TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🕒ቀጠሮ ያዙ ዛሬ ውይይት ይኖረናል🕒 ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ በሁለት መልኩ የሚታይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተስፋ የሚሰጡ ተግባራት እያየን እንገኛለን። በሌላ በኩል ዛሬም የመፈናቀል፣ የሞት እና የጉዳት ዜናዎችን መስማት ቀጥለናል። ከሰሞኑን ደግሞ በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሰማናቸው ዜናዎች አሉ። ዛሬም የግለሰቦችን ፀብ ወደብሄር መቀየሩ አልቆመም፣ ወንጀል ሰርቷል ተብሎ የተጠረጠረም…
እንኳን ደህና መጣችሁ!

ውይይታችን ከዚህ ሰዓት አንስቶ ለቀጣይ 30 ደቂቃ ይቀጥላል!

.ሁላችሁም በየቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ስለሀገራችሁ ተወያዩ ተነጋገሩ...(እናት አባቶች ልጆቻችሁን ሰብስቡ እና ተነጋገሩ)

.የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየዶርማችሁ ሆናችሁ ውይይቱን ተቀላቀሉ...

ስለሰላም እንነጋገር! ስለአንድነት እንነጋገር! ስለኢትዮጵያ እንነጋገር!

የምታነሷቸውን ጠንካራ ሃሳቦች ለኛ መልካችሁን እንዳትረሱ!(በድምፅ ቢሆን ይመረጣል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ሀገሬ #ኢትዮጵያ መልካምሽ ይወራ
ከምድርሽ ላይ ይራቅ ፍዳና መከራ
ልጆችሽ በሙሉ በክብርሽ #እንኩራ
.
.
ኢትዮጵያን ሁሉ እህት ወንድሞች
በደስታ በሀዘን የአንድ እናት ልጆች
ጥላትን መክቶ ሀገር የሚያድን
ልባችን ቅናዊ በመከራም ቀን
.
.
ፍቅር አለን ስላንቺ ኢትዮጵያ
ክብር አለን ስላንቺ ኢትዮጵያ
ባንቺ ያምራል ወግ ማረጉ
ሀዘን ሆነ ሰርጉ
.
.
.
በሰላም በፍቅር ተቻችሎ ነዋሪ
ልጅ እናት አባቱን ጧሪና ቀባሪ
አምላክም ባርኮነው ጥንትም የፈጠረሽ
የቅዱሳን ፀሎት ሁሌም አይለይሽ!
.
.
ዞሮ መግቢያ ቤታችን ኢትዮጵያ
የዘር ሀረግ ውርሳችን ኢትዮጵያ
ሰላም ይሁን ሳር ቅጠሉ
ሜዳና ገደሉ
.
.
ሁሉም እንደያቅሙ ሰርቶ የሚያድርብሽ
የድህነት ጩኸት የማይሰማብሽ
የሰው ልጅ በፍቅር እንዲኖር ተስማምቶ
ዙሪያሽ ጥጋብ ይሁን ገበታሽ ሞልቶ
.
.
ሰላም ይሁን ሳር ቅጠሉ
ሜዳና ገደሉ

©ራሔል ዮሀንስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዚህ ቀደም እንደተነጋገርነው፦

TIKVAH-UNIVERSITY የተመደበለትን ጊዜ አጠናቋል። ቻናሉ ከሚዘጋ ወደ TIKVAH-DAILY( @tikvahdaily ) ተቀይሮ የተለያዩ መልዕክቶች እና መረጃዎች እንዲተላለፉበት በአባላቶች ተወስኗል(በእንግሊዘኛ ብቻ)።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ፦

•ልዩ ዜናዎች ከመላው አለም
•አነቃቂ መልዕክቶች
•እውነታዎች
•የተመረጡ አባባሎች

🔹ቻናሉ ያለምንም ማስታወቂያ በቆንጆ አቀራረብ በቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶችን ያቀርባል።

https://publielectoral.lat/joinchat/AAAAAEcez-WeEn84b8FUyA

@tsegabwolde @tikvahdaily
መከላከያ ሰራዊት‼️

በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት የተዘጉ የፌደራል መንገዶችን #በማስከፈትና አከባቢዉን #በማረጋጋት ህግ የማሰከበር ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አስታወቀ፡፡

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል #አስራት_ዴኔሮ በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እንደተናገሩት በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ክልል ህዝቦችና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ተዘግተዉ የነበሩ የፌደራል መንገዶችን ሙሉ በሙሉ የማስከፈት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ አሶሳ፣ከነቀምት ቡሬ ጎጃም ከነቀምት እስከ ኤሉአባቦራ ድረስ ያለዉን የፌደራል መንገዶች ከመዘገትና ከፀጥታ ስጋት ነፃ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወሰን አከባቢዎች በተፈጠረዉ አለመረጋጋት የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራም ሜጀር ጄኔራል አስራት ተናግረዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ አርሶ አደሩም ሆነ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች ከእርሻ ማሳቸዉ ላይ ያልሰበሰቧቸዉን የሰብል ምርቶች እንዲሰበሰቡ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ድንበር አከባቢ እየተበራከተ የመጣዉን ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝዉዉር ለመግታት እንደሚሰራ የገለፁት ዋና ኣዛዡ ህገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀዉ ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትና ተባባሪዎች ላይ እርምጃ በመዉሰድ የህግ የበላይነት የማስከበር ስራዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሊበን ጃዊ ወረዳ ፖሊስ‼️


በሕገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ዳኖ ወረዳ ሲጓጓዝ የነበረ 521 ሊትር ዘይትና ስምንት ኩንታል ስኳር በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የሊበን ጃዊ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ዓለሙ ገላና ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ስኳሩና ዘይቱ በቁጥጥር ሥር የዋለው ኅብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አዲስ አበባ 27655 በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ ቶኬ እሬንሳ ቀበሌ ውስጥ  የተያዘው ታህሳስ 4/2011 ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡

አሽከርካሪውና ረዳቱ  መኪናውን አቁመው በመሰወራቸው ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።

ሕገ-ወጥ የንግድ ዝውውር ሃገሪቱን ስለሚጎዳ  ኅብረተሰቡ ወንጀሉን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር ኢንስፔክተር ዓለሙ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባ‼️

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በታረዙና በተራቡ ታዳጊዎች እየተሞሉ ነው፡፡ ውሎ ባደረ ቁጥር የጎዳና ላይ ወጣቶች በዝተው ይታያሉ፡፡

ከየክልሉና ከአዲስ አበባ ወደ ጎዳና የሚወጡ ታዳጊዎችን ወደ ትክክለኛው ፈር አስገብቶ ብቁ ዜጋ ለማድረግ ተከታታይ ጥረት ሲደረግ አይታይም፡፡ ወይም ውጤቱ አልታየም፡፡

ታዳጊዎቹ በዚያ ሁኔታ መገኘታቸው ቢያሳዝንም ኑሯቸው ወደ መጥፎ ባህርይ እየመራቸው ለሱስ የተጋለጡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፣ በወንጀል ተሳታፊ አድርጓቸዋል፡፡ እንዲህም ከቀጠለ ዛሬ ልብ ያልተባለ ነገር ነገ ቢታገሉት የማይጥሉት ችግር ይሆናል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምን አስቦ ይሆን፡፡

ከሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ከተማ‼️

ትናንት በደጋፊዎች ግጭት ምክንያት ሳይደረግ የቀረው ጨዋታ ዛሬ እንደሚከናወን ቢገለፅም የሀዋሳ ቡድን አባላት በአሁኑ ሰዓት #ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የትናንቱ የስድስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ መካከል ከመደረጉ አስቀድሞ በደጋፊዎች መካከል የተነሳው ግጭት ጨዋታው እንዳይካሄድ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። በመሆኑም ዛሬ 9፡00 ላይ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም ሀዋሳ ከተማዎች ዛሬ ማለዳ ወደ መቀመጫ ከተማቸው ሀዋሳ ጉዞ መጀመራቸው ታውቋል።

ሶከር ኢትዮጵያ ጉዳዩን አስመልክቶ ከክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ጠሀ አህመድ ጋር ባደረገችው ቆይታም ተከታዩን ምላሽ አግኝታለች። ” ጨዋታውን ማካሄድ አንችልም ፤ በኛ በኩል ከ20 በላይ ደጋፈዎቻችን ተጎድተውብናል። በአጋጣሚም ቢሆን ወደ ስድስት የሚጠጉ ተጫዋቾቻችን ጉዳት ገጥሟቸዋል። በዚህ ሁኔታ ላይ ደግሞ ተጫወቱ ማለት እጅጉን ይከብዳል። እኛ አስቀድመን እንግዳ ቡድን ስለሆንን የቀኙን ጥላ ፎቅ ስጡን ስንል የሰጡን ያልሆነ ቦታ ነው። ያ ቢሆን ይህ ሁሉ አይነሳም ነበር። በዚህ ነገር ደስተኛም አልነበርንም። ሁኔታውም ቀስ በቀስ ወደ አስፈሪ ድርጊት ሄዷል። ስለዚህ በዚህ መንፈስ ውስጥ ሆነን ለመጫወት የሚያስችል ሞራል ላይ አይደለንም።

በሌላ በኩል ባገኘነው መረጃ የሊግ ኮሚቴው በትናንቱ ውሳኔ መሰረት ጨዋታው ዛሬ እንደሚካሄድ በመጠበቅ ላይ ሳለ ሀዋሳዎች መሄድ በመጀመራቸው ሀሳባቸውን ቀይረው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ በስልክ ግንኙነት ለማድረግ ጥረት ላይ ቢሆንም እስካሁን እንዳልተሳካለትና ሀዋሳዎችም ጉዟቸውን እንደቀጠሉ ታውቋል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ🔝

ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች ተገቢው መልስ #አልተሰጠንም ያሉ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቋሙን ለቀው በመውጣት ላይ ይገኛሉ። የግቢው በር ግን እስካሁን እንደተዘጋ ነው። ምዝገባ ያላከናወኑ ተማሪዎችን አላስተናግድም ያለው ተቋሙ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ አግዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድብቅ እስር ቤቶቹ‼️

በአዲስ አበባ የተገኙት 7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች #ንብረትነታቸው የቤቶች ኮርፖሬሽን መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሸገር ራድዮ ተናገረ፡፡

ዜጎች የተለያየ ስቃይ እና እንግልትን አሳልፈውባቸዋል የተባሉት እነዚህ ድብቅ እስር ቤቶች በቀድሞው የኪራይ ቤቶች ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሲተዳደሩ እንደቆዩ #ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደነገሩን ከ7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል የሚደረግባቸው
ምርመራ ተጠናቆ የተወሰኑት ለቤቶች ኮርፖሬሽን ተመልሰዋል፡፡ የቀሩት ግን የሚካሄደው ምርመራ ስላላለቀ ታሽገው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በድብቅ እስር ቤትነት ሲያገለግሉ የቆዩት ቤቶች በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ የሚገኙ እንደሆኑ ግን አቶ ዝናቡ በግልፅ ለመናገር #አልፈቀዱም፡፡

#የቤቶች_ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚያስተዳድራቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶቹን ገሚሱን ለመንግስት ሹማምንት በመስጠት የተረፉትንም ለተለያዩ ግለሰቦች በዝቅተኛ ዋጋ #በማከራየት ያስተዳድራል፡፡

ድብቅ እስር ቤት ሆነው ቆይተዋል የተባሉት ቤቶች ኮርፖሬሽኑ ለባለስልጣናት ከሰጣቸው መኖሪያዎች መካከል ይሁኑ ወይንም ሌላ እስካሁን አልታወቀም፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

አቶ #አወል_አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው #ተሾሙ። የክልሉ ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ምክር ቤቱ በቀጣይም የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ በመምረጥ በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በተዘጋጀ አዋጅ ላይም ውይይት ያደርጋል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሲያጋጥም የነበረው የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ችግር #መፈታቱን በመከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥሜጀር ጀኔራል አስራት ደኔሮ አስታውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእንባ የታጀበ ተማፅኖ...

የኢፌዲሪ የሠላም ሚኒስትርና የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ወ/ሮ #ሙፍሪያት_ካሚል በእንባ የታጀበ ተማጽኖ
-
"...እኛ #ኢትዮጵያውያን በድርጅታችን ውስጥ የምንገኝ አመራርና አባላት አንዳችን የቆምነው በአንዳችን የተከፈለ የህይወት፣ የአካል፣ የደምና የአጥንት መስዋእትነት ነው። እኔው ውስጥ እናንተ አላቹህ ፥ እናንተ ውስጥ እኔ አለሁ፥ ታድያ እርስ በርሳችን በእብሪት፣ በትእቢት፣ በንቀት ዓይን ላይ በመተያየት አንዳችን የአንዳችን መጥፋት፣ መበርከክ፣ መጎተት፣ አንገት መድፋት እንዲኖር ፈለግን። …"

(በመቐለ ከተማ ትላንት በተካሄደው የኢህአዴግ የሴቶችሊግ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር)

©DireTube
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨዋታው ዛሬ ይደረጋል...

በስድስተኛ ሳምንት ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ መርሀ ግብር ወጥቶለት የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ ጨወታ ከጨዋታው አስቀድሞ በተፈጠሩ የደጋፊዎች ግጭት ምክንያት ያልተገቡ ትዕይንቶችን ካሳየን በኋላ ጨዋታው ሳይደረግ ማደሩ ይታወሳል።

ትላንት ይህ ጨዋታ ለዛሬ 9 ሰዓት በዝግ ስታዲየም እንዲደረግ የዕለቱ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች መወሰናቸው የሚታወስ ቢሆንም የሀዋሳ ከተማ ክለብ “ተጫዋቾቼ ተጎድተውብኛል፤ ደጋፊዎቻችንም ጉዳት ገጥሟቸዋል፤ አንጫወትም” በማለት ዛሬ ማለዳ ወደ ሀዋሳ ጉዞ በመጀመራቸው ጨዋታው የመደረጉ ነገር አጠራጥሮ ነበር።

አሁን ደግሞ አይደረግም ሲባል የነበረው ጨዋታ እንደሚደረግ ሶከር ኢትዮጵያ አገኘሁት ባለው መረጃ ጠቁሟል። ዛሬ 4 ሰዐት ላይ በተደረገ የቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ በተያዘለት ሰዓት እንዲደረግ የተወሰነ ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች በቦታው ሲገኙ በጉዞ ላይ የነበሩት የሀዋሳ ከተማ ተወካዮች አልተገኙበትም። ይሁንና ባቱ ከተማ (ዝዋይ) ደርሰው የነበሩት ሀዋሳዎች ፌድሬሽኑ አስቸኳይ ጠንከር ያለ #ማስጠንቀቂያን ለክለቡ በመላኩ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሲገኙ
በአሁኑ ሰዓት ዐለም ጤናን እያለፉ መሆኑ ታውቋል። በዚህም ጨዋታው ምናልባትም ሀዋሳ በጉዞ ላይ ከመሆኑ አንጻር በአንድ ሰዓት ተግፍቶ 10 ሰዓት ላይ በዝግ ስታዲየም እንደሚከናወን ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በማረቆና መስቃን አካባቢ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አመራሮችንና ግለሰቦችን #በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለfbc አንደገለጸው ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ #በለጠ_ደራሮንና የመስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ #ሚፍታህ_ሸምሱን ጨምሮ ሌሎች የወረዳዎቹ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

በፖሊስ ኮሚሽኑ የማዕከላዊ ዞኖች የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተጠሪ ኮማንደር እንዳለ አበራ እንደተናገሩት፥ ከአስተዳዳሪዎቹ በተጨማሪ የሁለቱ ወረዳዎች አስተዳደርና ፀጥታና ፖሊስ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በህዳር ወር መጀመሪያ በተከሰተው ግጭት ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 69 መድረሱንም ነው ኮማንደር እንዳለ የሚናገሩት።

በዚሁ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ መስከረም ወር ላይ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘም ለዚሁ ጉዳይ በተቋቋመ ግብረሃይል ጉዳያቸው የተጣራ 115 ተጠርጣሪዎች ላይም የዕስር ማዘዣ መውጣቱንና በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ሰላምን በማስጠበቅና የህግ የበላይነትን በማስከበር ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንዲተባበር በፖሊስ ኮሚሽኑ የማዕከላዊ ዞኖች የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተጠሪ ኮማንደር እንዳለ አበራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሁለቱ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ከ43 ሰዎች በላይ ህይወት ሲያልፍ፤ ከ32 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ መፈናቀላቸውም ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፦

ከማረቆና መስቃን አካባቢ #ግጭት ጋር በተያያዘ የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ #በለጠ_ደራሮንና የመስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ #ሚፍታህ_ሸምሱን ጨምሮ ሌሎች የወረዳዎቹ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

ጥያቄዎቻችን አልተመለሱልንም ያሉ ተማሪዎች ተቋሙን ለቀው እንዳይወጡ መታገዳቸውን ተናግረዋል። የድጋሜ ምዝገባ ባለመፈፀማቸውም የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል። ተማሪዎች ተቋሙ ፍፁም ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል ቁርስ እና ምሳ ሳንበላ እስካሁን ቆይተናል። የምግብ አገልግሎት እንዳናገኝ ከተደረግን የግቢው በር ዘግቶ እኛን በረሀብ መቅጣት ተገቢ አይደለም ብለዋል።
.
.
በሌላ በኩል ትምህርት ለመቀጠል የተመዘገቡ ተማሪዎች ተቋሙ ባወጣው ማስታወቂያ፦ ከዛሬ ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ካርድ እንዲወስዱ አሳውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia