TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንጠንቀቅ!!

#ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። ትንሽ ስህተት ሁላችንም ወደ #እልቂት ስለሚወስደን ከተቻለን #እንጠንቀቅ ካልሆነም በየቦታው እየገቡ ከመቀባጠር #እንቆጠብ!! ሁለት ህይወት የለም!! ኢትዮጵያ ከጥይት እሩምታ፤ ከቦንብ ፍንዳታ፤ ከእርስ በእርስ ግጭት #ብትርቅ የምትጠቀመው አንተ እና ምስኪን ትንንሽ ልጆችህ ናቸው!! ለራስህ ስትል ስለሰላም ሌት ተቀን ዘምር!! ኮሽ ሲል በቦሌ አድርጎ ከሀገር ከሚወጣ ሰው ጋር ህብረት ፈጥረህ ከወንድምህ እንዳትጣላ፤ እሳቱ ሚበላው አንተን ነውና!!

#የሰላም #የፍቅር #የአንድነት ቀን ይሁንልን!
#TikvahETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
#STOP_HATE_SPEECH

በሀገር አቀፍ ደረጃ TIKVAH-ETH "የፀረ ጥላቻ ንግግር" ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን #ወደማትወጣው መከራ ውስጥ የሚከታት በመሆኑ ጊዜው ሳይረፍድ ይህን እኩይ ተግባር በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል።

በቅድሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገራችን ወጣቶች በሚገኙባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትኩረት በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሊያመጣ የሚችለውን ችግር የማስገንዘብ ስራ እየሰራን እንገኛልን።

ሀሳቡን ካቀረብንላቸው የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሀሳቡን በመደገፍ እንዲሁም ዘመቻውን ለማገዝ ፍቃደኝነቱን ያሳየን #የመጀመሪያውን ተቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ በዶክተር #ታከለ ለሚመራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንዲሁም #ለተማሪዎች_ህብረቱ ያለንን ላቅ ያለ ምስጋናና ክብር እንገልፃለን!!
.
.
.
ውድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኑ ...3 ተከታታይ ምሽቶችን ከTIKVAH-ETH ጋር አሳልፉ! ስለጥላቻ ንግግሮች እና ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋ ስለመጣው አግባብነት የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንነጋገር! የሀገራችሁ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሀሳባችሁን ስጡ...የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጠቁሙ!

ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በተከታታይ!

🔹ቦታ - ዋናው ግቢ(በተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር አካባቢ)

⌚️ሰዓት - ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ

እንግዶች ይኖራሉ!!

#በፍቅር ኢትዮጵያን እንገንባ!!
ከጥላቻ ንግግሮች #እንቆጠብ!!

(የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት)

በቀጣይ፦

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
መቀለ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

#ለቀጣዩ_ትውልድ ከጥላቻ የራቀችን ሀገር እናወርሳለን! ሀሳቡን ለመደገፍ የምትፈልጉ፦
0919 74 36 30 @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia