TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጉጂ ዞን‼️

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች #ማስተማር ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ  አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል። በዞኑ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል። በአባገዳዎች ሰብሳቢነት አስተዳደሩ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ጋር በመወያየት በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቁመዋል። በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎችና በሁለት ከተሞች የተካሄደውን የሰላም ውይይት ተከትሎ ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ማስተማር መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

በፀጥታ ችግር አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትም በአብዛኛው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በዱግዳ ዳዋና ቡሌ ሆራ ዙሪያ ወረዳ ያልተከፈቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር በአሁኑ ወቅት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑንም አቶ አበራ አመልክተዋል፡፡ በጉጂ ዞን በአሁኑ ወቅት 592 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ። በትምህርት ቤቶቹ ከ300 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችም መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia