TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አበሽጌ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳልጌ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ባለሀብቶችና አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ ኃይል በአፈሳ እየተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶች ከቤት ለመውጣት ፍርሀት ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል።

አካባቢው በተለይ ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰንባቸው መንደሮች ካሁን በፊት ግጭቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ በስጋት መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከሰሞኑ እየሆነ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ወጣቱ በፍርሀት ቤቱ ቢቀመጥም አንዳንዶቹ ቤታቸዉ ባሉበት መያዛቸዉን ተከትሎ ፍርሀቱ ከፍ ሊል ችሏል።

ሁኔታውን በተመለከተ ማን ማንን ነው እየያዘ ያለው ? ስንል የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሞን ጣይቀናል።

እሳቸውም " የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን እየያዙ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ሰው ፍርሀት ውስጥ ነው ለሚባለው " ወንጀል ውስጥ እጁ ካለበት ሰው ውጭ ንጹሀኑ ፍርሀት ሊገባው አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" አሁን ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በአካባቢዉ ተሰማርተዉ አሰሳ በማድረግ የጥፋት ኃይሎችን እየያዙ ነው " በማለት አካባቢዉ በፍጥነት ወደነበረ ሰላሙ ይመለሳል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዉ " እንቅስቃሴዉ በአበሽጌ ወረዳና በኦሮሚያ ወሰን መካከል መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ያለስጋት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia