TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአሜሪካን ተራድዖ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር (#USAID) Mr. Sean Jones ደም ለግሠዋል። #ETHIOPIA #OCT22

እርሶስ?
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Conflict Sensitive Reporting (Amharic Handbook).pdf
3.4 MB
ግጭት አገናዛቢ ዘገባ - የጋዜጠኞች ማጣቀሻ

'ግጭት አገናዛቢ ዘገባ፤ የጋዜጠኞች ማጣቀሻ' ወደ አማርኛ የተተረጎመው በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ድጋፍ በኢንተርኒውስ ኔትዎርክ (Internews Network) ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ነው።

#USAID #Internews
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
 
#USAID #OCHA

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) አሳስቧል።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በሌላ መረጃ ፦ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም USAID/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር የትግራይ ግጭት እጅግ የከበደ ረሃብ እያስከተለ እንደሆነ እና ከ5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል።

ሳምንታ ፓዎር "የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቅኝታችን አጣዳፊ የምግብ ችግር መኖሩን ይጠቁማል" ያሉ ሲሆን ችግሩ እጅግ አስከፊው ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጲያ መንግሥት ግጭቱን ለማቆም እንዲሁም የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ እንዲችሉ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ ገልፀዋል። #VOA

@tikvahethiopia
#USAID

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በትግራይ ክልል ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ የሚውል የ181 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ ማድረጉን የUSAID ሃላፊ ሳማንታ ፓወር አሳውቀዋል።

ድጋፉ ፦

- አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው 3 ሚሊየን ዜጎች ይውላል።

- የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ፣ መጠለያ፣ የጤና አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግቶችን ለማቅረብ ያስችላል።

- ለአርሶ አደሮች ዘርና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብርና ግብአትን ለማቅረብ ይውላል።

- ለማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጫና ማገገሚያ ፕሮግራም ይውላል።

ከዚህ ባለፈ ትላትን የUSAID ኃላፊዋ ሳምንታ ፓወር የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ውስጥ ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት መሰናክል እየሆነ እንዳለ ትዊተር ገጻቸው ገልጠዋል።

ትግራይ ውስጥ 5.2 ሚሊዮን ዜጎች ምግብ ዕርዳታ እንደሚፈልጉና ሁኔታው ከቀውስ ደረጃ ማለፉን ገልፀዋል፡፡

ዛሬ የአሜሪካ USAID እና የአውሮፓ ኅብረት (EU) የሰብዓዊ እና ልማት ዕርዳታ ሃላፊዎች በክልል ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የUSAID ኃላፊዋ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕርዳታን እንዳያሰናክልና ግጭት እንዲያቆም ጫና እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለዚህ የሳማንታ ፓወር ገለፃ በቀጥታ እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም ትላንት በጠ/ሚ ፅ/ቤት በተሰጠው መግለጫ በትግራይ እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ስራ በስፋት ተብራርቷል።

መንግስት ድጋፍ እያደረጉ ላሉ አካላት ከፍተኛ እገዛ እና የእርዳታ አሰጣጥ ሂደሱ እንዲሳካ የማመቻቸት ስራን እሰራ መሆኑን እንዲሁም የሚደረገውን ድጋፍ እየተቆጣጠረ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#USAID-ኢትዮጵያ ባለው መጋዘን 58 ሺ ሜትሪክ ቶን እህል እንዳለው ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

እህሉ በትግራይ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ዜጎችን ሊመግብ የሚችል ነው ብለዋል።

ፓወር የእርዳታ እህሉ ተረጂዎች ጋር ለማድረስ ምቹ እና ያልተገደበ ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#USAID

በአፋር እና አማራ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ከ136 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ሕይወት አድን ምግብ መላክ መጀመሩን USAID አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ ​​አመቺ ከሆነ በአማራ እና በአፋር ክልል ተጨማሪ 340,000 ሰዎችን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#WFP #USAID

USAID በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ ከአገሪቱ ሊወጣ ነው የተባለ ሐሰት ነው ሲል አስታወቀ።

ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

USAID እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቀጠሉን አስታውቋል።

የተቋሙ ቃል አቀባይ ሬቤካ ክሊፍ ፥ " የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሠራተኞቻችን ከአገሪቱ ቢወጡም፤ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፦የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ኮምቦልቻ ውስጥ ያሉት የሰብዓዊ እርዳታ ማከማቻ መጋዘኖቹ መዘረፋቸውን ዛሬ ገልጿል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ ፥ ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ድርጅት በአማራ ክልል ኮምቦልቻ የሰብዓዊ እርዳቃ እንዲያቀርብ ፍቃድ አግኝቷል ብለዋል።

ድርጅቱ ባደረገው ቅድመ ግምገማ መሠረት በርካታ ንብረቶቹ መውደማቸውን እና መጋዘኖች ውስጥ የነበረ እህልም መዘረፉን አሳይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#USAID

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ወደ ትግራይ የሚደረጉት የእርዳታ በረራዎች መጨመራቸውን አሳውቀዋል።

ከታህሳስ ወር ጀምሮ 210 ሜትሪክ ቶን የህክምና እንዲሁም ስነምግብ አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን ፓወር አመልክተዋል።

ነገር ግን ብቸኛው የተቸገሩትን ሁሉ ለመድረስ የሚያስችለው ፤ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሄዱበት መንገድ እንደተዘጋ ነው ብለዋል።

700 ሺህ ሰዎች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ያሉት ሳማንታ ፓወር " የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦትን ማመቻቸት አለበት " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 313 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እየሰጠች መሆኑ አስታውቃለች።

አሜሪካ ፤ በ #USAID በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ወደ 313 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ እርዳታ እየሰጠች መሆኑን ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአፋር ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች እየተካሄድ ያለው ግጭት ወደ 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋላጠቸው ሲሆን ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ ማድረጉንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ብቻ 90 % የሚሆነው የክልሉ ህዝብ እርዳታ የሚሻ ነው ያለው መግለጫው በ3ቱም ክልሎች ወደ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በሚቀጥለው ሰኔ ከፍተኛ ረሀብ ለመሰለ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ብሏል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው አዲሱ እርዳታ ወደ 7 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያደርግ ሲሆን የማህበረሰባዊ ጤና ተቋማትን ለማጠናከር የሚውል መሆኑም ድርጅቱ መግለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USAID

" ... ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ  " - ሳማንታ ፓወር

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል።

በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች ላይ እንግልት መድረሱን በመጠቆም ፤ ህወሓት (TPLF) በእርዳታ ሰራተኞች ላይ ያደረሰውን እንግልት ድርጅታቸው አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው " ያሉት ፓወር ህወሓት (TPLF) የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስራዎችን እንዲያከብር በድርጅታቸው ስም ጥሪ አቅርበዋል።

ከነዳጅ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ አሁንም ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን እያወገዙ ሲሆን ህወሓት (TPLF) በሰጠው ምላሽ " ከወራት በፊት ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስድኩ እንጂ ዘረፋ አልፈጸምኩም " ብሏል።

ነዳጁን ለድርጅቱ ያበደርኩት ከጥቂት ወራት በፊት በነዳጅ እጥረት ምክንያት የምግብ እርዳታ ማከፋፈል ባለመቻሉ ነው ያለው ህወሓት ድርጅቱ ነዳጅ መበደሩንና እንደሚመልስ ግንዛቤ ነበር ሲል ገልጿል፤ " ስምምነታችን በጽሁፍ ተሰንዶ ተቀምጧል " ሲል እየቀረበበት ላለው ክስ ምላሽ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia