TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና⬆️ከ1997 ጀምሮ ታጥረው የቆዩ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው #ተቋርጦ ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ግዜ ታጥረው የተቀመጡ በመንግስት፣ በግል ባለሀብቶችና በተለያዩ የዲፕሎማቲክ ተቁዋማት ተይዘው የነበሩ አጠቃላይ ስፋታቸው 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ መሬቶች የሊዝ ውላቸው ተቁዋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ውሳኔ ተላለፈ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ከካቢኔ አባላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ነው ውሳኔውን ያስተላለፉት።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግስት የተያዙ 11 ቦታዎችን። ጨምሮ በድምሩ 154 በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎች ለህዝብ ጥቅም ተመላሽ ይደረጋሉ።

ቦታዎቹ በዝርዝርም:-

1, ከግል ባለሀብቶች 95 ቦታዎችን በካሬ 456,428.00/ አራት መቶ ሀምሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ ስምንት ካሬ/

2, ከመንግስት መስሪያ ቤቶች 19 ቦታዎችን በካሬ 127,140.93/ አንድ መቶ ሀያ ሰባት ሺህ አንድ መቶ አርባ አንድ ካሬ/

3, የሸራተን ማስፋፊያን ጨምሮ ከሚድሮክ ግሩፕ 11 ቦታዎችን በካሬ 549,241.00 /አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ካሬ/

4, ከዲፕሎማቲክ ተቁዋማት 18 ቦታዎችን በካሬ 250,413.89 / ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ አራት መቶ አስራ አራት ካሬ/

5, ከፌደራል ተቁዋማት መከላከያና ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽንን ጨምሮ 11 ቦታዎችን በካሬ 2,743,200.00 / ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ካሬ ባጠቃላይ 154 ቦታዎች በካሬ 4,126,423.83/ አራት ሚሊየን አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት ካሬ የሊዝ ውላቸው
ተቋርጦ ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።

ቦታዎቹ ከ 1997 እስከ 2004 በተለዬዩ ጊዜያት የተላለፉና እስካሁን ምንም አይነት ልማት ሳይከናወንባቸው ታጥረው የተቀመጡ ናቸው።

📌ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ጨምረው እነዚህና መሰል ቦታዎች የከተማዋን ልማት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆኑ ጠቅሰው ይህ ስራ የአንድ ጊዜ ዘመቻ ሳይሆን ከዚ በኹዋላ መስተዳድሩ ቦታ ወስደው ወደልማት የማይገቡ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ባለሀብት ላይ ጥብቅ ክትትል አድርጎ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል።

©Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንተርኔት የተቋረጠው "ለሀገራዊ ጥቅም" ነው...
/ከኤልያስ መሰረት/

ኢንተርኔት ለበርካታ ሰአታት #ተቋርጦ የነበረው "ለሀገራዊ ጥቅም" ሲባል እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አሳውቀዋል። ይህም እየተሰጠ ካለው ሀገር አቀፍ ፈተና ጋር ይያያዛል ተብሎ ቢገመትም "እኛ ይሄ ነው ማለት አንፈልግም፤ የሚመለከተው አካል ያሳውቃል ብለን እናምናለን" ብለዋል። ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት አረጋግጫለሁ እንዳለው መቋረጡ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተከስቶ ነበር።

Via Ethio NewsFlash/@eliasmeseret/
@tsegabwolde @tikvahethiopia