TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የፀጥታ_ጉዳይ

" የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ

ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል።

ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ ጥቃት እያደረሱ ነው።

ነዋሪዎቹ በቅድሚያ ጥቃቱ በገጠር ቀበሌዎች ላይ መጀመሩን አመልክተው ማለዳ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጉንዶመስቀል ከተማ በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችም እየተዘረፈ ነው ብለዋል።

በጉንዶ መስቀል ከተማ ዙሪያ ላይ ባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጎችም መኖሪያ ቤቶች በታጣቂዎቹ እየተቃጠለ እና ከብቶቻቸው እየተወሰዱባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። በስፍራው ላይ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር እንደሌለም አክለዋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶመስቀል መግባታቸውን ገልጸዋል።

" ታጣቂዎቹ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦችን ንብረት እየዘረፉ ነው " ያሉት አስተዳዳሪው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባላቸው ማመልከታቸውን ለአል አይን ኒውስ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia