TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የህፃናት ፈንድ እንዳስታወቀው በአገር ውስጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ደርሷል፡፡

ከስድስት ወራት በፊት 1.6 ሚሊዮን የነበረው የተፈናቃዮቹ ቁጥር በ1.2 ሚሊዮን ጨምሮ የእርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል፡፡

የኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች ተፈናቃዮቹ የሚገኙባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

የክረምቱን ጎርፍ ተከትሎም የሚፈናቀለው ህዝብ ቁጥር እንዳይጨምር ተሰግቷል፡፡

የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹን ለመደገፍ 111.8 ሚሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን እስካሁን የተገኘው ድጋፍ ከ31 በመቶ እንደማይብልጥ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ሽንዋ ዩኒሴፍን ጠቅሶ እንደዘገበው ከአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያና ኤርትራ የተሰደዱ ተፈናቃችን አስጠልላለች፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚከሰቱ #ግጭቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቃዮቹን ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል ተብሏል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕊ትግራይ አማራ የሰላም መድረክ🕊

የትግራይና አማራ ክልሎች የሰላም መድረክ #በመቐለ_ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ትላንት ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክሩ፣ ስጋት ለፈጠሩ ክስተቶች መፍትሔ የተባሉ ሃሳቦች ቀርበውበታል፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጨምሮ የተሻለ ምክረ ሀሳብ ለፖለቲካ መሪዎች ለማቅረብ በቀጣይነት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

የመድረኩ አስተባባሪና ጥናት አቅራቢ ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ የግጭት ስጋቶች ለማምከን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚስተዋሉ #ግጭቶችና የግጭት ስጋቶች ለመከላከል ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tukvahethiopia
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ #ግጭቶችና አለመግባባቶችን ለመከላከልና ይቅር መባባልን ለማጎልበት የሠላም ግንባታ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ፡፡ የጉባኤው ከፍተኛ አመራሮች በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማና ሁላ ወረዳ ተከስቶ በነበረው ሁከት የተጎዱ ዜጎችን ጎብኝተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia