TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማንዌል ማክሮን በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት #ላሊበላ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ላሊበላ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

Via የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ዛሬ 7 ሰዓት አካባቢ ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" - አቶ ማንደፍሮ ታደሰ (የላሊበላ ከተማ ምክትል ከንቲባ) (በቢቢሲ እና ሮይተርስ) ህወሓት ወደ ላሊበላ ከተማ መግባቱ ታወቀ። የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ሀሙስ (7:00 ሰዓት አካባቢ) ወደ ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የታጣቂዎች…
#Update

"...ላሊበላ የገባው የህወሓት ሽብር ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው" - አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

በትላትናው ዕለት የህወሓት ታጣቂዎች አማራ ክልል ወደምትገኘው #ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ማረጋገጣቸው ይታወቃል።

የቡድኑ ታጣቂዎች በሶስት ትምህርት ቤቶች ውስጥም ካንፕ ሰርተው መቀመጣቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ አይዘነጋም።

ላሊበላ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናግረዋል።

ላሊበላ የገባው የህወሓት ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው ብለዋል አቶ ግዛቸው ሙሉነህ።

ህብረተሰቡ በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አካባቢውን ለቆ መውጣት እንደሌለበት የገለፁት አቶ ግዛቸው "ህብረተሰቡ ሳይሸበር ራሱን ሊከላከልና  አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል" ብለዋል።

ህወሓት አሁን ላይ በክልሉ 3 ግንባሮች ውጊያ መክፈቱን አቶ ግዛቸው የገለፁ ሲሆን አሁን ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል ፣ በፋኖ እየተደመሰሰ እና እየተመታ ነው ብለዋል።

ዳይሬክተሩ በርካታ የቡድኑ አባላት መማረካቸውን መጥቀሳቸውን ኤፍ ቢ ሲ በድረገፁ አስነብቧል::

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ስፔን ዜጎቿ ወደ አማራ ክልል ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳሰበች።

ስፔን አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ ለዜጎቿ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

ሀገሪቱ በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት የስፔን ዜጎች ወደ አካባቢው ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳስባለች።

በጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ " #ላሊበላ " የሚገኙ ስፔናውያን ከሆቴላቸው ወይም ከቤታቸው እንዳይወጡ እና አዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲ እንዲያነጋግሩ (0911219403) ጥሪ አቅርባለች።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ከተደረገ በኃላ በጦርነቱ ምክንያት እጅግ ተዳክሞ የነበረው የላሊበላ የቱሪዝም እንቅስቃሴ የተወሰነ መነቃቃት ማሳየቱን ተከትሎ የተለያየ ሀገራት ዜጎች ላሊበላን ለመጎብኘት ወደ ስፍራው ሲያቀኑ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
#ላሊበላ

" ' ቫይብሬሽን ትንሽ ነበረ የሚባለው ' ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉ ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው... ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለም ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷ አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት " - አቶ አበባው አያሌው

(በኢዮብ ትኩዬ)

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ስለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ጉዳት ደርሷል ስለሚባለው ጉዳይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአማራ ፤ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ዙሪያ በፋኖ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ሰሞኑን ተደረገ በተባለ የተኩስ ልውውጥ በቅርሱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፣ ከባድ መሳሪያ እየተተኮሰ በመሆኑ ከፍተኛ ንዝረት እንዳለ በዚህም ቅርሱ አደጋ እንተጋረጠበት የተለያዩ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያው ሲንሸራሸሩ ተስተውለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ " ቅዱስ ቅርሱ " አደጋ ላይ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፦
* በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ?
* ስለ ጉዳዩ የሚወጡት መረጃዎች ምን ያህል እውነተኛነት አላቸው ?
* አዲስ ስንጥቅ አለ ? የሚሉትን ጥያቄዎችና አጠቃላይ ስለጉዳዩ ያለው ማብራሪያ ምን እንደሆነ ለቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርቧል።

በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይስ የለም ? ተብሎ በመጀመሪያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው ኮሚቴ ተልኮ ተረጋግጧል ያሉትን ሁኔታ ከማብራራት ጀምረው እንደሚከተለው ገልጸዋል።

" ላሊበላ አካባቢ ግጭት ነበረ። ከዚያ በመነሳት ነው ' በጥይት ተመቷል ' ይሉ የነበረው " ሲሉ ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም 7 ሰዎች ያሉበት (ከደብሩ ካህናት 3 ሰዎች፣ ከላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት 3 ሰዎች፣ በቦታው ከሚገኝ የቅርስ ባለሥልጣን 1 ሰው) ኮሚቴ ተዋቅሮ ከ3፡00 እስከ 6፡40 ገደማ ዞረው ቅርሱን አይተዋል ብለዋል።

በዚህም የሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ኮሚቴ ፦
- ቤተ አማኑኤልን፣
- ቤተ ሊባኖስ፣
- ቤተ ገብርኤል ያሉባቹውን ቦታዎች ተመክተዋል ነው ያሉት።

አቶ አበባው አክለውም ፤ " ' በቤተ ገብርኤል አናቱ ላይ ጥይት አርፏል' የሚል ነው ወሬው እዛ ሲወራ የነበረው " ብለው፣ "ቤተ ገብርኤል ተወጥቶ ታይቷል። ጥይት ያረፈበት ምንም ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

2ኛው ደግሞ ' ቤተ ሊባኖስ አካባቢ ጥይት ተተኮሰ ' የሚል ነገር እንደነበር ገልጸው፣ " እዛም ላይ ምንም ምልክት የለም። እንዳውም ጥገና እየሰራንበት ነው። 'ቤተ አማኑኤል ላይ ደግሞ የመጠለያውን ብረቱን ጥይት መትቶታል' የሚል ነው፣ ምንም የተመታ የለም። በቦታው የነበሩ ጥበቃዎች አሉ ፣ የተመታ ነገር የለም፣ ግን ሲተኮስ #ቫይብሬሽን ስለነበረው ቃቃ ይል ነበር መጠለያው ከዚያ ውጭ ምንም ነገር የለም " ሲሉ ከኮሚቴዎቹ ያገኙትን ምላሽ አስረድተዋል።

ከሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ቀጥሎ የደቡብ ምዕራብ ግሩፕ ደግሞ ፦
- ቤተ መድኃኒዓለም፣
- ቤተ ማርያም፣
- ቤተ ጎለጎልታ ያሉበትን ቦታ እንደተመለከተ፣ እዚያ ሲባል የነበረው ደግሞ 'የቤተ መድኃኒዓለምን መጠለያ ብረቱን መትቶታል' የሚል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ " ጥይት ሲያርፍ ምልክት ይኖረዋል። ግን ዙረው አይተዋል። ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

አንድ ያሳዩአቸው የመጠለያው አናት ሸራ ከጎኑ ቀዳዳ አለ ' ተመትቶ ነው ' የሚል ነው፣ ያቺ ደግሞ ሸራ ቀዶ መግባትም ብዙም ትልቅ ችግር እንደማይኖረው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ጎለጎልታ፣ ቤተ ደናግል እንዲሁም ቤተ ጊዮርጊስ ምንም የተኩስ ምልክት እንደሌለ ተናግረዋል።

አክለውም ፣ ' ትንሽ #ቫይብሬሽን ነበረ ' የሚባለው ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉት ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው" ብለው፣ የአካባቢው ማኅበሰሰብ የደብሩ ካህናት ሆነው አጠቃለሁ የሚለውን ኃይል በግዝትም ቢሆን ወደ ቅርሱ እንዳይጠጋ ማድረግ፣ በመንግሥት በኩል ቅርስ ጥበቃም፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ምንም አይነት ታጣቂ ቡድን በአካባቢው እንዳይኖር ለማድረግ መስራት፣ ከዚያ ውጭ ደግሞ ቤተ ክህነትም ሆነ የመንግሥት አካላት መግለጫ ሲያወጡ ጠይቀው እንዲያወጡ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከኮሚትዎቹ ጋር መወያየታቸውን አስረድተዋል።

ኮሚቴው ቦታው ላይ ተገኝቶ ሳይመለከት የቆየበት ምክንያትን ሲያስረዱም አቶ አበባው ፤ " #ሀዘን ሆኖ ነው አካባቢው ያዘገየነው። ብዙ ሰው አልቋል። በቦታው ድንኳን አለ፣ እንዲያው በትኩሱ ተነሱና እዩ ከምንላቸው ብለን ነው " ብለዋል።

አክለው " ቅርስ ፖለቲካ አይሆንም፣ ያኔ የነበሩ ሰዎች ቅርሱን ለእኛ አውርሰውናል ሲሆን እንጠብቀዋለን እንጂ በእኛ የፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ቅርስን አናስገባም፣ ከፖለቲካም ከምንም በላይ ነው፣ መተኪያ የለውም፣ ይህን ማንም ማሰብ አለበት" ነው ያሉት።

" ከዚያ ውጭ ቀጣይ የምንሰራው ንዝረቱ ካለ ምን አስከትሏል የሚለውን ነው። እያንዳንዷን ስንጥቅ እናውቅምታለን። አዲስ ስንጥቅ ካለ እናሳውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።

ባደረጋችሁት ዳሰሳ አሁን አዲስ ስንጥቅ የለም? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት ምላሽ፣ "የላሊበላን ያሉትን ስንጥቆች ካህናቱም ያውቋቸዋል። እዚያ ያለው ጽሕፈት ቤት ኃላፊም ያውቀዋል። የእኛም ባለሙያ ያውቀዋል። አዲስ ስንጥቅ የለም ኢን ኬዝ ግን ቫይብሬሽኑ ስንጥቅ አስፍቶ ይሆን እንዴ? የሚለውን ለማረጋገጥ 3ዲ ስካን እናወጣለን። አሁን ያለውን እናያለን፣ እናነጻጽራለን እንጅ ላሊበላ ስንጥቅ በስንጥቅ ነው 22 ቦታዎች ተሰንጥቀው እየተጠገኑ ነው" ብለዋል።

አቶ አበባው በሰጡት አክለው ማብራሪያ፣ "ተመታ የሚባለው ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለምን ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷም አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት፣ እሷን ነው እያነሱ ሲበትኑ የነበረው ያ ደግሞ አጥሯ ላይ ግንብ ነው በ2012 ዓ.ም የተሰራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሁለተኛ ጥይት ያለችው ቤተ ደናግል ማርያም ጋ ኢህአዴግ ሰቆጣ ሲገባ የደርግ ወታደሮች እዛ ገብተው ነበር ይተኩሱ ነበር እሷም አለች" ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ስለጉዳዩ ምን ማብራሪያ እንዳላቸው የተደረግልው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ ጉዳዩን በተመለከተ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ቅዱስ ቅርሱ አደጋ ላይ እንደሆነና ልንታደገው እንደሚገባ ገልጸው ነበር።

የብፁዕነታቸው መግለጫ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አበባው፣ "አቡነ ኤርሚያስ ትልቅ ሰው ናቸው ግን ሰው ሊያሳስታቸው ይችላል። ሁሉም ልጆቻቸው ናቸው ፤ እዚያ ያሉት በኮሚቴው የተገመገመው ትክክል አልነበረም የሚል ነው ፤ እርሳቸውም ትንሽ ቹኩለዋል " ብለዋል።

አክለውም ፣ " በመንግሥት በኩልም ግጭት የለም በቦታው ላይ ማለት ትክክል አልነበረም ግጭት ነበረ በእርግጥ " ያሉት አቶ አበባው ፣ " እርሳቸው በተፈጥሯቸው የእውነት ሰው ናቸው ከመቆርቆር የተነሳ ሊሆን ይችላል። መቆርቆሩንም እንወደዋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia