TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" 3,241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም መግለጫው በ " ህገ ወጥ  መንገድ " ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸእ 3 ሺህ 241 የስፖርት ቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

ወደ እርምጃ የተገባው የቤቲንግ ጨዋታ ፤ በከተማው አስተዳደር ላይ እንዲሁም ቀን በቀን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ እየፈጠረ ያለውን አሳሳቢ ችግር በመረዳት ነው ብሏል።
 
ቢሮው ለማሸግ ምክንያት ናቸው ያላቸው ዝርዝር ጉዳዮች ምንድናቸው ?

- ከስፖርት መጫወቻነቱ ባለፈ ሀገር  ተረካቢ ትውልድን እያጠፍ በመሆኑ፤
- ከፍተኛ የወንጀል ማስፍፊያ እየሆነ በመምጣቱ
-  የከተማውን ወጣት ግዜውን አላግባብ በስፍራው እያሳለፈ በመምጣቱ፤
- ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ዉጪ እየሰሩ በመምጣታቸው
- የሰዉ ልጅ ህይወት አላግባብ እየጠፋ በመምጣቱ፤
- ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ትተዉ በቦታው እየተገኙ በተገቢው መንገድም እንዳይማሩ በማድረጉ ፤
- የመማር ማስተማሩን ሂደት እያወከ በመምጣቱ የሚሉት ተነስተዋል።

ቢሮው በመግለጫው.  ከትምህርት ተቋም 200 ራዲየስ ርቀት ላይ መገኝት እንዱሁም እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በቦታው ላይ መገኝት እንደማይገባቸው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህግ እንደሚደነግግ አስገንዝቧል።

እርምጃው ፦
° የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣
° #የብሔራዊ_ሎተሪ_አስተዳደር
° የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን፣
° የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣናት በቤቶቹ ላይ የልየታ ምልከታ ካደረጉ በኃላ የተወሰደ ነው ተብሏል።

ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ምንም እንኳን በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ እየሰሩ ነው በተባሉ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ቢወሰድም በአጠቃላይ የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ኢትዮጵያ ውስጥ #አልታገደም

በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ ነው የሚሉ ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ከተሰራጩ በኃላ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም ስህተት እንደሆነና የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አሳውቆ ነበር።

ከዚህ ቀደም ከ " ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ " ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

መ/ቤቱ " ቤቲንግ " በወጣቱና ለታዳጊው ላይ ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምን ሲሆን  የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን " ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " ብሎ እንደማይወስደው ፣ በዚህ ዘርፍ በርካታ ሰው ተቀጥሮ እንደሚሰራ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር " ቤቲንግ " በስርዓት እንዲመራ መመሪያዎች ወጥቶ እየተሰራበት እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።

ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ አስተያየት ካላችሁ በ @Birlikethiopia ገብታችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia