TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

- በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል።

- ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች።

- አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ ውጭ ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተክርስቲያን አትሸከምም አትቀበለም።

- ሰላሟን እያወጀች፣ ሰላሟን እየሰበከች በሰላም መንገድ ትጓዛለች።

- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን መሞትን ስራዬ ብላው ይዛ ኖራለች ወደፊትም ሞት ከሆነ በሰላም ለመቀበል ዝግጁ ናት።

- " ይሄን ካደረግሽልኝ ይሄን አደርግልሻለሁ " የሚል መደራደሪያ የላትም ፣ ሊኖራትም አይችልም። ድርድሯ ሰላምና ሰላም ብቻ ነው።

- እኔ ያልኩሽን አድርጊ የሚል በቀኝም ይሁን በግራ ፤ ከገዢውም ክፍል ይሁን እገዛለሁ የሚል ሃሳብ ቢመጣ ያን ተቀብላ የማስተናገድ አቅምም ብቃትም የላትም።

- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ በዓሉ ዓለም አቀፍ ስለሆነ የተለያየ እምነት ያላችሁ ልጆች ፣ የሌላ እምነት ተከታይ ሆናችሁ በዓሉ በዓላችን ነው የምትሉ፣ የምትደግፉ በዓሉን እራሳችሁ አክባሪዎች ፣እራሳችሁ የፀጥታው አስተናጋጆች የሰላም መሪዎች ሆናችሁ በዓሉ በሞቀና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ቤተክርስቲያን መልዕክት ታስተላልፋለች።

- የፀጥታ አካላት ትላንት እንዲህ ተብያለሁ ይሄ እንደገና በተቃውሞ ካልታወጀልኝ በስተቀር ይሄን አላደርግም የሚለውን አስተሳሰብ ትቶ ህግን በህግ ስርዓትን በስርዓት ለመፈፀም አእምሮውን አስፍቶ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

- ሌላው ሌላው ችግር በመድረክ ዙሪያ፣ ማነው ጥፋተኛ ? ምን አስቦ ነው ? ምን ብሎ ነው ? የሚለውን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚመክርበት የሚዘክርበት፣  የሚገሰፀውን የሚገስፅበት ፣ ከቀኖና የወጣውን ከቀኖና ወጥተሃል የሚልበት የራሱ ስርዓት ስላለው ለህጉ እንተወዋለን።

- " ይሄን በሉ ይሄን አድርገ፣ ይሄን ካላደረጋችሁ ይሄን አናደርግም " የሚባል መያዣ ነገር ቤተክርስቲያን አስተናግዳ አታውቅም ፤ ወደፊትም አታስተናግድም።

- እገሌ እገሌ ባልልም ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ናት በዓሉም የህዝብ ነው ይሄን መያዣ አናድረግም ችግሩ ችግር ሳይሆን እንዲፈታ ይደረግ በመልካም ነገር በዓሉን በሰላም እናክብር ብለው የተናገሩ መሪዎች አሉ በዚህ አጋጣሚ ሊደነቁ ይገባል። ከመሪዎች የሚጠበቀው ይሄ ነው። ችግርን እንዴት እንፍታው ችግርን እንዴት እናስወግደው ፣ ሰላም እንዴት እናስፍን ነው መባል ያለበት።

- በየሄድንበት " ደግሞ ለኦርቶዶክስ፣ ለተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ቃሉም ይከብዳል በየቢሮው ስንሄድ ቢያንስ አይሆንም አይባልም " ያንን ያንን ያርሙ " ይላሉ።

- " ኦርቶዶክስ ሃገር ናት ፣ ለሀገር ዋልታ ናት፣ ምሰሶ ናት አምድ ናት ይሄን ታሪክ አይክደውም። ዘመን ቢያስረጃትም ዘመን ቢጥላትም ዘመን ያነሳታል።

- ዛሬም ሲደረግላት እያመሰገነች ነው። ለሀገር ሰላም ማድረግ ያለባትን እያደረገች ነው ፤ በየመስሪያ ቤቱ ስንሄድ " ደግሞ ለኦርቶዶክስ " የሚለው ቃል ሊታረም ይገባል።

- ቤተክርስቲያን ትከበር ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥም #በሃይማኖት_ስም እንደፈለገ የሚዋኙ ሰዎች ቆም ብለው ያዳምጡ፣ የሚናገሩትንም ይመርምሩ ፣ ሃይማኖታዊ ቃል ነው አይደለም ይበሉ ከሃይማኖታዊ ቃል ውጭ የሆነው ሁሉ የእኛ #አይደለም

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት…
#Update

" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ #ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ምንድናቸው ?

በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው።

በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ #ጣልቃ_መግባት_እንደማይችል ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦

° የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣

° የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል #አለባበስን እና የተማሪዎች #አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ምን አሉ ?

የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ #የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም #በመንግሥት እና #በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል።

አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት #ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡

Credit - Reporter Newspaper

@tikvahethiopia