TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስጋና

ለአበበች ጎበና ሕጻናት ማሳደጊያና ልማት ማህበርና ለመላ ሰራተኞቹ
ድርጅቱን ለማገዝ ከፈለጉ 011 155 3622/ 011 869 4629
የእንጀራ እና የባልትና ምርታቸውንም ከልማት ስራዎቻቸው ጥቂቱ ነው፡፡

ግራፊክስ ዲዛይነሮቻችን

👉 AMG(Amanuel Girma) @AGraphics 0928406521or 0924163982
👉 ሰለሞን(sc) ግራፊክስ @Scgpx +251912831494

በሳውንድ ሲስተም

ዲጄ ጆ ለሰርግና ለፓርቲ በቂ እቃዎችን ያቀርባል፡፡ +251911432922

በብዙ የተባበረን የዛው ሰፈር ልጅና የቤተሰባችን አባል
አብዱልከሪም ሁሴን +251 91 173 0261

ሽልማቶችን በመሸለም ለተባበሩን
👉 ቲ ማክስ ፍላሽ
👉 ሴንቸሪ ሲኒማ /@Century_Cinema/
👉 ቴድ ቴክኖሎጂ @Tedtechofficial
👉 @habmartofficial /ሀብማርት

በስራ እያገዙን ለነበሩት፦ ሜዳ ቻት ግሩፕ /@medachat/

እንዲሁም፦

√የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
√ፋና ቴሌቪዥን...የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸

በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት የተከበረውን TIKVAH-ETH ሁለተኛ አመት የምስረታ በዓልን #በፎቶ ተመልከቱ!

📸ዶክተር ኤልያስ ገብሩ
📸የWKU ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
📸የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ
📸የ"ተስፋ የሰነቀ ጉዞ" ፀሃፊ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ካሳ
📸የWKU የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሲሳይ ሸዋማረ

#ሁለተኛ_አመት🎂#TIKVAH_ETH

#አበበች_ጎበና_የህፃናት_እንክብካቤና_ልማት_ድርጅት #ሀምሌ21

🏷በዕለቱ የተላለፉ መልዕክቶችን በቀጣይ ቀናት በዩትዩብ እና በቴሌግራም ቻናላችን በኩል ወደእናተ ይደርሳል!! በድጋሚ እንኴን አደረሰን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TIKVAH_ETH

📹የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፂዮን ተክሉ
📹የWKU ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
📹የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ
📹የ"ተስፋ የሰነቀ ጉዞ" ፀሃፊ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ካሳ
📹የWKU የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሲሳይ ሸዋማረ

#ሁለተኛ_አመት🎂#TIKVAH_ETH

#አበበች_ጎበና_የህፃናት_እንክብካቤና_ልማት_ድርጅት #ሀምሌ21

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሱዳን የትምህርት ተቋማት ተዘጉ!

ሱዳን ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ የትምህርት ተቋማትን ዘጋች፡፡ አምስት ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ ተከታታይነት ያለው ሀገር አቀፍ ሰልፍ እንደሚኖር በመሠጋቱ የሱዳን ባለስልጣናት ለጊዜው ትምህርት እንዲቋረጥ አዘዙ፡፡
ወታደራዊ ምክር ቤቱ ያወጣው መመሪያ ከረቡዕ ጀምሮ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በራቸው ዝግ እንዲሆን ማዘዙን የሀገሪቱ የዜና አውታር አስታውቋል፡፡

ትናንት ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ ካርቱምን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች በርክተዋል፡፡ በተለይ በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት የተገደሉት አራት ሰልፈኞች ተማሪዎች መሆናቸው ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

አል ኦቤይድ በተባለው አካባቢ የነዳጅና የዳቦ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ በርካቶች ዘመናዊ መሣሪያ በታጠቁ አልሞ ተኳሾች መቁሰላቸውም ተሰምቷል፡፡ ሰልፈኞቹ የሱዳንን ፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የተፈጠረውን የፀጥታ ስጋት ተከትሎም ባለስልጣናት ከነገ ጀምሮ ትምህርት በሁሉም ደረጃ እንዲቋረጥ አዝዘዋል፡፡ ‹‹ለሁሉም ግዛት አስተዳዳሪዎች ተጨማሪ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ መዋዕለ ሕጻናት፣ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላልፏል›› ሲል ሱና የተሰኘው የዜና ማሠራጫ መዘገቡን ቢቢሲ አስታውቋል፡፡

Via BBC/#AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀርመን

በፍራንክፈርት የስምንት አመት ልጅ ከነ አናቱ ወደ ባቡር ሐዲድ ገፍቶ በመጣል የተጠረጠረው ኤርትራዊ በጥምር ግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረትበት ነው፣ የ40 አመቱ ተጠርጣሪ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነው። ስዊትዘርላንድ ከገባ 13 አመታት አስቆጥሯል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ ከቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በ2011 ይካሄዳል ተብሎ የነበረውን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች አባለት ምርጫ እና የአካባቢ ምርጫ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ ባለመቻሉ ከቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ነው ያፀደቀው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን #ዘመናዊ አሰራር ለማላበስ እና አዋጆችን ለማዘጋጀት እንዲሁም አዳዲስ የቦርዱን አመራር ለመምረጥ ጊዜ በመወስዱ ምርጫውን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ማካሄድ እንዳላስቻለ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የከተማዎቹ ምክር ቤቶች አባላት እና የአከባቢ ምርጫ አብሮ እንዲካሄድ ወስኗል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቱሪዝም ኢትዮጵያ አዲስ ሃላፊ ተሾመለት!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ሀላፊዋን ሌንሳ መኮንንን ከሀላፊነታቸው እንዳነሱ አዲስ ፎርቹን ዘግቧል። በምትካቸው አቶ ስለሺ ግርማ ተተክተዋል።

Via አዲስ ፎርቹን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ትግራይ

ሁለተኛው አለም አቀፍ የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል ከዛሬ ሐምሌ 24 እስከ 30 በተለያዮ ዝግጅቶች እንደሚካሄድ የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቬስቲቫሉ ‹‹የትግራይ ዲያስፖራ አንድነት ለትግራይ ህዝብ ደህንነትና ህልውና›› በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የትግራይ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ችግኝ ተከላውን ጊነስ መዝግቧል
/ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

"ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የዛፍ ተከላ ሪከርዱን እንዲመዘግብ ተጋብዞ ነበር፣ ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም!" ሲሉ የግብርና ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን ተናገሩ።

ሚኒስትሩን "ሰኞ የተተከለውን 343 ሚልዮን ችግኝ ጊነስ መዝግቧል ወይ?" ተብለው ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ለተጠየቁት ጥያቄ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል፦

"አሜሪካ ባለው ኤምባሲ በኩል ጥሪ ደርሷቸው ነበር። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ጉዳዩን ይዞት ነበር። ነገር ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም። ኮሚኒኬሽኑ ትንሽ ዘግየት ብሎ ነበር መሰለኝ። ተከላው እና የቆጠራ ሂደቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የውጭ ዜጎችም እንዲያዩት ክፍት ሆኖ ነበር። ነገር ግን የኛ ሀሳብ ከዛ የዘለለ ነው። አሁን ይህንን ያህል ስራ ከሰራን መድገምም እንደምንችል እናውቃለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው አገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በየክልሉ የተተከሉትን ችግኞች ብዛት የሚያሳይ ካርታ፡-
የኢቦላ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ እና በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቢኖሩም ለማከም እንዲቻል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከወኑ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኃይሌ የለመደብህ #ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ
.
.
የሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ኩባንያ የሆነው ማራቶን ሞተርስ ከቀረጥ የ155 ሚሊዮን ብር ገቢ በማስገኘት ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. የግብር ከፋዮች የማበረታቻ ዕውቅና ሽልማት የብር ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኃይሌ የለመደብህ ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› በማለት በቀልድ መድረኩን አዋዝተውት ነበር፡፡ 

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ክዊንስ ኮሌጅ በትላንትናው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ5000 በላይ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወታደራዊ ልምምዱ ተጠናቋል...

11 አገሮችን በማሳተፍ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ትብብር የተሰጠው ወታደራዊ ስልጠና በቀጠናው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አሜሪካ ገለጸች።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ በአፍሪካና ደቡባዊ አውሮፓ የአሜሪካ ጦር ግብረ ሃይል ምክትል አዛዥ ሌተና ጄነራል ላፕቲ ፍሎራ እንደገለጹት፤ የተሰጠው ወታደራዊ ስልጠና በቀጠናው ያለውን የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና እየተስፋፋ የመጣውን የአሸባሪነት ተግባር ለመግታት የሚያስችል አቅም የመገንባት ዓላማ ይዞ በተካሄደው ስልጠና ኢትዮጵያ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጂቡቲ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ፣ ሶማሊያና ኡጋንዳ ተሳትፈዋል።

በስልጠናው በሚሳተፉ ወታደሮች ብዛት ኢትዮጵያና አሜሪካ ትልቁን ድርሻ የሚይዙ ሲሆን ባጠቃላይ ከ1 ሺህ 100 በላይ ወታደሮች ተሳትፈዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
ፎቶ: #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰሜን_ተራሮች

የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ባለፈው ከደረሰበት የእሳት ቃጠሎ የተጎዱ እጽዋቶች አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዳገገሙ ተገለጸ።

Via #አስራት_ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia