እና #ሀገር በመወከል በርካታ ውድድሮችን አድርጎ ጥሩ ውጤት ያመጣ እንደነበርም ታውቋል፡፡ አትሌቱ ህይወቱ ያለፈው በአሜሪካ ሀገር ሲሆን በቅርብ ቀናት አስከሬኑ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ/Bekal Alamirew/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ታርጫ

በአሁኑ ሰዓት በዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ታርጫ የዞኑ ተወላጅ ምሁራን፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት "የዳውሮ ምሁራንና አጋሮች ማህበር ምስረታ" የመክፈቻ ስነስርዓት እየተደረገ ይገኛል። ስነስርዓቱ በአገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተከፍቷል።

Via Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia