TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንሰፔክተር ከበደ ገመዴ እንደገለጹት በይርጋጨፌ ከተማ #ትላንት ማምሻውን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ቤት ከሙሉ ንብረቱ ጋር #ሊወድም ችሏል።

በከተማው በተለምዶ #ደንቦስኮ ሰፈር በሚባለው አከባቢ በ25 ሊትር ጀርካኖች ተቀድቶ የተቀመጠ ነዳጅ #ፈንድቶ እሳት ማንሳቱን ተከትሎ አደጋው መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡

በአደጋው የስድስት ወር አራስ እናትና ልጇን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበት በይርጋጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን ተናግረዋል።

“ቃጠሎው ወደ ሌሎች ቤቶች #እንዳይዛመት ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ባደረጉት ጥረት ለማስቆም ተችሏል” ያሉት ኢንስፔክተሩ አደጋው በደረሰበት ቤት የችርቻሮ የነዳጅ ሽያጭ ይካሄድ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

በከተማው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጎዳና ላይ የነዳጅ ሽያጭ መበራከቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ንረትና እጥረት ከመታየቱም ባለፈ ለተለያዩ አደጋዎች መንስኤ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ከሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ባለፈ በአያያዝና አጠቃቀም ጉድለት ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia