TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኦሮሚያ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ‼️
(20/80ና 40/60)

የ20/80ና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ይፋ ከመሆን ጋር ተያይዞ ቦታው የኦሮሚያ ነው በሚል ከ10 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆነው የአዲስ አበባ መስተዳድር ውሳኔ የሚያሳልፈው እንዴት ነው፤ ለተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች የተሰጠው ካሳ እዚህ ግባ የማይባል ነው፤ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ሀሳቦችን ተቃዋሚዎቹ አንስተዋል።

#በምስራቅ_ኦሮሚያ ጪሮ ከተማ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ሰልፈኛ " በዚህ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ መልዕክታችን በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉት መሬቶች ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" የሚል ነው። ተቃዋሚው ጨምሮም ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው አወዛጋቢው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊመለስ አይገባም ብሏል።

ተቃውሞዎቹ በሻሸመኔ፣ ጪሮ፣ ጂማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሂርና ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፉ ሲሆን በሻሸመኔ አካባቢ የሚገኙ ሰልፈኞች "ኦዲፒ ያልነውን ረስታችሁታል፤ መሬታችን የደም ስራችን ነው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር።

በትናንትናው ዕለት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የዕጣ ማውጫ ስነ ስርአት ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት ያለ ዕጣ እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ያልደበቁት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛ መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተሰሙ ነው።

ምንም እንኳን የተቀናጀው ማስተር ፕላን ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ውድቅ ቢደረግም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና ኦህዴድ ሊቀ መንበር አቶ ኩማ ደመቅሳ ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ "ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል" ብለው ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ምንም እንኳን ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሰው የተባበሩት ኦነግ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ያለውን ድንበር መወሰን ያለበት የኦሮሚያ ክልል ነው የሚል ነው።

በ13ኛው ዙር የ20/80 ቤቶች 32ሺ 653 ቤቶችና በ2ኛ ዙር የ40/60 ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 1ሺ 248 ስቱዲዮ፣ 18ሺ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7ሺ 127 ባለሁለት መኝታ እና 5ሺ455 ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው ተገልጿል።

በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች መሆኑ ተገልጿል።

Via BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰት ነው። ምክትል ከንቲባው የስራ መልቀቂያ አላስገቡም፤ በዛሬው ዕለትም በስራ ገበታቸው ላይ ነበሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፈ ጉባኤ #ታገሰ ለምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ የፃፉት ማሳሰብያ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከትናንት በቀን 27/06/2011 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ለምክር ቤቱ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ግንባታ ተብሎ የተተወውን ባሻ ወልዴ ሰፈር ያለውን ቦታ ለመናፈሻ አገልግሎት መዋሉን ተችተው በቦታው ያለው እንቅስቃሴ #እንዲቆም አሳስበዋል።

Via Elias Mesret & Zinashi Tadesse
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ከአዲስ አበባ ህዝብ የተሰበሰበውን #ድጋፍ ለማስረከብ #ጌዴኦ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዕጣ የወጣባቸው #የኮዬ_ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት ለባለዕድለኞች ይተላለፋሉ‼️
.
.
#በድሃ ገንዘብ የተሠራ ነው፤ ቤቶቹን ባለዕድለኞች ከማስተለለፍ የሚያግደን ነገር የለም” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
.
.
በወሰን ይገባኛል ውዝግብ እጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ያልተላለፉት የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሣምንት ለባለዕድለኞች እንደሚተላለፉ ተገልጿል፡፡ 

ቤቶቹን ለማስተላለፍ አስቸጋሪ ሆኖ በቆየው የወሰን ይገባኛል ውዝግብ ጉዳይ የህግ ችግር አጥንቶ እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ውሣኔውን ሰሞኑን ያሳውቃል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ሠናይት ዳምጤ፤ የኮሚቴውን ውሣኔ ተከትሎ ቤቶቹን በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ የማስተላለፍ ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡ 

በም/ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የሚመራውና ከኮዬ ፈጬ ጋር ተያይዞ የተነሳውን የወሰን ጥያቄ ለመመለስና ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ የተቋቋመው የአስተዳደር ወሰን አጣሪ ኮሚቴ ስራውን ባለመጨረሱ የቤት እጣ ከወጣ ጀምሮ መተላለፍ የነበረባቸው ቤቶች ለባለዕድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ኢ/ር ሰናይት ተናግረዋል፡፡
 
በቀጣይ የሚኖረውን እጣ አወጣጥ በተመለከተ የቤቱ ግንባታ 30% ከተጠናቀቀ በኋላ ዕጣውን በማውጣት ያላለቁ ግንባታዎች እንደሚሠሩ የገለፁት ኃላፊዋ፤ ይህ የሚደረገው ባለ ዕድሎች ቤታቸውን ተከታትለው የማየትና የመቆጣጠር ሃላፊነት እንዲኖራቸው ታስቦ ነው ብለዋል፡፡ 

መመሪያው የሚፈቅደው 80 በመቶ የሚሆነው ተጠናቆ ከተሰራ በኋላ ቢሆንም 30 በመቶ ላይ ሳለ እጣ አውጥቶ 80% ሲደርስ ግን ለባለዕድለኞቹ እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል፡፡  

አያይዘውም ቀደም ሲል ከባንክ ጋር ውል የመፈፀም ስራ ይከናወን እንደነበር ገልፀው፤ አሁን ግን በቤቶችና ልማት አስተዳደር የባንክ ሒሳብ ገቢ በማድረግ ውል ለመፈፀም የሚያስችል አሠራር ተዘርግቶ መጠናቀቁን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ 
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰጡት መግለጫ፤ ዕጣው ለባለ ዕድሎች እንዲተላለፍ ታስቦ የተሠራ በመሆኑና የተሰራውም በድሃው ገንዘብ በመሆኑ ከመተላለፍ መስተጓጐል እንደማይገባው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የአስተዳደር ወሰን ማጣራቱ ከግለሰቦች የዕጣ አወጣጥ ጋር እንደማይገናኝ ተናግረዋል፡፡ 

Via አዲስ አድማስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ለአዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሠረተው የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ባደረገው ጥረት እስከ አሁን 3147 የጎዳና ላይ ነዋሪዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል 701 ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪዎቹን ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በእስከ አሁን የማገገሚያ ቆይታቸው የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እና የስነ-ልቦና ትምህርቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡

ለዚህ ስራ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የተገኙት ኢ/ር #ታከለ_ኡማ እስከአሁን ማገገሚያ የገቡትን ስራ የማስጀመርና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅርቡም ተጨማሪ የጎዳና ላይ ልጆችን የማንሳትና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የማስገባት ስራው እንደሚካሄድም ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ለማህበራዊ ትረስት ፈንዱ በዋናነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ህብረተሰቡን እና ተቋማትን በማስተባበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AAU🔝

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባላት ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪሃት_ካሚል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ፣ ወይዘሮ #የትነበርሽ_ንጉሴ እና የዩኒቨርሲቲው ሃለፊዎች አባላት ናቸው ከተማሪዎቹ ጋር የተወያዩት፡፡ በውይይት መድረኩ ተማሪዎቹ #አስተዳደራዊ እና #አገልግሎት_አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን አንስተው ከቦርዱ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

#fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ !!

የስቅለት እና የፋሲካ በዓል የመስዋዕትነት፣የይቅርታ ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ስለሆነም በሕዝብ አገልግሎት ላይ የተሰማራን እኛ አገልጋዮች በተለይ የስቅለትን እና ትንሳኤን ትርጉም ጥቂቱን እንኳን ብንከውን ለህዝባችን ችግር ከመድረስ ባለፈ ለሀገራችን አይደለም ለአለምም እንተርፋለን።

ንፁህ ሆነን እንደተፈጠርነው ሁሉ በንፅህናና በቅንነት መኖር እና ህዝባችንን ከልብ ማገልገል ይጠበቅብናል።

የበዓላቱን ጥልቅ ተምሳሌትነቶች በእለት ተለት ህይወታችን ተግባራዊ በማድረግም በአምላክ አርአያ የተፈጠሩትን ወገኖቻችንን በማገልገልና ለችግሮቻቸው በመድረስ መንፈሳዊም ሆነ ሀገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ አደራ እላችኃለሁ፡፡

እናም ሁላችንም የህዝብ አገልጋዮች በተሰማራንበት መስክ ሃላፊነታችንን በትክክል በመወጣት መጨውን ጊዜያችንን ብሩህ እንድናደርግ ወንድማዊ የአክብሮት ጥሪዬን እያቀረብኩ መልካም የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ።

አምላክ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

መልካም አውዳ ዓመት !!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ወራዊው የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ የ3 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ክንውኖች ተካሂደዋል፡፡ በማስ ስፖርቱ ላይ የተገኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከግሪክ እና ጃፓን አምባሳደሮች የኦሎምፒክ አክሊል እና ማስኮት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች ተሳታፊ በሆኑበት መርሃ ግብር ላይ የቀድሞ አትሌቶች፣ አምባሳደሮች፣ ሚንስትሮች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የስፖርት ማህበራት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመኖሪያ ቤት ችግር ይፈታ ይሆን

በመጪው አዲስ ዓመት በተለይ #ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ተናገሩ። ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣት ታምራት...

ኢ/ር #ታከለ_ኡማ እና ኢ/ር #እንዳወቅ_አብቴ ከሶስት አመት በፊት ሜክሲኮ አከባቢ በተፈጠረ ከባድ የእሳት አደጋ ከተዘጋ ቤት ውስጥ ተራ በተራ እየተመላለሰ 12 ሰዎችን ከእሳት የታደገውን ወጣት ታምራት ጎሹ በስራ ቦታው ተገኝተው በመጎብኘት ላደረገው #ሰብዓዊነት ምስጋና ችረውታል።

ወጣቱ በዚህ ምግባሩ ሙሉ በሙሉ ሰውነቱ በእሳት ተቃጥሎ ሁለት አመት አልጋ ላይ ያሳለፈ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም የ8 ወር ነብሰጡር ከሆነችው ባለቤቱ ጋር በሚሰሩበት ምግብ ቤት ውስጥ እየኖሩ እንደሚገኙ ኢ/ር ታከለ በጉብኝታቸው ተመልክተዋል። ኢ/ር ታከለ ኡማ ወጣት ታምራት ጎሹ ላሳየው ሰብዓዊነት ያላቸውን አድናቆት ገልፀው ቀሪ ህይወቱን የሚመራበት የመኖሪያ ቤት እንደሚያገኝ ቃል ገብተዋል።

Via MayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
''የከተማችን ነዋሪ በበጎ ፍቃድ እያሳየን ያለው ተሳትፎ እስካሁን ካገለገልነው በላይ ዝቅ ብለን እንድናገለግል የሚያደርግ ነው''- ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ

የከተማችን ነዋሪ በበጎ ፍቃድ መርሀግብሩ እያሳየን ያለው ከፍተኛ ተሳትፎ እስካሁን ካገለገልነው በላይ ዝቅ ብለን እንድናገለግል የሚያደርግ ነው ሲሉ የከተማዋ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። የመርካቶ ነጋዴዎችን ጨምሮ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሰባሰቡት ከ1.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍን ለከተማ አስተዳዳሩ አስረክበዋል።

ስጦታውን የተረከቡት ኢንጅነር ታከለ ኡማ በክፍለ ከተማው የሚገኘውን የአዲስ ከተማ ት/ቤት የክረምት እድሳት የደረሰበትን ደረጃንም ጎብኝተዋል። ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመርካቶ አካባቢ ነጋዴዎችም የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ አስፋልት ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በአዲስ አመት በመንግስት ት/ቤት ለሚማሩ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመደገፍ የታያዘው ግዙፍ ህልም በከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ተሳትፎ ሊሳካ ችሏል ብለዋል። የህዝቡ ተሳትፎ የከተማ አስተዳደሩን ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳው እንደሆነም የተናገሩት ኢንጅነር ታከለ በአፍሪካ ግዙፉ የገበያ ማእከል የሆነውን መርካቶን ታሪካዊ አሻራውን ሳይለቅ በዘመናዊ መልኩ እንዲገነባ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስከረም አራት ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለመጠበቅ ተስማሙ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉትን ችግሮችን በተመለከተ ለመጪው መስከረም አራት ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩ መንፈሳዊ ማሕበራት ሕብረት የቤተክርስቲያኒቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ለመጠበቅ ተስማሙ። የማሕበራቱ ተወካዮች በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ጋር ተነጋግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-06-3
"አዲስ አበባ ከተማ በቴክኖሎጂ ቀዳሚ መሆን አለባት" ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ
-
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ በዋነኛነት የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-09

ምንጭ፦ Mayor Office Of AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia