TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

#መሀመድ_ሁሴን 1ኛና #ዳኜ_አሰፋ 2ኛ ተከሳሽ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል ልዩ ቦታው አፍሪካ ካፌ ውስጥ ህዳር 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ 05፡30 ሰዓት ሲሆን በ1996 ዓ.ምየወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና 692/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀሙት አታላይነት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች ለጊዜው ባልተያዘው ግብረ አበራቸው አማካኝነት የግል ተበዳይ አቶ ታዬ ጀቤሳን አግኝተው 1ኛ ተከሳሽ እኔ ጅንአድ ውስጥ ነው የምሰራው 400 ፍሬ ባለ25 ሊትር ዘይት ትወስዳለህ አብርንም እንሰራለን ህጋዊ ደረሰኝም እሰጥሀለሁ ክፈልና ትወስዳለህ በማለት ሲለው2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ዘይቱ መኪና ላይ እስኪጫን ለመተማመኛ እንዲሆንህ ቼክ እሰጥሃለሁ በማለት 200,000 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኋላ የተሰወሩ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የአታላይነት ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አራዳ ምድብ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ደረቅ ቼክ ፅፎና ፈርሞ በመስጠቱ
ሁለተኛ ክስ መስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ የተከሳሾችን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ሁለት የሰው ምስክሮችን በማቅረብ አሰምቶ የተከራከረ ሲሆን ተከሳሾችም ባለመከላከላቸው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

በመጨረሻም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 27 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ያርማል በማለት 1ኛ ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እና 2000 ብር 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ በ2ዓመት ከ3 ወር እስራትና በ2000 ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia