TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሰራዊቱን ስም #በማጠልሽተ የሚገኝ ምንም አይነት ቁምነገር የለም!"
.
.
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዩኒፎርም የለበሱና መለዮ አድርጎ በህዝብ መገልገያ ስፍራዎች ለሚገኙ ወታደሮች ከሁሉም ተገልጋይ በፊት ቅድሚያ በመስጠት፤ ለሞያውና #ለወታደሮቹ ያለንን #ክብር ማሳየት እንደሚኖርበት ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ አሳሰቡ፡፡

ሚድያውን ጨምሮ አጠቃላይ የኪነ-ጥበብ ማህበረሰቡ መከላከያ ሰራዊቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዲቀረፅና በህዝብ ዘንድ ያለው እምነት እንዲያድግ የማድረግ ሀላፊነት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ7ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በአል ላይ ባደረጉ ንግግር የኪነጥበብ ባለሞያዎች በሚሰሯቸው የኪነጥበብ ስራዎች የአገር መከላከያ ሰራዊትን በተመለከተ በጥንቃቄ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የሰራዊቱን ስም #በማጠልሸት የሚገኝም ምንም አይነት ቁምነገር እንደሌለም ጠቅላይ ሚንስትሩ አንስተዋል፡፡

#ሆሊውድ አገርን በውትድርና ማገልገል ትልቅ ሞያ እንደሆነ በማሳየት በኩል #ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን አሜሪካ በተሸነፈችባቸው አውደ ውጊያወችም ጭምር ወታደሮቿ የፈፀሙትን ገድል በማሳየት የወታደሮቻቸውን ጀግንነትና አገልጋይነት ለማጉላት ይሰራሉ፡፡

በአንፃሩ በአገራችን በአብዛኞቹ ፊልሞቻችን፣ ቀልዶቻችንና ፅሁፎቻችን የሚሳለው የወታደሮች እና የጦር አመራሮች ገፀባህሪ ቀረፃ #ጥንቃቄ_የጎደለው እንደሆነ መታዘብ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መከላከያ ሰራዊት ነገ ህዝብ የመረጠው ፓርቲን ተቀብሎ የሚያስቀጥለው ሰራዊት በመሆኑ ከጅምላ ፍረጃ እና ሂስ ሊታቀቡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia