TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትኩረት...‼️

በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ግድያ፣ አፈና እና የንብረት ጉዳት የማይቆም ከሆነ ስራ #ለማቆም እንደሚገደዱ የኢትዮዽያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስታወቀ።በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር እና በሀረርና ድሬደዋ አካባቢዎች ባሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስ እንግልት በተለይ የከፋ መሆኑ ተገልጿል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰላ👆

በአሰላ ከተማ በተፈጠረው ግጭት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአሰላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ፎቶ: #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እነ አቶ ጌታቸው አሰፋን "የፌድራል ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ" የሚለው መረጃ "መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ትእዛዝ ተሰጠ" በሚለው እንዲታረም የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ለሚዲያዎች በጻፈው ደብዳቤ ገለጸ።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህርዳርን ጨምሮ በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግላይ ይገኛሉ። መምህራኑ የደሞዝ ጭማሪን ጨምሮ ልሎች ጥያቄዎችን አንስተዋል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

በፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት፣ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፈለገ ህይዎት ሆስፒታል አካባቢ የተኩስ ልውውጡ አሁንም እንዳለ ተሰምቷል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

አልፎ አልፎ ከሚሰማ ተኩስ ውጭ፣ የተኩስ ልውውጡ ቆሟል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል መንግስት ላይ ተሰነዘረ ያሉትን "መፈንቅለ መንግስት" አወገዙ። አሜሪካን ሀገር የሚገኙት የአዴፓ ሊቀመንበር "የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በመከታተል አስፈላጊው #እርምጃ ይወስዳል" ብለዋል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

መንግስት #በባህርዳር ከተማ ተሞከረ ባለው መፈንቅለ መንግስት ክስተቶችን ያስተናገዱ ዋና ዋና ቦታዎችን በካርታዎቹ ላይ መመልከት ይቻላል። ካርታውን ያይን እማኞች ነን ያሉ ግለሰቦችና የመንግስት ባለስልጣናት የተናገሩትን መሰረት ያደረገ ነው።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ዶክተር አምባቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው የተገደሉበት የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት በከተማ ማህል የሚገኝ ባለ 3 ፎቅ ህንጻ ሲሆን ዘወትር ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለታል።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ብርጋዴር ጄነራል #አሳምነው የሚኖሩበትና ትዕዛዝ ሲሰጡበት ነበር የተባለው 'ገስት ሀውስ' በጣና ዳርቻ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት በጫካ የተከበበ ባለ 2 ፎቅ ህንጻ ነው። ይህ ህንጻ ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት 1 ፌርማታ ይርቃል።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የክልሉ ም/ደህንነት ሀላፊና የፕሬዝደንቱ ሹፌር ታገቱበት የተባለውና "መፈንቅለ መንግስት" አድራጊዎች እንደካምፕ የተጠቀሙበት የአማራ ስራ አመራር ተቋም ከገስት ሀውሱ በ3 ፌርማታ እርቀት ይገኛል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ና በአባይ ወንዝ ይዋሰናል።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ከግድያው ቀደም ብሎ የክልሉ የጸጥታና የደህንነት ሀላፊዎች ተሰበሰቡበት፣ ቀጥሎም እገታ ተፈጸመባቸው የተባለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስርያቤት ከፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ቢያንስ በ3 ወይም በ4 ፌርማታ ይርቃል። በዚሁ ህንጻ በጸጥታ ሀይሎች መካከል ለሰዐታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ሕንጻው የሚገኝበት አካባቢ የአማራ ቴሌቪዥንና ራዲዮን ጨምሮ አብዛኞቹ የክልሉ መንግስት ቢሮዎች ይገኛሉ።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በቅዳሜ ከፍተኛ ጥቃት ካስተናገዱ የከተማው አካባቢዎች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚኖሩበት ቀበሌ ሶስት የሚገኝ በአጥር የተከለለ የመኖሪያ መንደር (gated community) አንዱ ነው። በፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግቢውን ከሚጠብቁ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ቢያንስ 6 ተገለዋል። በግቢው ከሚኖሩ ባለስልጣናት ጋርም የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የተገደሉባት #ዘንዘልማ 'ከገስት ሀውሱ' በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ 'ሳተላይት' ከተማ ናት። በከተማዋ የግብርና ኮሌጅ የሚገኝ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ በአብዛኛው ጫት በማምረት የሚተዳደሩ ናቸው። አካባቢውም በጫት ማሳ የተሸፈነ ነው። በከተማው ምዕራባዊ ዳርቻ የኢ.መ.ሠ ምዕራብ ዕዝ ዋና መስሪያቤትና የኢ.አ.ሀ ሰሜን ምድብ ዋና ጣቢያን ጨምሮ የወታደርና የፌ. ፖሊስ ካምፖች የሚገኙ ሲሆን፣ ቃል አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን እንዳሉት በክልሉ ም/ፕሬዝደንት ግብዣ ወደ ከተማው እንዲገቡ ሆኗል። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም። ካምፖቹ ለሰዐታት የተኩስ ልውውጥ ከተደረገበት የፖሊስ ኮሚሽን ህንጻ በቅርብ ዕርቀት ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የፌድራል ሀይሎች ስንት ሰዐት ላይ ወደ ከተማ እንደገቡ አቶ ንጉሱ አልተናገሩም።

Via #elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia