TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_ኡመርና የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ #አህምድ_ሽዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ዉይይቱም የተኮረው በሶማሌ ክልል ልማትና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሲሄን ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም የክልሉን ልማት የበለጠ #በማጠናከር ረገድ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

#PMOffice
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ፌሊክስ ቲሺኬዲን እና የልዑካን ቡድናቸውን በጠ/ሚ ጽ/ቤት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፕሬዜዳንቱ እና ልዑካቸው ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ የሆኑ መፍትሄዎችን በመፈለግ እንዲሁም በአሁኑ የህብረቱ ሊቀመንበር አመቻችነት በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የድርድር ሂደት ቁርጠኛ መሆኗን በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡

- የታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የትብብር እና የጋራ ልማት ተምሳሌት ሊሆን እንደሚችል እና በሁለቱም ሀገራት ላይ ምንም ጉዳት በማያስከትል መንገድ እንደሚከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ጽኑ አቋም አስረድተዋል፡፡

- በትብብር መርህ ማህቀፍ [ ዴክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ ] መሠረት ለሁሉም ወገኖች የሚጠቅም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት ደግመው ገልፀዋል።

#PMOffice

@tikvahethiopia
#BREAKING

በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው የህወሓት ቡድን ላይ “ብርቱና የማያዳግም” እርምጃ እንዲወሰድ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አቅጣጫ ሰጠ።

መንግስት “ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይል” ባለው አሸባሪው የሕወሐት ኃይል እና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ ብርቱና የማያዳግም እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጥቷል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች የማያዳግም ክንዳቸውን እንዲያሳርፉ አቅጣጫ ተቀምጧል። ከጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸው ኢትዮጵያውያን ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

ህወሓት እየከፈተ ያለው ጥቃት ሕዝባዊ መልክ እንዲይዝ በማድረጉ ያንኑ ለመመከት ሕዝባዊ ምላሽ እንደሚያሻው ገልጿል።

"ውጊያው የትግራይን ሕዝብ ምሽግ ካደረገው እኩይ ኃይል ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር አይደለም ፤ እናም ስንፋለም መጠቀሚያ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ብሎም መላዋ ኢትዮጵያን ከአሸባሪው ቡድን ነጻ ለማውጣትና የሀገራችንን ሰላምና አንድነት ለማስከበር ነው" ብሏል የፌዴራል መንግስት።

የፌዳራል መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም የተናጠል የተኩስ አቁም አድርጌያለሁ ብሎ ፀጥታ ኃይሉን ከትግራይ ክልል እንዳስወጣ መግለፁ አይዘነጋም።

#PMOffice

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ቻይና

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።

ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፎቶ፦ #PMOffice

@tikvahethiopia