TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012

ከመቶ ሀምሳ ዓመታት በሀኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ሊከበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢሬቻ በዓል እንደ ትልቅ እድል ሊታይ ይገባል እንጂ የስጋት ምንጭ መሆን እንደሌለበት የገዳ አባቶች አስገንዝበዋል፡፡

#OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው ከአባገዳዎች፣ ቄሮዎችና ከፎሌ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። አሁን ላይ በዓሉን አስመልክቶ እየተደረጉ ባሉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የከተማ አስተዳደሩም የኢሬቻ በዓል ከምንጊዜውም በላይ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል። አባገዳዎቹ በበኩላቸው በዓሉ ደማቅ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ከ5 እስከ 7 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚሳተፍ ተገለጸ። በበአሉ ላይም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል። በኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ፣ የባህል እሴቶች ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ቶላ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ብዙ ልምዶች ፣ በዓላት እና ቀናት ከምዕራቡ አለም እየተዋስን እያከብርን ነው፣ ሀገር በቀል ባህል የሆነውን ኢሬቻ የኢትዮጵያ የምስጋና ቀን ሆኖ ቢከበር መልካም ነው ብለዋል።

በ2012 የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ከ 5 እስከ 7 ሚሊየን ህዝብ ይሳትፍል ተብሎ እንደሚጠቅም አቶ ስንትአየሁ ተናግረዋል። በዘንድሮ የኢሬቻ በዓል መስከረም 11፣ 2012 ዓ.ም ከ 50 ሺ በላይ ሰዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ሩጫ ይካሄዳል ፣ መስከረም 23 ፣2012 ዓ.ም ለጊዜው ምንነቱ ያልተገለጸ ካርኒቫል ይካሄዳል፣ መስከረም 24 በአዲስ አበባ ሆራ ፌንፌንኔ እና ማጠቃለያው መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር ተነግሯል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012 የመልካ ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ መከበሪያ ቦታ ተለይቶ መወሰኑ ተገለፀ፡፡ #OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ዘንድሮ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

#Irrecha2019
@tsegabwoldw @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012 ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቄራ
• ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
• ከሳርቤቶች አደባባይ ወደ ቄራ
• ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር
• ከቂርቆስ ወደ ገነት ሆቴል
• ከመስቀል ፍላወር ወደ አጎና ሲኒማ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው
• ከኡራኤል ወደ ጦርኃይሎች አደባባይ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ካዛንቺስ->አራት ኪሎ->ሸራተን አዲስ->ሃራም ቤሆቴል->ጎማ ቁጠባ
• ከፒያሳ ወደ ቦሌ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ሃራምቤ ሆቴል->ፍልውሃ->ካዛንቺስ->ኡራኤል->አትላ ስሆቴል->ቦሌ
• ከሳርቤት ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
መካኒሳ አቦ መታጠፊያ->መድሃኒት ፋብሪካ->ሦስት ቁጥር ማዞሪያ->ብስራተ- ገብርኤል አቅጣጫ->በካርል አደባባይ->ቴሌ->ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
• ከፒያሳ ሳሪስ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ቸርችል ጎዳና->ጥቁር አንበሳ->ኦርማ ጋራዥ->በዘውዲቱ ሆስፒታል->በፍልውሃ->በኡራኤል
• እንዲሁም ከፒያሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር ያለውን መንገድ በአማራጭነት መጠቀም ይቻላል።

አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመሮች 991 ፣6727 ፣816 እና በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ011-1-01-02-97

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የኢሬቻ በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ታዬ ግርማ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እና ከዚያ በፊት ለሚከበሩት ፌስቲቫሎች ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ኢሬቻ2012
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ በመሆን ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2012 ጠዋት ከአባ ገዳዎችና ሌሎችም የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የመጪውን ኢሬቻ በዓል አከባበርና በተጨማሪ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-21-4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012

"ከማንኛውም የፖለቲካ አቋም፣ እምነት ውጪ መደረግ አለበት። ባህላዊ ፕሮግራማችን ነው፤ ስለዚህ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ፣ ባንዲራ መታየት አይፈቀድም። ባህሉም ይከለክላል። ዩኔስኮ ውስጥም አንዱ ይህን ባህል የምናቆይበት መንገድ አንዱ ይሄ ነው፤ ከዚህ መጠበቅ አለበት። ነፃ ሆኖ ሁሉም ሰው በዚህ ውስጥ መሳተፍ አለበት። የፖለቲካ ምልክቶች፣ አርማዎች በዚህ ውስጥ መኖር የለባቸውም ይሄንን ህዝቡ እርስ በእርሱ ተባብሮ ፈትሾ፤ ሲታዩም በሰላማዊ መንገድ አውርዶ አጣጥፎ በክብር የሚያስቀምጥበት፤ ምንም አይነት እንደዚህ አይነት ነገር የማይታይበት በዓል እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።" አቶ ሽመልስ አብዲሳ/የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የኢሬቻ ሰላም ሩጫ ላይ በርካታ ሰዎች ተሳትፈዋል። ከአማራ ክልል፣ ከደቡብ ክልል ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 500 ገደማ አትሌቶችም በሩጫው ተሳትፈዋል።

በሩጫው በክብር እንግድነት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት የተገኙ፣ አቶ አዲሱ አረጋ እና ሌሎችም የመንግስት ሹማምንት ተገኝተው ነበር። በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች፣ አትሌቶች አርቲስቶች የዝግጅት አካል ነበሩ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ እና ሌሎችም በእንግድነት በቦታው ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia