TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቴፒ‼️

በደቡብ ክልል በቴፒ ከተማ #ለተቃዉሞ አደባባይ በወጡ ወጣቶች ላይ ፀጥታ አስከባሪዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ሰባት ቆሰሉ። የዐይን ምስክሮች እንዳሉት ከሟቾቹ አንዱ የአስራ ሶስት ዓመት ታዳጊ ወጣት ነዉ ተብሏል። የጀርመን ድምፅ ራድዮ የከተማይቱን ነዋሪዎች ጠቅሶ እንደዘገበዉ ከግጭቱ በኋላ የከተማይቱ የንግድ፣ የትራንስፖርትና የመንግሥት መስሪያቤቶች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ #ተቋርጧል። ፀጥታ አስከባሪዎች የከተማይቱን ዋና ዋና መንገዶችን በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ነዉ። የቴፒና የአካባቢዋ ነዋሪዎች የራስ አስተዳደር ጥያቄ በማንሳት አደባባይ መዉጣት ከጀመሩ ካለፈዉ ጥቅምት ጀምሮ ነዋሪዎችና ፀጥታ አስከባሪዎች በተደጋጋሚ ይጋጫሉ። በየግጭቱ የሰዉ ሕይወት ይጠፋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️

በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።

ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።

"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።

በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።

በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።

ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።

ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።

ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።

ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።

በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።

በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።

አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia