TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠንቀቁ⚠️ በምስሉ የተያያዙት በኦንላይን " ቀላል በሆነ ስራ ብዙ ትርፍ ታገኛላችሁ " በሚል #የማጭበርበር ስራ ተታለው ገንዘባቸውን የላኩ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ እና ያጨብረበሯቸውን አካላት የቴሌግራምና የዋትአፕ አድራሻ የሚያሳይ ነው። " ቀላል ስራ፣ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ " በሚል ከ65 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ምንም እንኳን አጨብረባሪዎቹ በውጭ ሀገር…
#ተጠንቀቁ ⚠️

ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም።

የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ ፣ ይህ እድል ለነሱ የተመቻቸ " እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

ቅድመ ክፍያ እንደሌለው ፤ ከ100 ብር አንስቶ እስከ 50 ሺህ ብር በቀን የሚያስገኝ እንደሆነም መልዕክቱ ይገልጻል።

እነዚህ አጭበርባሪዎች የሚያጭበረብሯቸው ሰዎች የሚያናግሩበት መንገድ ፍፁም ትህትና የተሞላበትና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ስለሆነ በተበዳይ ዘንድ ጥርጣሬ እንዳይጫር ያደርጋሉ።

ልክ የማግባባት ስራቸውን ከሰሩ በኃላ ትንሽ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሆነ በመግለፅ ወደ " ጎግል ማፕ/ ሎኬሽን " ገብተው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አድራሻ ስር ጥሩ አስተያየት እንዲሰጡ ያዟቸዋል። (ይህ ከማጭበርበሪያ መንገድ አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም)

የሚጭበረበረውም ሰው እጅግ በጣም ቀለል ያለ ስራ ስለሆነ የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣቱን የሚገልጽ screenshot ለአጭበርባሪዎቹ  ይልካል። እነሱም አካውንቱን ይጠይቃሉ።

ከዚህ በኃላ ነው ዋናው ጨዋታ የሚጀመረው።

ሰዎቹ ለተሰራው ስራ ክፍያ በሚል ከ300 - 1,000 ብር ከዚህም ከፍ ያለ ገንዘብ ያስገባሉ። ይህ ሰዎችን የማሳመኛና እንዳይጠራጠሩ ማድረጊያ መንገዳቸው ነው።

ይቀጥሉና ታስክ ይሰጣችኋል ስሩ ይላሉ። በተሰራው ስራ ልክም የተወሰነ ገንዘብ ይልካሉ። ይህ እንደ ሰውየው የመክፈል አቅም እየተገመገመ የሚደረግ ነው።

በዚህ መኃል ላይ " ኮሜርሻል ቤኔፊት " የሚል ነገር ያመጣሉ ይኸውም ከ1,000 ብር እስከ 1,000,000 ብር ሰዎች እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው። ሰዎች ባስገቡት ብር ልክም በሰሩት ቀላል ስራ በፐርሰንት ትርፍ እንዳለው ይነገራቸዋል።

ለምሳሌ ፦ የሚጭበረበረው ሰው በዚህ ማታለያ ተታሎ 1000 ብር ቢያስገባ ሰዎቹ መልሰው በደቂቃ ውስጥ 1500 ብር አድርገው ያስገባሉ። (ይህ አንዱ የማሳመኛ መንገዳቸው ነው)

በዚህም የሚጭበረበረው ሰው ብሩን ከፍ በማድረግ ብዙ ትርፍ ለማግኘት ሲል በዛ እያደረገ ብር ይልካላቸዋል።

የተጭበርባሪውን ሰው የመክፍል አቅም ገምግመው አጭበርባሪዎቹ የተላከው ብር ላይ 500ም ይሁን 5000 ብር ጨምረውበት መልሰው ይልካሉ። (ይህን እድታምኗቸውና ብዙ ብር እንድታስገቡ ማሳመኛ ነው)

ድጋሚ ሌሎች ስራዎዥ ይላሉ በዚህም ከፍ ያለ ብር እንድታስገቡ ያደርጋሉ። የላካችሁትን ብር እንዳታጡ የሚሳጣችሁን ስራ እንድትወጡ ይጠየቃል። እናተም ብራችሁ ተበልቶ እንዳይቀር የብሩን መጠን ከፍ ወደማድረግ ትሄዳላችሁ። (በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ሰዎቹ የምክፈል አቅማችሁን እያጠኑና ከፍ ያለ ብር ከቻሉ እስከ #ሚሊዮን ለመቀበል ጥረት ያደርጋሉ ስለሆነም በመሃል በመሃል የሰራችሁበትን እያሉ ያራሳችሁን ብር መልሰው ይልኩላችኃል)

የመክፈል አቅማችሁንም አይተው ለዚህ ማጭበርበር ስራ ታልሞ ብቻ ወደ ተከፈተው ግሩፕ እንድትገቡ ይደረጋል። (ሁሉም ግሩፑ ውስጥ ያለው አካውንት የአጭበርባሪዎቹ ነው)

እንዲህ እንዲህ እያለ በዛ ያለ ብር ከፈፀማችሁ በኃላ ስህተት ሰርታችኋልና እሱን ለማረም ስራችሁን ቀጥሉ ይላሉ። እናተም ብራችሁን ላለማጣት ውስብሰብ ችግር ውስጥ ትወድቃላችሁ።

በመጨረሻም እየተጭበረበራችሁ እንደሆነ ስታውቁ ታቆማላችሁ። ብራችሁም መና ሆኖ ይቀራል። ሰዎቹ ግን ብር አስገቡ ያኛውን ብር ለማስመለስ ማለታቸውን ይቀጥላሉ።

ብር የሚያስልኩት ኢትዮጵያ ባለ ሰው አካውንት ነው። 

በዚህ መንገድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባጣራው ብቻ ከ150 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ይህም የሰዎችን ህይወት አመሰቃቅሏል።

ለምሳሌ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሆነው ስማቸውን በይፋ መግለፅ የሚያስፈልግ ሰዎች #የተጭበረበሩት የገንዘብ መጠን እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
1. 600 ሺህ ብር
2. 470 ሺህ ብር
3. 300 ሺህ ብር
4. 300 ሺህ ብር
5. 150 ሺህ ብር
6. 150 ሺህ ብር
7. 100 ሺህ ብር
8. 80 ሺህ ብር
9. 80 ሺህ ብር
10. 65 ሺህ ብር

ይህ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው።

በመሆኑንም ፦

1ኛ. ማንኛውም የቴሌግራም ሆነ የዋትስአፕ የውጭ የማይታወቅ መልዕክት አትመልሱ።

2ኛ. በምንም ተአምር በትንሽ ብር ኢንቨስት አድርጉና ትርፍ አግኙ የሚሉ ሰዎችን አታናግሩ አትመኑ ተጠራጠሩ።

3ኛ. አሁንም በዚህ ውስብስብ ነገር ውስጥ ያላችሁ ተጨማሪ ብር እንዳትበሉ አቁሙ።

በቀጣይ በዘርፉ ያለ የባለሞያ አስተያየት እናቀርባለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia