TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የካራማራው ድል‼️

የካቲት 26 1970 አመተ ምህረት ወራሪው የሱማሊያ የዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት 41ኛ አመት የመታሰቢያ በዓል ነው፡፡

በአሜሪካ እና በሶቪየት ሕብረት ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው ወራሪውን የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያን አንድነት ዳግም የታየበት ስለመሆኑም ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የካራማራ ድል ዘንድሮም ለ41ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያ(ናይሮቢ)🛫

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር #ለመወያየት በአሁኑ ወቅት ወደ #ናይሮቢ ኬንያ አቅንተዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ በሶማሊያና ኬንያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀ መንበርነታቸው በቅርበት በመከታተል ወደ #ዕርቅ የሚመጡበትን መላ እያፈላለጉ ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኬንያታና የሶማሊያው አብዱላሂ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት በዘለቁ ወቅት ከሁለቱም ጋር ባደረጉት ምክክር፤ ይህንን የኬንያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት ለማመቻቸት ወስነው ነበር። ይህ የውይይት መድረክም በሁለቱ መካከል ያለውን የተካረረ ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይታመናል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ። ለ6 ቀናት የቆየው የዕሳት ቃጠሎ ከ160 እስከ 200 ሄክታር የሸፈነ ቦታ ላይ የሚገኝ አሰታን(Alpine) አውድሟል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ የካቲት 27/2011 በእጣ ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፈው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር እና በዕጣው ለመግባት የሚያስፈልገው የቁጠባ መጠን፦

ሀ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ዝርዝር በቁጥር

1. ባለ 1 መኝታ = 3,060
2. ባለ 2 መኝታ = 10,322
3. ባለ 3 መኝታ = 5,194
በጠቅላላ ለ2ኛው ዙር ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ 18,576 የ40/60 ቤቶች ናቸው

ለ. በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ያሉ ተመዝጋቢዎች

1. በባለ 1 መኝታ = 11,699
2. በባለ 2 መኝታ = 57,277
3. በባለ 3 መኝታ = 56,138
በጠቅላላ 125,114 ተመዝጋቢዎች በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ይገኛሉ።

ሐ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን (ለሁሉም የመኝታ ዓይነት በምዝገባው ወቅት ከነበረው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 40% እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ)

1. ለባለ 1 መኝታ = 162,645x0.4 = 65,058 ብር
2. ለባለ 2 መኝታ =250,000x0.4 = 100,000 ብር
3. ለባለ 3 መኝታ = 386,400x0.4 = 154,560 ብር

መ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የዕጣ ፕሮግራም ብቁ (ዝቅተኛ የቁጠባ መጠንን ያሟሉ) ሆነው ለዕጣው ተወዳዳሪ የሚሆኑ የተመዝጋቢዎች ብዛት በቁጥር
1. በባለ 1 መኝታ = 5,502
2. በባለ 2 መኝታ = 25,634
3. በባለ 3 መኝታ = 26,126

በጠቅላላ 57,262 ብቁ ተመዝጋቢዎች ለ18,576 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ በሚገኘው የአፄ ቴዎድሮስ ሐውልት ላይ ጉዳት ያደረሰችው ግለሰብ #በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው የወንጀል ዐቃቤ ሕግ አቶ ድረስ ዘለለው ለኢዜአ እንደተናገሩት ቅጣቱ የተላለፈባት ነዋሪነቷ በጎንደር ከተማ በሆነው በወይዘሮ መንደሬ እያዩ አባተ ላይ ነው፡፡ ግሰሰቧ የካቲት 5 ቀን 2011 ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ30 ሲሆን፣ ፒያሳ አደባባይ ላይ የቆመውን ሐውልት ቀኝ እጅ ጎራዴ ላይ ጉዳት ማድረሷ በሦስት ምስክሮች በመረጋገጡ ነው፡፡ ግለሰቧ በወንጀል ሕግ ቁጥር 690 ንዑስ ቁጥር ሁለት የሕዝቦች የጋራ ሐውልት በሆኑ ታሪካዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት በማድረስ የተደነገገውን አንቀጽ ተላልፋ መገኘቷንም አመልክቷል፡፡ ተከሳሿ በቀረበባት ክስ በፍርድ ቤት ወንጀሉን አልፈጸምኩም በሚል ክዳ ብትከራከርም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባትን ማስረጃን ባለማስተባበሏ ቅጣቱ ተወስኖባታል፡፡ የጎንደር ከተማ ፍርድ ቤት ግለሰቧ የቤተሰብ አስተዳዳሪና ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ የሌለባት መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት ተይዞላታል፡፡ ግለሰቧ የፈጸመችው ወንጀል እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን በቅጣት ማቅለያነት እንደያዘላት ዐቃቢ ሕጉ አስረድተዋል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
20/80🔝

ነገ ረቡዕ የካቲት 27 በእጣ ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፈው የ20/80 #የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ዝርዝር እና #በዕጣው ለመግባት የሚያስፈልገው የቁጠባ መጠን።

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሞያሌ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ለመፍታት ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ የፊታችን ሀሙስ የሚካሄድ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ-ለሚመለከተው አካል‼️

የ20/80 ቤቶች መረጃ ላይ በየቤቶቹ አይነት የቆጠቡ የተመዝጋቢዎች ብዛት ይፋ ያልተደረገበት ምክንያት ጥያቄ አስነስቷል። የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሚመለከተው አካል በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወደ አሰብ ወደብ መዳረሻ ያለው 60.6 ኪሜ የኤሊዳር - ማንዳ - ቡሬ (ኤርትራ ድንበር) መንገድ ጥገና መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል። ለጥገና 120 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia